Site icon ETHIO12.COM

በኢድ የሶላት ስርዓት ላይ ረብሻ ተቀሰቀሰ፤ ንብረት ወድሟል

በዛሬው ዕለት በኢድ ሶላት ላይ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል። ቢቢሲ አማርኛ በስፍራው የነበሩ ” ነገሩኝ” ሲል ከአንድ ወገን ብቻ ባሰራጨው ዜና የጥይት ድምጽ ይሁን የአስላቃሽ እርግጠኛ እንዳልሆኑ የገለጹ ራሳቸውን ለማትረፍ ሽሽት መርጠዋል።

ቢቢሲ ያናገራቸው ክፍሎች ለምን ህንጻ በድጋይ ሲፈርስና የመንገድ ማሳመሪያ የአትክልት ማስቀመጫዎችና ንብረት ማውደም እንደተፈለገ አላስረዱም።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ባሰራጨው አጭር መግለጫ ” ሚያዝያ 24 ቀን 2014 ዓ/ም የኢድ ሶላት ከመሰገዱ በፊት በሰማዕታት ሀውልት አካባቢ ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ምዕመኑ አሁን ተረጋግቶ ወደ መጣበት እየተመለሰ ስለሆነ ህብረተሰቡ በመረጋጋት ራሱንና አካባቢውን እንዲጠብቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል በቀጣይ የረብሻውን መነሻና ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሌሎች ጉዳዮችን ለህዝብ ያሳውቃል” ብሏል።

የኢድ ሶላት ከመሰገዱ በፊት በቀይ ሽብር ሰማዕታት ሙዚየም አካባቢ “ጥቂት ግለሰቦች ባስነሱት ረብሻ በንብረት ላይ ጉዳት” መድረሱንና ሰፊ ጉዳት ሳይከተል ስርዓቱ መቋረጡን ያመለከተው ፖሊስ ዝርዝር መረጃ አላሰራጨም። ” ጥቂት” ያላቸውን ወገኖችም አላብራራም።

የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ያናጋራቸው እንዳሉት ” ምን እንደሚፈልግና ምን ዓላማ ለማስፈጸም እንዲህ ማድረግ እንደተፈለገ አለገባንም” ብለዋል። በሁኔታው ማዘናቸውን አመልክተው በየሰፈራቸውና በየአካባቢያቸው በጉዳዩ እንደሚመክሩ ጠቁመዋል።

አንዳንድ በማህበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ ምስሎችና የቪዲዮ ፊልሞች አስለቃሽ ጢስ ፖሊስ መጠቀሙን ፣ድንጋይ የያዙ ህንጻ ሲሰባበሩና ሲያወድሙ አሳይተዋል። ተንቀሳቃሽ ምስሎች በቀጥታ ወደ ፀጥታ ኃይሎችና ሕንጻዎች ላይ ድንጋይ ሲወረወር አሳይተዋል።

በጎንደር በቀብር ቦታ በተነሳ ግጭት ሳቢያ እየሰፋና መልኩን እየቀየረ የሄደው ይህ ረብሻ ከሁዋላው የሚያሾረው አካል እንዳለ እየተገለጸ ነው። መንግስት ከዓመት በፊት “ሁሉንም ችግር እናልፋለን፤ የሃይማኖት ረብሻው የመጨረሻ ካርዳቸው ነው። በጥበብ ለማለፍ ህዝብ ይዘጋጅ” ሲል ማስጠንቀቁ የሚታወስ ነው።

አብሮ የኖረን ሕዝብ ለማባላት ከዚህና ከዚያ ሆነው በማክረር ምዕመኑንን እየነዱ ያሉ አክራሪዎች ከሁሉም ሃይማኖት ሊለቀሙ እንደሚገባ፣ መንግስት የከረረና የማያዳግም እርምጃ እንዲወስድ ሕዝብ እያሳሰበ ይገኛል።

ሰሞኑን የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በርካታ ተጠርጣሪዎችን የያዙ ሲሆን ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

Exit mobile version