ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ፤ ትናንት በሸራተን ሆቴል በተደረገ ስብሰባ ከሥልጣን መነሳታቸው በየትኛውም ተቋም ተፈፃሚነት እንደሌለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
ም/ቤቱ በዛሬ መግለጫው፤ ትናንትና ግንቦት 18 ቀን 2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ ውሳኔዎች
በሚል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተካሄደውን ስብሰባም ህገወጥ መሆኑን ገልጿል ፡፡
ህገ ወጥ የተባለው የሸራተኑ ስብሰባ ባካሄደው ምርጫ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሀጂ ኢብራሒም ቱፋ የመጅሊሱ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የደቡብ ክልል እስልምና ጉዳዮች ም/ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ አብዱልከሪም ሼኽ በድረዲን የመጅሊሱ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጦ ነበር።
ከዚህ ባለፈም በስብሰባው ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ዑመር እድሪስ እና ምክትላቸው ጄይላን ከድር (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች የመጅሊሱ አመራሮችም ከቦታቸው እንዲነሱና የፈትዋ ምክር ቤት አመራር እንዲሆኑ ተወስኖ ነበር።
ውሳኔው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጽ ዛሬ አርብ ግንቦት 19 ቀን 2014 ዓ/ም መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስብሰባውንም ሆነ የስብሰባውን ውሳኔ ውድቅ አድርጓል፡፡ ዜናው የ [Alain] ነው