Site icon ETHIO12.COM

አየር ሃይል ለትህነግ መሳሪያ ጭኖ የአየር ክልል ለመጣስ የሞከረ አውሮፕላን አወደመ

U.S. Air Force F-15E Strike Eagle aircraft from the 335th Fighter Squadron drop 2,000-pound joint direct attack munitions on a cave in eastern Afghanistan Nov. 26, 2009. The 335th is deployed to Bagram Airfield, Afghanistan, from Seymour Johnson Air Force Base, N.C. (DoD photo by Staff Sgt. Michael B. Keller, U.S. Air Force/Released)

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል

የኢትዮጵያን መዳከም የሚፈልጉና ለዚሁም ለዘመናት የሚንቀሳቀሱ ህወሃትን በመደገፍ ላይ የሚገኙ ታሪካዊ ጠላቶች ንብረት እንደሆነ የሚታመን አውሮፕላን ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ጭኖ በሱዳን አልፎ የአየር ክልላችንን ጥሶ ሲገባ በጀግናው አየር ሃይል ተመትቶ ወድቋል።

ሠራዊቱ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ዝግጁ መሆኑም ተገልጿል።

በሀገር መከላከያ ሠራዊት የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊ ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ላለፉት በርካታ ወራት ከፍተኛ ወታደራዊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው አሸባሪው ህወሃት ካለፉት ሁለት ሳምንታት ጀምሮ ኃይሉን ለውጊያ ሲያስጠጋ ነበር።

በየጊዜውም ተኩስ እየከፈተ የሀገር መከላከያን ሲተነኩስ መቆየቱንም ነው ያነሱት።

ቡድኑ መንግስት የዘረጋውን የሰላም አማራጭ ከቁብ ሳይቆጥርና የሰላም ሂደቱ ቴክኒካሊ ፈርሷል ብሎ መግለጫ ባወጣ ማግስት ነሐሴ 17 ቀን 2014 ዓ.ም ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በቆቦ ግራና ቀኝ ባሉ አካባቢዎች፣ በዞብል ተራራ፣ በቢሶበርና በወትወት ውጊያ መክፈቱን ገልጸዋል።

በዚህም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረሱን ጠቅሰው፤ የሽብር ቡድኑ እየላከ ያለው ጀሌ በሀገር መከላከያ ሠራዊትና በጸጥታ ሃይልች እየተለበለበ ነው ብለዋል።

ሜጀር ጀኔራሉ አክለውም በሱዳን አድርጎ የአየር ክልላችንን ጥሶ በሁመራ ሰሜናዊ ክፍል በኩል ወደ ትግራይ ሊያልፍ የነበረና ለሽብር ቡድኑ የጦር መሳሪያ ሊያቀበል የነበረ አውሮፕላንም በጀግናው አየር ሃይል ሌሊት አራት ሰዓት ላይ ተመትቶ መውደቁን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስደፈር የሽብር ቡድኑን እየጋለቡ ያሉ ሃይሎች ቢኖሩም የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለማስክበር በተጠንቀቅ ላይ ምሆናቸውን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም የሽብር ቡድን ሀገር የማፍረስ ህልሙን ትቶ ወደ ሰላማዊ መፍትሔ ካልመጣ እስከመጨረሻው ርምጃ ለመውሰዱ ሙሉ ዝግጅተ መደረጉን ጠቅሰዋል
አሁን የመከላከል ርምጃ እየተወሰደ ሲሆን በቀጣይም የማጥቃት ርምጃዎች እንደሚኖሩ ነው የጠቀሱት።

(ኢዜአ)

Exit mobile version