ETHIO12.COM

ትህነግ በሪፈረንደምና በእርቀሰላም ፈረስ – “ወይ ድሉን ወይ ልጆቻችንን” ቀጣዩ የትግራይ የውስጥ ማዕበል

በሽንፈትና “ማፈግፈግ” መካከል አንድ እውነት እንዳለ የትግራይ ተወላጆችም ሆኑ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር አፋቸውን ሞልተው ሊከራከሩት የማይቻላቸው እውነት እንዳለ እየተነገረ ነው። እሱም” ወይ ልጄን፣ ወይ ድሉን” የሚለው የትግራይ ቤሰቦች ጥያቄ የመነሳቱ ጉዳይ ነው። ዛሬ ትህነግ “አመጣዋለሁ። እምበር ተጋዳላይ እንላለን” ብሎ ተነስቶ፣ ወደ መቀለ መመለሱን፣ ሲመለስም ሃይሉ ምንም ሳይሆንና ሳይጓደል መሆኑን አስታውቋል። እናም “ሃይላችን ካልተጓደለ፣ ድሉም ካልተገኘ ሎቻችን የት አሉ?” የሚለው ጥያቄ መነሳቱ አይቀሬ እንደሆነ፣ በአንዳንድ ቦታም ጭምጭምታው እንዳለ እየተደመጠ ነው።

ይህነግ በተሰበረበት የብሄር ብሄረሰቦች ካሚዮን እንደገና ጠጋግኖ ካሳፈራቸው ድርጅቶች መካከል የአንዱ ለጊዜው ስማቸው እንዳይገልጽ ጠይቀው የትህነግ ሰዎች “ግራ ተጋብተዋል” ሲሉ ለአሜሪካ ተባባሪያችን መረጃ አካፍለዋል። ግራ መጋባቱን ሲገልጹ የትህነግ አመራሮች በአንድ ፈረስ ላይ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ተቀምጠው ለመጋለብ እንደመሞከር አይነት ነው።

“በትግራይ እናት በቅስቀሳ ልጇን ወይም ልጆቿን ለትህነግ አስረክባ የድል ዜና ስትጠባበቅ ነበር። ብዙ እናቶች፣ ቤተሰቦች በተመሳሳይ በድል ላይ ድል እየታወጀላቸው፣ ደጋፊዎች ከልቅሶና ከአደባባይ ሰልፍ ርቀው የድል ከበሮ እያሰሙ ሳለ በድንገት ሃዘን ዋጣቸው” ያሉት መረጃ ሰጪው፣ በድንገት ሁሉም ነገር መቀልበሱና ራሳቸው በስልታዊ ማፈግፈግ ወደ ትግራይ መመለሳቸውን ማስታወቃቸው የውስጥ አለመግባባት እያስነሳ መሆኑን በጎንዮሽ ውይይት ከድርጅቱ ሰዎች በጆሯቸው መስማታቸውን አመልክተዋል።

“ድሉ ቢኖር” አሉ ” ድሉ ቢኖር በድሉ ስሜትና በድሉ እርካታ ልጃችን የት ገባ? ሳይሆን ለዚህ ድል ተሰዋ” የሚል ዜማ ልክ እንደቀድሞው ይዜም እንደነበር ምልከታቸውን አግርተዋል። አሁን ግን እናት ለልጆቿ ህይወት ማካካሻ የሚሆናት ምንም ነገር ሳይዝ ትህነግ ወደ ትግራይ መመለሱ ሃዘኑንን እንደሚያመረው፣ የደረሰውም ጉዳት ሰፊ በመሆኑ ሊሸፋፈን የማይቻል በመሆኑ አመራሮቹ ስጋት ላይ እንደወደቁ በጎንዮሽ ግንኙነታቸው ካደረጉት ውይይት መረዳታቸውን አመልክተዋል።

ከዙም ስብሰባ በዘለለ ከትህነግ ሰዎች ጋር በሚደረግ የግል ንግግር ግፋ ቢል በሶስት ወር ውስጥ በትግራይ ህዝባዊ ዓመጽ ሊነሳ ፣ በችግር ምክንያት ህዝብ ወደ አፋርና አማራ ክልል ሊጎርፍና ሊሰደድ እንደሚችል ትህነግ አስቀድሞ መረዳቱን ሰምተዋል። በዚህም ሳቢያ በግልጽ መደባውን ማወቅ ባይቻልም ባስቸኳይ መፍትሄ በሚል አመጹን ወይም ስደቱን ለመቅደም በተያዘ አቋም መለያየት ተፈጥሯል።

“መለያይቱ ታክቲካል ነው” ሲሉ ያብራሩት መረጃ አቀባያቸን፣ የአንደኛው ቡድን ሃሳብ “ሪፈረንደም እንዲካሄድ እንጠይቅ” የሚል ሲሆን ሁለተኛው ሃይል ” እንደ ሩዋናዳና ደቡብ አፍሪካ አይነት እርቀ ሰላም እናውርድ” የሚሉ ናቸው። ሁለቱም ሃሳቦች የተወለዱት በቅርብ ጊዜ ሊነሳ ሊነሳ ይችላል ብለው ባሰሉት ስሌት መሰረት የጦርነቱን ወሬ በዚህኛው መልኩ አስታግሶ ለማለፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

“ትህነግን እንደፓርቲ አሳቡን አካቶ እስከወዲያኛው ማክሰም” በሚል መርህ እየተንቀሳቀሰ ያለው መንግስት የትኛውን አካሄድ እንደሚደግፍ ባይታወቅም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቅርቡ ” ሌሎች ትህነግን ከላያቸው ላይ ታግለው እንደወረወሩት ሁሉ የትግራይ ሕዝብም ትህነግን ለመጣል አያንስም። ድጋፍ እናደርጋለን” ማለታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ጦር ወደ ትግራይ እንደማይገባ የታዘዘበትን ምክንያት ለማብራራት ” በስሜታዊነት አንወስንም” በሚል ጽሁፋቸው ነበር ይህን ያሉት።

መረጃ የሰጡት በሁለት የተከፍለውን ሃሳብ ከመግለጽ ውጪ እነማን የትኛውን አሳብ እንደሚያራምዱ አላብራሩም። ይሁን እንጂ አንድ ትልቅ ሚስጢር መስማታቸውን አልሸሸጉም። የእርቀ ሰላም አቋም የሚያራምዱት ወገኖች ከመንግስት ወገን ሰሚ አላገኙም። የእርቀ ሰላም ሃሳብ የሚያራምዱትና በስፋት ጽሁፍ የሚያሰራጩት ወገኖች የወረራውን ስልት የነደፉ፣በመንግስ በህግ የሚፈለጉና ዋራንቲ የተቆረጠባቸው ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክተዋል። የትኛው ሃሳብ ጎልቶ ሊወጣ እንደሚችል ግን የዜና ምንጭ አላመለከቱም።

የኢትዮጵያን ጉዳይ ጠንቀቀው ከሚያውቁ መካከል አንዱ የሆኑት የአትላንቲክ ካውንስሏ የአፍሪካ ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ብሮንዋይን ብሩተንና የባልሲሊ ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤት ሊቀመንበርና የዓለም አቀፍ ደኅንነት ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጀራልድ በጋር ባቀረቡትና በፎሬን ፖሊሲ በታተመው ጽሁፋቸው ዋናዎቹ የትህነግ መሪዎች እጃቸውን እንዲሰጡ ከትናት በስቲያ ምክረ ሃሳብ ለጆባይደን አስተዳደር ማቅረባቸው ይታወሳል። ጽሁፉ ምን አልባትም እርቀ ስለማ የማውረድ ሃሳብን በፍጥነት ለማራመድ እየተንቀሳቀሱ ካሉት የትህነግ ሰዎች ማንነት አንጻር ሲታይ ተገጣጥሟል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ከትግራይ እንዳገኘው ገልጾ ከሁለት ሳምንት በፊት በትግራይ ወላጆች ጩኸት እያሰሙ መሆናቸውን አመልክቶ እንደነበረም አይዘነጋም። ከትህነግ ወገን ግን የትግራይ ሕዝብ በመከራ የማይበገር፣ ተላቶቹን መቅበር የሚችል፣ ልዩ ስብዕናና ጽናት ያለው ሕዝብ በመሆኑ ሁሉንም ችግር ማለፍ እንደሚችል ከመግለጽ ውጪ ችግር የሚባል ነገር ሊገጥመው ቀርቶ በአጠገቡ ሊያልፍ እንደማይችል በተደጋጋሚ ይገልጻል።

ትህነግ ሰፊ ሃይል እንዳለውና በፈለገ ሰዓት የለቀቃቸውን ቦታዎች መልሶ የመያዝ አቅም እንዳለው አቶ ጌታቸው በተደጋጋሚ ሲናገሩ ነበር። እሳቸውም ብቻ ሳይሆኑ ለወረራ የተዘጋጀውን ሃይል የሚመሩትም ቢሆኑ ሃይላቸው አሁንም ድል እየተጎናጸፈና የሚደረግበትን ጥቃት ሙሉ በሙሉ እየመከተና ” ጠላት” የሚሉትን የኢትዮጵያ መከላከያ፣ የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እየደመሰሱ መሆናቸውን ነው የሚናገሩት። ስልታዊ ማፈግፈግ ሲያውጁም ሰማኒያ ሺህ የኢትዮጵያን መከላከያና ታጣቂ ሃይል መደምሰሳቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም። አሁን ላይ አቶ ጌታቸው እንደተለመደው አከታትለው መጻፍ በማቆማቸው አቋማቸውና ቁመናቸው ለጊዜው አልታወቀም። የድርጅቱ የዩቲዩብና የፊስ ቡክ ገጽ ግን ዛሬም ድል እያደረጉ እንደሆነ ነው የሚያስታውቁት።

ወደ ትግራይ ሙሉ ሃይላቸውን ይዘው በስልታዊ ጉዳይ መመለሳቸውን የሚያስታውቁት የትህነግ አመራሮች ” ወይ ድሉን ወይ ልጃችንን” የሚለው ጥያቄ ከረሃብና ችግር ጋር ተያያዞ ሊነሳ እንደሚችል ግን በዝግ ገምግመዋል። በዚህ ግምገማ መነሻቸው ነው ሁለት ሃሳብ ላይ የተጣበቁት ተብሏል። የቀድሞው የመንግስት ከፍተኛ መኮንና የአንበሳ ባንክ ከፍተኛ ባለድርሻ ጻድቃን ገብረትንሳኤ እና ዶክተር ደብረጽዮን በጻፉት ጽሁፍ አሜሪካም ሆነች ሌሎች ደጋፊዎቻቸው ከቃላት ውጪ ምንም ድጋፍ እንዳልሰጡዋቸው፣ በተለይ ጻድቃን የትህነግ ወራሪ ሰራዊት ሩጫና የዲፕሎማሲው ስራ ተጣጥሞ አለመሄዱ ከድሮን ድብደባ ጋር ተዳምሮ አዲስ አበባን ሳይዙ ወደ ትግራይ ያራገፉትን አራግፈው እንደተመለሱ መናገራቸው ስጋቱን አመልካች እንደሆነ ነው ታዛቢው ያስታወቁት።

የውጭ ወዳጅ ሚዲያዎችና አገራት ሳይቀሩ የትህነግ ወራሪ ሃይል የተሸነፈው በድሮን ጥቃት መሆኑንን ማጉላታቸው በውስጥ ሊነሳ የሚችለውን ተቃውሞ ከማርገብ አንጻርና በውጭ ያለውን ደጋፊ ከማረጋጋት ጋር ተያይዞ የተቀነባበረ መሆኑን ከሌላ ወገን የሆኑት አብዛኞች ሲተቹና ሲያጣጥሉ መክረማቸው ይታወሳል።

“የድሮን ጥቃት የሽንፈት መንስኤ ከሆነ የጉዳቱ መጠን እንጂ ጉዳት ስለመድረሱ ጥርጥር የለም” ሲሉ የሚከራከሩ ምንም ሆነ ምን በትግራይ ” ከድሉም ከልጆቻችንም አልሆንም” በሚል ተቃውሞ መነሳቱ አይቀሬ መሆኑንን በራሳቸው ትንተና ሲናገሩና ሲጽፉ ነበር የከረሙት። መንግስትም ይህቺኑ ቃል እየደጋገመ ነው።

የትህነግ ሰዎች ቀደም ሲል ያጣጣሏቸውን ኦብሳንጆን መቀሌ እየተበቁ መሆናቸውና ለእኚሁ አሸማጋይ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ እንደሚደረግ በተደጋጋሚ አሁን እየተገለጸ መሆኑ ምን አልባትም የርዋንዳና የደቡብ አፍሪካ አይነት ዕርቀ ሰላም ለማውረድ ለሚተጉት መልካም ዜና ቢሆንም ዕርቅ ከፍትህ ሊለይ ስለማይችልና ከፍትህ የተለይ እርቅ መንግስት እንደማይቀበል ማስታወቁ እንቅፋት ሊሆን እንደሚችል ስጋት እንዳለም ታውቋል።

ከኢትዮጵያ ወገንም ዋጋ መከፈሉን የሚያወሱ አገሪቱ ክፉኛ መጎዳቷን በመጥቀስ ሰላም የሚወርበትንና ሰላማዊ ዜጎች እርፍት እንዲያገኙ ቅድሚያ ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ የሚያሳስቡ እየብ እየበረከቱ ነው። ይህ እንደ አንጀት የሚሳብ ጦርነት አገሪቱ አመሽክ አድርጎ እየበላ በመሆኑ፣ ጦርነቱ ከጀረባው በርካታ እጆች ስላሉበት በወኔ ብቻ የሚታለፍ እንዳልሆነ በመረዳት አቶ የሺህ ዋስ እንዳሉት ልክ እንደ ጦር ሜዳው ጅግንነት ሰላም የሚያመጡ ጀግኖችም ሊነሱ እንደሚገባ የሚያሳቡ እየተነሱ ነው።

አሜሪካ ባስቸኳይ ሁሉን አካታች ውይይት፣ እንዲሁም የሰላም ድርድር እንዲጀመር እየወተወተችና ኢትዮጵያን በማዕቀብ ለማዛል ወገቧን አስራ መነሳቷ የአደባባይ ሚስጢር ነው። ዛሬም ዲያስፖራ እንኳን ደህና መጣችሁ በሚል በሰላም ክብረ በዓለ እየተደረገ ባለበት ሰዓት ” ለቃችሁ ውጡ” የሚል ማሳሰቢያ ማሰራጨቷ ለዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈራ ነገር እንደሌለና ዘመቻው ከንቱ እንደሆነ ለማሳየት ሽርጉዱ በተጀመረበት ቀን ” አገር ለቃችሁ ውጡ” የሚል ማሳሰቢያ ማሰራጨቷ መንግስትን ነክሳ መያዟን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

በሌላ ተመሳሳይ ዜና በአማራና ፋር ክልል በትህነግ ወራሪ ሃይሎችና አለቆቻቸው የተፈጸመው አስነዋሪ ተግባር በከፍተኛ ደረጃ በሚዲያ ሳይሸፋፈን መቅረቡ ከፍተኛ የፖለቲካ ውድቀት ላይ እንደጣላቸው በቁጭት ሲናገሩ መስማታቸውን ለማስተባበል ቢሞከርም አለመቻሉን፣ አሁን ካደራጇቸው የብሄር ቤረሰብ ስብስቦች ጋር በመሆን አዳዲስ ሚዲያዎችን የማደራጀት አሳብ እንዳላቸው መስማታቸውንም እኚሁ የዜና ምንጭ አመልክተዋል።


Exit mobile version