Site icon ETHIO12.COM

የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ለመግደል የሞከረው ከ41 ዓመት እስር በኋላ ተለቀቀ

ጆን ሂንክሌይ የተሰኘው ይህ ግለሰብ በሚቀጥለው ሳምንት ከእስር ይለቀቃል ተብሏል

ግለሰቡ ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገንን ነበር ከ41 ዓመታት በፊት ለመግደል የሞከረው

የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ለመግደል የሞከረው ግለሰብ ከ41 ዓመት እስር በኋላ ተለቀቀ፡፡

40ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሮናልድ ሬገን በፈረንጆቹ 1981 ላይ ጆን ሂንክሌይ በተሰኘ ግለሰብ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው ነበር፡፡

ፕሬዝዳንቱ ከተፈጸመባቸው የግድያ ሙከራ የተረፉ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመው ተጠርጣሪ ላለፉት 41 ዓመታት በእስር ላይ ነበር፡፡

በወቅቱ ሙከራውን ሲያደርግ ጤነኛ እንዳልነበር በመረጋገጡ ፍርድ ቤት ነጻ በሚል ከ41 ዓመታት በኋላ እንደሚለቀው አስታውቋል፡፡ ከሳምንት በኋላ ከእስር ቤት ይወጣልም ብሏል ኒዮርክ ፖስት፡፡

ግለሰብ አሁን ላይ ከአእምሮ ህመሙ ማገገሙ የተገለጸ ሲሆን በእስር ቤት ቆይታውም መልካም ባህሪ በማሳየቱ ምክንያት ከእስር ለመለቀቁ ዋነኛ ምክንያቶች ናቸው ተብሏል፡፡

ግለሰቡ አሁን ላይ ለማህበረሰቡ አስጊ ባህሪ እንደሌለው በህክምና ባለሙያዎች ማረጋገጫ እንደተሰጠበትም ተገልጿል፡፡

ሮናልድ ሬገን በወቅቱ ጆን ሂንክሌይ በተኮሰባቸው ጥይት ቆስለው የነበረ ቢሆንም ከደረሰባቸው ጉዳት ለማገገም ረጅም ጊዜ አልወሰደባቸውም፡፡ ጥቃቱ ሲፈጸም አብረው የነበሩት ጸሃፊያቸው ቲሞቲ ማካርቲ ግን የተወሰነ የሰውነት ክፍላቸው አልታዘዝ ብሏቸው ረጅም ጊዜያትን በህመም አሳልፈዋል፡፡

የግድያ ሙከራውን የፈጸመው ጆን ሂንክሌይ ከእስር ቤት ሆኖ በከፈተው የዩቲዩብ ቻናል ሙዚቃዎችን እና ሌሎች ስራዎችን በበይነ መረብ አማካኝነት ለተከታዮቹ በማድረስ ከፍተኛ ገቢን ያገኝ እንደነበር ተገልጿል፡፡

አል-ዐይን

Exit mobile version