ETHIO12.COM

ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ አንደኛ

የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከዓለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች።

ባሕር ዳር: መጋቢት 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያ ከዓለም አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ፆታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣት ችለዋል፡፡

ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሜሪካ እና ስዊዘርላንድ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2008 በተደረገው 12ኛው የቫሌንሽያ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 4 ወርቅ፣ 1 ብር፣ 1 ነሃስ ስታመጣ በ2018 በተካሄደው 17ኛው የበርሚንግሃም የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ደግሞ 4 ወርቅ፣ እና 1 የብር ሜዳሊያ ማምጣት መቻሏን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው

 

 

 

Exit mobile version