Site icon ETHIO12.COM

ሀጂ ዑመር እድሪስ “ከስልጣን እንደተነሱ ተደርጎ የተወሰነው ውሳኔ በየትኛውም ተቋም ተፈጻሚነት የለውም” ተባለ!

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፤ ትናንት በሸራተን ሆቴል በተደረገ ስብሰባ ከሥልጣን መነሳታቸው በየትኛውም ተቋም ተፈፃሚነት እንደሌለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

ም/ቤቱ በዛሬ መግለጫው፤ ትናንትና ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ውሳኔዎች በሚል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተካሄደውን ስብሰባም ህገወጥ መሆኑን ገልጿል ፡፡

ህገ ወጥ የተባለው የሸራተኑ ስብሰባ ባካሄደው ምርጫ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ አብዱልከሪም ሼኽ በድረዲን የመጅሊሱ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጦ ነበር።

ከዚህ ባለፈም በስብሰባው ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና ምክትላቸው ጄይላን ከድር (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮችም ከቦታቸው እንዲነሱና የፈትዋ ምክር ቤት አመራር እንዲሆኑ ተወስኖ ነበር።

ውሳኔው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ዛሬ አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ/ም መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስብሰባውንም ሆነ የስብሰባውን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል፡፡ ዜናው የ [Alain] ነው

Exit mobile version