ደራርቱ የፖለቲካ መሪዎችን በእንባ ተማጸነች

ኮማንደር ደራርቱ ተማፅኖዋን ያሰማችው በቤልግሬድ የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ላይ ከዓለም አንደኛ ሆኖ ላጠናቀቀው የአትሌቶች እና አሰልጣኞች ቡድን በተዘጋጀ የምስጋና ፕሮግራም ላይ ነው።

” የሀገራችን ጉዳይ ሁላችንንም ያመናል ” ያለችው ደራርቱ ” የትግራይ እናቶች አባቶች ፤ እናቶቻችን አባቶቻችን ናቸው በእርግጠኝነት ደግሞ ነገ ሌላ ቀን ነው ኢትዮጵያ ታርቃ አንድ ሆና ትቆማለች ” ስትል ተናግራለች።

ኮማንደር ደራርቱ ፤ ከትግራይ ክልል የተገኙ ድንቅ አትሌቶችን ክብር ይገባችኃል ያለች ሲሆን ” በብዙ ፈተናዎች አልፈው በብዙ ተፅእኖ አልፈው የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ስላደረጉ ምስጋና አቅርባለች።

” በእርግጠኝነት ቤተሰቦቻችሁ የት እንዳሉ ታውቃላችሁ ” ያለችው ደራርቱ ” ግድ የላችሁም እንወዳችኃለን እናከብራችኃለን ፤ እንደልጆቻችን ነው አሁንም የምናያችሁ ስለሆነም ትግራይ ዛሬ ብቻዋን አይደለችም ከኢትዮጵያ ጋር ነች፤ ነገም ከኢትዮጵያ ጋር ትሆናለች ” ስትል ተናግራለች።

ኮማንደር ደራርቱ፤ የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልላዊ መንግስት መሪዎች ተጎድታችሁም ቢሆን ለኢትዮጵያ ህዝብ ብላችሁ ኢትዮጵያን አንድ አድርጓት ስትል በእንባ የተማፀነች ሲሆን ” ከእግዚአብሔር ጋር ትችላላችሁ። እናተ አንድ ካደረጋችሁ ኢትዮጵያ አንድ ትሆናለች። ” ብላለች።

ኮማንደር አትሌት ደራርቱ አሜሪካ ፤ በ ” H.R. 6600 ” ኢትዮጵያንም ሆነ ትግራይን ለመጥቀም ሳይሆን ለመበተን እንደሆነ ተናግራ መሪዎች ከተስማሙ የሚፀድቅበት ምክንያት ስለሌለ ለወደፊት ኢትዮጵያ ሲሉ እዲስማሙ ተማፅናለች።

ህዝቡም በመተባበር #ኢትዮጵያን አንድ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርባለች። ምንጭ – https://t.me/tikvahethiopia

You may also like...

Leave a Reply