ETHIO12.COM

በአፋር የተደበቁ 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ከጋላፊ እስከ ሰርዶ በየመንገዱ ዳር ተደብቆ የቆዩት 15 ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በተጨማሪም አንድ ቦቴ ጫካ ውስጥ ነዳጅ ሲቀዳ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡

ዘመቻ ከተጀመረ ጌዜ ጀምሮ በየቦታው ተደብቀው የቆዩ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች መንቀሳቀስ መጀመራቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም ባለፉት ሦስት ቀናት በነዳጅ እጥረት ምክንያት ተዘግቶ የነበሩ የሰመራ ነዳጅ ማደያዎች ሥራ ጀምረዋል ሲል የአፋር መገናኛ ብዙኃን ዘግቧል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

Exit mobile version