Site icon ETHIO12.COM

ዐቃቤ ህግ 93 ተከሳሾች ላይ የምስክሮችን ቃል እያሰማ ነው

ዐቃቤ ህግ በቤሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከእኛ ውጭ ሌሎች ብሔሮችን እናጠፋለን በማለት ለ49 ሰዎች ሕይወት መጥፋት፡ ከባድ የንብርት ውድመትና ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት በሆኑ 93 ተከሳሾች ላይ የምስክሮችን ቃል እያሰማ ነው ።

የዐቃቤ ህግ የምስክሮች ቃል እየተሰማ ያለው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አሶሳና አካባቢው 1ኛ ተዘዋዋሪ ችሎት ነው ።

በመንግስት ላይ የሚደረግ ወንጀል ߹ የመሸሸግ߹ ለበላይ ሃላፊ አለመታዘዝ ߹ለጠላት እጅ መስጠት߹ በጦርነት ወቅት ያለአግባብ ሃብትን ማባከን߹ የአደጋ ምልክቶች ሲስተዋሉ ቀድሞ አለማሳወቅ ߹ከባድ የሰው ግድያና ከባድ የውንብድና ወንጀሎች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32 /1/ /ሀ/ እና /ለ/፣ 35፣ 38 /1/ እና 240 /3/ ፡/4/ ߹340߹298 /2/ ߹ 313 /ለ/፡/ሐ/߹539 /1/ሀ/߹308/2/߹306/4/߹27/1/߹አንቀፅ 671/2/ እና አንቀፅ 682/1/ ስር የተደነገገውን በመተላለፍቸው ነው ክስ የተመሰረተባቸው ።

በዚህ ወንጀል ላይ ወንጀሉ በተፈፀመበት ቦታ በመገኘት ከፖሊስ ጋር በመሆን ከወንጀል ምርመራው አንስቶ የምስክሮችን ቃል እያሰማ ያለው በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የተደራጁና ደንበር ተሸጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክቶሬት ጄኔራል ዐቃቤ ህግ ነው ።

ተከሳሾች ከሌሎች ለጊዜው ስማቸው ተለይቶ ካልታወቁና ካልተያዙ ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን ከጥር ወር 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 2013 ዓ.ም ድረስ በነበሩ የተለያዩ ቀናት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከማሽ ዞን ሰዳል እና ኦዳ ብልድግሉ ተብለው በሚጠሩ ወረዳዎች በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች የብልፅግና መንግስትን ማየት አንፈልግም፣ ይህ የብልፅግና መንግስት እኛን አይመራንም እኛ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ሆነን የስራ እድል አላገኘንም ስራ የሚሰሩት ሌላው ቀይ ማህበረሰብ ስለሆነ የጉሙዝ ብሄር ተወላጅ ለሆነ በሙሉ የጉህዴን ወታደሮች ነን፣ ለእናንተ ለጉምዝ ጭቁን ህዝብ ነው እየታገልን ያለነው በማለት፤ መሳሪያ ያለው በመሳሪያ፣ ገንዘብ ያለው ደግሞ ገንዘቡን ይርዳ የብልፅግና ደጋፊ እና አመራር እንዲሁም ሌላ ቀይ ቀለም ያላቸውን ብሄር ብሄረሰቦች እናጠፋለን፣ እንገድላለን፣ እንለቅማለን የሚል አላማ በመያዝ በአካባቢው በተለምዶ መጠሪያ ቀይ ተብለው የሚታወቁትን ኦሮሞ፣ አማራ፣ አገው፣ ሽናሻ እና የጉራጌ ማህበረሰብ አካባቢውን ለማያውቁት በርካታ ቁጥር ለነበራቸው የሽፍታ አባላት ከጉሙዝ ብሄር ተወላጆች ውጭ የሆኑትን ቤቶች ቀይ ፌስታል እንዲሁም የጉሙዝ ብሄር ተወላጆችን ቤት ጥቁር ፌስታል በማሰር እና ጥቃት የሚደርስባቸውን ቤት በመለየት ፣ የምንመራው እኛ ነን በማለት ለሶስት ቀናት ያክል ከተማውን ተቆጣጥረው ከቆዩ በኋላ መከላከያ ሰራዊት ሲገባ ውጊያ በመግጠም እንዲሁም በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን እና ገዳይ የሆኑ ስለታማ ነገሮችን በመያዝ ዝርፊያ እና አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ግድያ በመፈፀም በደረሰው ጥቃት በመሳተፍ በዚህ ምርመራ የተጎጅዎችን ስም ማረጋገጥ እስከተቻለው ድረስ ብቻ 21 የጉሙዝ ብሄር ተወላጆችን፣ በተለምዶ ቀይ ተብለው ከሚጠሩት ማህበረሰብ ኦሮሞ፣ አማራ፣ አገው፣ ሽናሻ እና የጉራጌ ተወላጆች መካከል 24 እንዲሁም 04 የልዩ ሀይል የፀጥታ አባላት አንድ በድምሩ የ49 ሠዎች ህይወት እንዲጠፋ፣ ቁጥራቸው ያልታወቀ ግለሰቦች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት እንዲደርስባቸው፣ ከ170,000,000 (አንድ መቶ ሰባ ሚልየን) ብር በላይ የሚገመት የመንግስት እና የግል ተቋማት ንብረቶች እንዲወድሙ እና እንዲጠፋ፣ ከ32 ሺ በላይ ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸው እንዲፈናቀሉ በማድረግ ተከሳሾች በፈፀሟቸው በዋና ወንጀል አድራጊነትና ተካፋይ በመሆን በመንግስት ላይ የሚደረግ ወንጀል ߹ የመሸሸግ߹ ለበላይ ሃላፊ አለመታዘዝ ߹ለጠላት እጅ መስጠት߹ በጦርነት ወቅት ያለአግባብ ሃብትን ማባከን߹ የአደጋ ምልክቶች ሲስተዋሉ ቀድሞ አለማሳወቅ ߹ከባድ የሰው ግድያና ከባድ የውንብድና ወንጀሎችን ፈፅመው ክስ እንደተመሰረተባቸው ይታወሳል ።

በዚህም መሰረት ዐቃቤ ህግ ካስመዘገባቸው 171 ምስክሮች ውስጥ እስካሁን በ3 ዙር 73 የምስክሮችን ቃል አሰምቷል ።

ከዛሬ መጋቢት 26 እሰከ መጋቢት 30/2014 ዓ.ም ደግሞ ቀሪ 98 ምስክሮችን ዛሬ ማሰማት ጀምሯል ።
አምስት የዐቃቤ ህግ ምሰክሮች በጠዋቱ ቀጠሮ ተገኝተው በእውነት ለመምሰከር ቃለ መሃላ በመፈፀም የምስክርነት ቃላቸው በመቅረፀ ድምፅ ሲመዘገብ ውሏል ።

ቀሪ የዐቃቤ ህግ መስክሮች ከነገ መጋቢት 27 እስከ 30 የሚቀጥል መሆኑም ታውቋል።
በተመሳሳይ ወንጀሎች ዐቃቤ ህግ በሌላ የክስ መዝገብ በደቡብ ክል ሸካ ዞን ߹ በቤሻንጉል ክልል ካማሺ ዞን እና ሌሎች አካባቢዎች አልባት ባገኙ መዝገቦች በርካታ ወንጀለኞች እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ማስቀጣቱ የሚታወስ ሲሆን ሌሎች ብዛት ያላቸው መዝገቦች ደግሞ በሂደት ላይ ያሉ መሆናቸውን ለማሳወቅ እንወዳለን ።

Exit mobile version