Site icon ETHIO12.COM

የቡና ገለባ ከተበላሸ ለውዝ ጋር ቀላቅሎ የምግብ ዘይት በሚያመርት ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደ

በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ቀጨኔ ልዩ ቦታው ሁለገብ አካባቢ የቡና ገለባ ከሻገተ ለውዝ ጋር በመቀላቀል የምግብ ዘይት በመጭመቅ ሲያመርት በተገኘ ተቋም ላይ እርምጃ ተወሰደ፡፡

የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ተስፋዬ ኤልያስ እንዳሉት ዘይት ማምረቻው የጤና ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሌለው፣ ለግብዓትነት የሚጠቀምባቸው ምርቶች ጥራታቸውና ደህንነታቸው የተጠበቀ አለመሆኑ፣ የሀይጅንና ሳኒቴሽን ጤና አጠባበቅ መስፈርቶችን አለማሟላቱና የቡና ገለባ ከተበላሸ ለውዝ ጋር በመቀላቀል የምግብ ዘይት ሲያመርት በመገኘቱ ተቋሙ ላይ ህጋዊ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል፡፡

ተቋሙ የተጠቀመባቸው ጥሬ እቃዎች የሻገቱ የቡና ገለባና ለውዝ በመጠቀም የሚመርት መሆኑን መረጋገጡን አውስተው ድርጅቱ ላይ የተያዙት ባዕድ ግብዓቶች በአግባቡ እንደሚወገዱና በጉዳዩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢውን ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ከተማ ምግብ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን

Exit mobile version