የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከህግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ ስምንት የነዳጅ ድርጅቶች ቦቴዎችን መውረሱን አስታውቋል።

እነዚህን ቦቴዎች በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ በመውረስ የጫኑትን ነዳጅ በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቋል።

የንግድ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ይህንን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፤ ስምንት የነዳጅ ቦቴዎች ተደብቀው የተያዙት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ትብብር ነው።

ህግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ድርጅቶች ላይ እርምጃው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው ገልፀዋል።

Via ENA

Leave a Reply