Site icon ETHIO12.COM

አህጉር አቋራጭ ሮኬት ሰርቼ የሀገሬን ወታደራዊ ኃይል አጠናክራለው – ተማሪ ሳሙኤል ዘካርያስ

 የETR S1KM ተብሎ የሚጠራ ሮኬት መስራት የቻለውን ታዳጊ ሳሙኤል ዘካሪያስ አህጉር አቋራጭ የሆነ ሮኬት ሰርቼ ሀገሬን በወታደራዊ ኃይል ጠንካራ አንድትሆን አደርጋታለው አለ፡፡

የ16 ዓመቱ ባለ ልዩ ተሰጥኦ ተማሪ ሳሙኤል ከዋልታ ጋር በነበረው ቆይታ ችግር ፈቺ የሆኑ የምርምርና የፈጠራ ሥራዎችን በመስራት በቴክኖሎጂው ዘርፍ ሀገር ከፍ እንድትል እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡

ከ6ኛ ክፍል ጀምሮ የፈጠራ ሥራዎች መስራት የጀመረው ተማሪ ሳሙኤል እስካሁ በትምህት፣ በጤና እና በግብርና ዘርፍ በርካታ የፈጠራ ሥራዎችን መስራቱንም ገልጿል፡፡

ኢትዮጵያ በወታደራዊ ኃይል ከሰለጠኑ ሀገራት ተገዳዳሪ እንድትሆን መስራት የሚችል ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው በርካታ ልጆች እንዳሏት የሚናገረው ተማሪ ሳሙኤል በፈጠራ ዘርፍ ለሚደረገው ሩጫ መንግሥት በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አስታውቋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር (ኢመደአ) በበኩሉ በሳይበር ደኅንነት እና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ታዳጊ ወጣት ኢትዮጵያውያንን የመደገፍና የማብቃት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአስተዳደሩ ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ግዛው (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ በዛሬው ታዳጊ ሳሙኤል ዘካሪያስን በመቀበል በአስተዳደሩ በሚገኘው የኢትዮ-ሳይበር ታለንት ማዕከል እንዲታቀፍና የፈጠራ ሥራዎቹን ወደተሻለ ደረጃ እንዲያደርስ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

በዙፋን አምባቸው – WALTA

Exit mobile version