Site icon ETHIO12.COM

አንድ ነገር ግልፅ ይሁንልን!

እነ አሜሪካ የአፍሪካን መሪ የሚጠሉት ለህዝባችን፣ ለጥቁር አፍሪካውያን አስበው፣ ተቆርቁረው አይደለም፣ ሆኖም አያውቅም። ፖትሪስ ሉሙንባን የገደሉት፣ ያስገደሉት ለኮንጎ ሕዝብ ብለው ተቆርቁረው አይደለም። የአፍሪካን ሕዝብ የጨረሱ አምባገነኖች በሞላ እነ ኢዲ አሚን፣ ቦካሳ፣ ሞቡቱ ወዘተ አሜሪካኖች Friendly dictators and our sons of bitches የሚሏቸው ናቸው።
በወለጋ ግምቢ ስለተፈፀመው ጭፍጨፋ አሜሪካ እንግሊዝ ተመድ ጭምር አቧራ እያጨሱ ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚጠሉት፣ ሊጥሉት የሚፈልጉት መሪ ስላለ ብቻ ነው። ሌላ ምክንያት የለውም። በሸኔ ለተጨፈጨፉት አዝነው አይደለም። እንደዚያ ዓይነት ተፈጥሮም የላቸውም እንደውም ኦነግ/ኦነግ ሸኔ ግድያውን እንዲፈፅም ከወያኔ ጋር ሆነው እጃቸው ይኖርበታል የሚል ወደ እውነት የተጠጋ ጠንካራ ጥርጣሬ አለኝ። ወያኔ በበደኖ አርባጉጉ ጉራፈርዳ ያን ሁሉ ሕዝብ ስትፈጅ ፕር መስፍንን ውሸት ነው እያሉ ሲያጣጥሉ፣ ሲሞግቱ የነበሩት እነ አሜሪካን ናቸው። እንግሊዝማ አገሬም እንዳይገቡ ብላ ፕር መስፍንን ቪዛ ሁሉ ከልክላቸዋለች። ሀያ ሰባት ዓመታት ሙሉ ስንታረድ ዝም ብለው ሲሸፋፍኑ የነበሩ USA & UK አሁን ደርሰው የኢትዮጵያ ሕዝብ ተቆርቋሪ ሆነው ቢቀርቡ ማን ያምነናል ብለው ነው? Collective memory is short ነው የሚባል ሳይኮሎጂ አላቸው። ሕዝብ ረስቶልናል ብለው ይሆናል። አንረሳም። ነፍሳቸውን ይማርና በፕር መስፍን እና በስዊስ መንግስት መካከል የነበረውን ጦርነት፣ ጠንካራ የቃላት ምልልስ መቼም አንረሳውም። ፕር ክብራችንን በገንዘብ አንለውጥም ብለው የስዊስ መንግስት ለኢሰመጉ ሰጥቶት የነበረውን አስር ሺህ ዶላር መልሰውላቸዋል። እነ አሜሪካ ለራሳቸው ጥቅም እንጂ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ብለው የሚያደርጉት ነገር የለም። ኖሮም አያውቅም። እኛ ግን የአሜሪካንን ጦርነት ኮንጎና ኮርያ ተዋግተናል። ትልቅ ጥፋት ነው ። አሁን ባለው World order
ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ ወይም International community እየተባባሉ እርስበርስ የሚሞካካሹት USA UK & their satellites EU World Bank IMF ናቸው። ይሄንን የአሜሪካና የእንግሊዝ World order የሚገዳደር ብራዚል ራሺያ ሕንድ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ BRICS ብለው ተደራጅተዋል። አሜሪካኖች የብራዚሏ ፕሬዜዳንት የነበረችውን በዚህ ቡድን በመግባቷ ተናደውባት ብዙ ተንኮል ሰርተዋት ከስልጣን ወርዳ ታስራም ነበር። ይሄ የአሜሪካ መር Old World Order አፍሪካ ውስጥ ታላላቅ መሪ ፈጠርኩ ብለው ያቅራሩበት ጊዜን ያስታውሰኛል። እኤአ በ1991 በአፍሪካ ወጣቶች ዳይናሚክ መሪዎች ፈጠርን ያሉት እነማንን ነበር? እነዚህ በእነ አሜሪካ ዳይናሚክ ተብለው ተሞካሽተው የነበሩት 1.መለስ ዜናዊ፣ 2._ኢሳያስ አፈወርቂ እና 3. የኡጋንዳው ሙሴቬኒ ነበሩ። ከሙሴቬኒ እንጀምር። ሙሴቬኒ እኤአ በ1986 ስልጣን ሲይዝ በአሜሪካ መንግስት የተወደሰበት በCNN BBC DW etc በቀን አስር ጊዜ እየተደጋገመ ሲቀርብለት፣ ሲወደስበት ሲነገርለት የነበረው ንግግር የሚከተለው ነበር።

” ማንም የአፍሪካ መሪ ከአስር ዓመት በላይ በስልጣን ላይ መቆየት የለበትም”
ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ

ሙሴቬኒ አሁንም ለ36ኛው ዓመት ስልጣን ላይ ነው። በቅርቡ በዓለ ንግሱን ያከብራል። ሌላው በእነ አሜሪካ የተወደሱት መሪ እኤአ ከ1991 ዓም ጀምሮ አሁንም ድረስ ስልጣን ላይ ያሉት ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። እነ አሜሪካ ከወዲ አፎም ጋር በወዳጅነት መዝለቅ አልቻሉም። ኢሳያስ ጥሩ ሎሌ አልሆነም። በተለይ NGO የሚባሉ የሲአይኤ ድርጅቶችን ጠራርጎ አባሮ ዘጋባቸው። ማን ቀረ? መለስ ዜናዊ። ይህ ሰው ሎሌነቱን ወደዱት። መለስ በአማራው ሕዝብ ላይ በደደቢት ማኒፌስቶው መሠረት እልቂት አወጀ። አሜሪካ እና ሎሌዎቿ ጆሮ ዳባ ልበስ አሉ። በወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሀመራ፣ ራያ በእነ በረከት፣ ጥንቅሹ፣ ሕላዊ በሚባሉ የትግራይ/ኤርትራ ተወላጆች አማካኝነት የብዐዴን መሪዎች ሆነው በርካታ ወልቃይቴዎች ተሰደዱ፣ በርካታ ሺዎች ተገደሉ። በ1984 ወያኔ ሕዝቡን አባራ አካባቢውን Depopulate አድርጋ ከጨረሰች በኋላ ትግሬዎችን አሰፈረች። አሁንም ድረስ የአሜሪካ መንግስት ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ ብሎ በትክክለኛ ስሙ አይጠራም። የአሜሪካ መሪዎች እና VOA በሰው አገር ጉዳይ ሳይጠሩ፣ ሳይጋበዙ በጉልበት ጣልቃ ገብተው አሁንም ምዕራብ ትግራይ ነው የሚሉት። ትግራይ ምዕራብ ምስራቅ የሚባል የውስጥ ክፍፍል የላትም፣ ኖሯትም አያውቅም
የኢትዮጵያ ሕዝብ ማወቅ ያለበት እነ አሜሪካ ኪሲንጀር ከኬምፕ ዴቪድ ስምምነት በኋላ ለአሜሪካ መንግስት ኢትዮጵያ መፍረስ አለባት ብሎ ባቀረበው ሀሳብ መሰረት ኢትዮጵያን የማፍረስ ዓላማ አላቸው። በመሆኑም
ወያኔ ከወደቀች በኋላ ጠሚ ዶር ዓቢይ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ስላልተስማማቸው ጠምደውታል። ለኢትዮጵያ ሕዝብ አስበው አይደለም። እንደውም ስሌታቸው ከዶር ዓቢይ በኋላ ኢትዮጵያ ማፍረስ ይቀለናል ብለውም ነው። በአሁን ወቅት ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ አወገዘ ምናምን እየተባለ ሲነገር እንሰማለን። ዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ የሚባለው ቡድን ውስጥ ግን የዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛዋ ወይም ምናልባት አንድ አምስተኛ ህዝብ ማለትም1.5 ቢልየን ሕዝብ ያላት China የለችበትም። 150 ሚልየን ሕዝብ ያላት Russia የለችበትም። 1.4 ቢልየን ሕዝብ ያላት India የለችበትም። ሕንድ እና ቻይና ብቻ 50% የዓለም ሕዝብ ገደማ ናቸው። 220 ሚልየን ሕዝብ ያላት Pakistan የለችበትም። North & South Korea, 1.4 ቢልየን ሕዝብ ያላት the entire Africa የለችበትም። vietnam፣ ላቲን አሜሪካ፣ etc የሉበትም።
ስለዚህ አሜሪካና ተመድ የወለጋን ግድያ አወገዙ ብላችሁ የምትፈነጥዙ ቆም ብላችሁ አስቡ።
አሜሪካ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ብላ የምትሰራው ነገር የለም። የአባይን ግድብ ለማኮላሸት በሁለት ወር ውስጥ ወደ አስራ አምስት የሚጠጉ ኢትዮጵያን የሚያወግዙ፣ ማዕቀብ የሚጥሉ ውሳኔዎች እያረቀቀች ለፀጥታው ምክር ቤት አቅርባ በወዳጆቻችን በራሺያ እና ቻይና ነው የከሸፈው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

በጓንጉል ተሻገር

Exit mobile version