Site icon ETHIO12.COM

የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ

Members of Amhara Special Forces stand guard along a street in Humera town, Ethiopia July 1, 2021. Photo: Reuters.

ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ ማድረጉን የአማራ ክልል መንግሥት አስታወቀ።

የአማራ ክልል መንግሥት ክልሉ የገጠመው የሰላምና የፀጥታ ችግሮችን በአግባቡ ለመቅረፍ ያስችል ዘንድ በክልሉ ያሉ የፀጥታ መዋቅሩ ላይ ያሉ ጉድለቶችን እና ጥንካሬወችን በዝርዝር ግምገማ ሲያካሂድ ቆይቷል።

በመኾኑም ክልሉ የገጠመውን የኅልውና አደጋ በአግባቡ በመመከት የሕዝቡን የፀጥታ ስጋት ለመቀነስ የአመራር ምደባና ስምሪት ማስተካከያ አድርጓል።

በዚህም መሠረት ፦

1- የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳደር የፀጥታ አማካሪ

2- የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሜጀር ጀነራል መሠለ በለጠ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል ዋና አዛዥ ኾነው ተሹመዋል ሲል አማራ ክልል የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮን ጠቅሶ አሚኮ ዘግቧል።

Exit mobile version