Site icon ETHIO12.COM

ዳይሬክተሩ ቴድሮስ – ከክህደት እስከ ውርደት

-the Tedros betrayal vs “Betrayal of the West”

By – የዓባይልጅ

ኢስሌማን አባይ

የአለም ፀረ-ጤና ዳይሬክተር በማለት በርካቶች ይፅፋሉ፤ ስያሜው አልተጋነነም ባይ ነኝ። ከህዋሃታዊ ውግንናው ባለፈ ዋነኛ ኃላፊነቱን ደጋግሞ በመጣስ ብዙ ወንጀል በግላጭ ፈፅሟል።

ጦርነት በጤና ተቋማትና የህክምና ባለሙያዎች የሚያደርሰው ጥቃት አሳሳቢነት ተከትሎ አለም አቀፍ ተቋማት አንድ የተቀናጀ ስርአት ለመዘርጋት ግድ ብሏል። በዚህም በዓለም ጤና ድርጅት ጉባኤ በተረቀቀው “WHA65.20″ መሰረት፤ የ”WHO” ዳይሬክተር ጀነራል በጤና ተቋማትና ባለሙያዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ተከታትሎ የሚመዘገብበትን አሰራር በበላይነትና በኃላፊነት ማስተግበር አለበት። በዓለም ዙሪያ በጤና ተቋማት የሚደርሱ ጥቃቶችን መመዝገብ የሚያስችል በ “UN” ዕውቅና የተሰጠው መተግበሪያ ስርዓት እንዲከፈት ተደረገ። ይኸውም Surveillance system for attacks on health care – SSA ተብሎ
2017 ላይ በይፋ አገልግሎት የጀመረ ነው። ነመተግበሪያው ፋይዳ ጥቃቶችን ከመመዝገብና ከመልሶ ማቋቋም የሚሻገር እንዲሆን በማሰብ ነው።
በተለይም በጤና ተቋማት ላይ ጥቃት አድራሾችን በሰብአዊ ወንጀል ለመጠየቅ እንደ ዋነኛ መነሻ ያገለግል ዘንድ ነው።

ይህ ሃላፊነት መጣስ ከባድ ወንጀል ቢሆንም የምእራባዊያንን ፍላጎት ያገናዘበ በመሆኑ ቴድሮስን ባላዬ አልፈውታል።
በጤና ተቋማት የሚደርሱ ጥቃቶችን ለመከታተል WHO በዬሀገራቱ ባሉት ቢሮዎች በኩል በሀገራቱ ከሚገኙ አጋሮች እና በይፋ የሚደርሱትን ጥቆማዎችን በመረጃ ምንጭነት ተጠቅሞ በ SSA ዳሽቦርድ በኩል በይፋ ያስቀምጣል። የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አካላትና ሌሎች ድርጅቶች በጤና አጠባበቅ ላይ የሚደርሰውን መጠነ ጥቃት ለመረዳት፣ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም የወንጀለኞችን ተጠያቂነትን ለማመቻቸት ይህ የዓለም ጤና ድርጅት በኩል የተከፈተው SSA የሚያስቀምጠው መረጃን ይጠቀማሉ። በርካታ የሰብአዊ፣ ህጋዊ እና የጤና ተሟጋቾች በጤና ክብካቤ ላይ የሚደርሱ ጥቃት አድራሾችን ተጠያቂ ለማድረግ ቅድመ ሁኔታ ነው ሲሉ ደጋግመው ጥሪ አቅርበዋል።
የዓለም ጤና ድርጅት SSA በዬሀገራቱ ደረጃ ለማስተሳሰር ቅድሚያ መስጠት አለበት። በዚህም በፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊና ፋይናንስ ዘርፎች ድጋፍና ትብብር እያደረገ መስራት አለበት። በዚህም ጥቃቶቹ የተፈፀመባቸው የጦር መሳሪያ አይነቶች፣ ጥቃቶቹ የተሰነዘሩባቸውን ቦታዎችና የጥቃት አይነቶችን በተመለከተ የተሟላ መረጃ እንዲሰበስብ የሚረዱ ይሆናሉ።
ተጠያቂነትንም ለማስፈን ወሳኝ ግብአት ይሆናል።
SSA መረጃዎቹን ይበልጥ ለማጠናከር ከሌሎች ፕላትፎርሞች ለምሳሌ Insecurity Insight/Heal Safeguarding Health in Conflict Coalition Database) በኩል ተጨማሪ መረጃዎችና ትክክለኝነቱንም እንዲገመግም ያስችለዋል።

WHO ከአለም ዙሪያ የደረሱ የጤና ተቋማት ላይ የደረሰ ጥቃት በ 2021 እኤአ 695 ነው ሲል በተጠቀሰው SSA ነው፤ በአመቱ ከፍተኛው ጥቃት የደረሰው በማይናማር 260፣ በእፍጋኒስታን 42 እና በማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ 81 በዋናነት ይጠቀሳል። በዚሁ አመት ህወሃት በአምስት ወራት የአፋርና አማራ ወረራው ያደረሰው የጤና መሰረተ ልማት ውድመት በብዙ እጥፍ የከፋ ሆኖ ነው የተገኘው።

ህወሃት ወዳደረሰው የጤና ተቋማት ውድመት ስንመጣ የጤና ምኒስትሯ ዶ/ር ሊያ እስካሁን ባለ መረጃ ከ 3 ሺ በላይ ጤና ተቋማት በህወሃት ውድመት ደርሶባቸዋል (Dec 13, 2021 ላይ በሰጡት መግለጫ)።
⏯በአማራ
-40 ሆስፒታሎች
453 ጤና ጣቢያዎች
1,850 ጤና ኬላዎች
4 የደም ባንኮች
1 የኦክስጅን ማምረቻ
የደሴ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ 80 አመታት በፊት የተገነባ ሲሆን 10 ሚሊዮን የሚሆኑ ከአፋር ከአማራና ትግራይ አካባቢዎች ለሚመጡ ዜጎች አገልግሎት እየሰጠ ነበር፤ በህወሃት ወረራም የተዘረፈና የወደመ ሆኗል።
▪️የፅኑ ታማሚዎች ማከሚያ ICU የሚያገለግሉ በሚሊዮኖች ወጪ የተገዙ ቬንትሌተሮ ተዘርፈዋል።
▪️ ቬንትሌተሮቹ በቁጥር 7 የነበሩ ሲሆን ሁሉም በህወሃት ተዘርፈዋል
▪️የሆስፒታሉ ሠጋዝን በሙሉ ተዘርፏል፤ ይህን ተከትሎም ደሴ ሆስፒታል ቀዶ ጥገና ማድረግ የማይችልበት ደረጃ እንዲደርስ ያስገደደ ሆኗል
▪️ደሴ ሆስፒታል ከመዘረፉ በፊት በነበረው አመት 450,000 ህሙማንን ተቀብሎ ማስተናገዱ ተገልጿል። ከዚህ ውስጥ 100000 ዎቹ ከህመም ውጪ ክትትል ያደረጉ፤ 50 ሺዎች ደግሞ የድንገተኛ ታካሚዎች ነበሩ።
▪️82 መንግስታዊ ጤና ቢሮዎች
▪️40 ሆስፒታሎች
▪️453 ጤና ጣቢያዎች
▪️1,850 ጤና ኬላዎች
▪️4 የደም ባንኮች
▪️ 1 የኦክስጂን ማምረቻ
▪️የኢትዮጵያ ፋርማሲዩቲካል አቅርቦት ኤጄንሲ፣ ደሴ ቅርንጫፍ (ለ27 ሆስፒታሎችና 303 ጤና ጣቢያዎች አቅርቦት የሚያሟላ) በሙሉ ተዘርፏል።
በተጨማሪም ህወሓት ወርሯቸው በነበሩ የአማራ ክልል ዞኖች የወደሙ የጤና ተቋማት ከ 1ሺ 107 መሆናቸውን ባሳለፍነው ሳምንት የገለፁት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መልካሙ አብቴ ናቸው። በዚህም በህወኃት ወረራ 13.5 ቢሊዮን ብር የጤና መሰረተ ልማት የወደመ ሲሆን ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ ሆስፒታሎችና የጤና ጽ/ቤቶች በከፍተኛ ደረጃ የጉዳቱ ሰለባ ናቸው ብለዋል(ባሳለፍነው ሳምንት በተሰጠ መግለጫ)
▪️በአፋር ክልልም 60 ጤና ማእከሎችን አውድሟል።

በስድስት ሀገሮች በተከሰቱ ጦርነቶች በ30 አመታት ምን ያህል ጤና ተቋማት ጥቃት እንደደረሰባቸው የመረመረ ጥናት ተደርጎ ነበር።
በጥናቱ የተዳሰሱ ሀገራት ዬመን (ከ2015-አሁን)፣ ሶሪያ (ከ2011-አሁን)፣ ኢራቅ (2003–2011)፣ ቼቺኒያ (1999–2000)፣ ኮሶቮ (1998–1999) እና ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና (1992–1995) ናቸው።
የጥናቱ ባለድርሻ ተቋማት Doctors Without Borders፣ Monitoring Violence against Health Care፣ PHR Physicians for Human Rights ናቸው።

በግምቦት 2018 ይፋ የተደረገው የጥናቱ ውጤት ተከታዮቹን ቁጥሮች አስቀምጧል።
▪️ሶሪያ (በ 7 ዓመታት) 315 ጤና ተቋማት
▪️ዬመን 93
▪️ኢራቅ 12
▪️ቼቺኒያ 24
▪️ኮሶቮ 100
▪️ቦስኒያ 21
▪️በWHO የቱርክ ጤና ክላስተር በኋላ ላይ ጤና ተቋማት ላይ የሚደረጉ ጥቃቶችን በሚከታተለው Monitoring Violence against Health Care MVH, የ135 ተጨማሪ ተቋማት ጥቃቶችን ሪፖርት አርጓል።
በድምሩ 700 ጤና ተቋማት ላይ ጥቃት ደርሷል።
ይህ በ 6 ሀገሮች የ 30 አመት ጦርነት ውስጥ የደረሰ የጤና ተቋማት ጥቃት ሲሆን አለማቀፍ ጥናቱ ጥቃቶችንና በህክምና ባለሙያዎች ላይ የደረሰው ጥቃት ጨምሮ ያካተተ ሲሆን በህወሃት የተፈፀመው በውድመት ደረጃ የተመዘገበ ነው።
በኮቪድ ጉዳይ ዋሽንግተን backlog ቴድሮስ ራሱ ያውቀዋል። ነገር ግን የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም በሚል ቀጥሎበታል። ውርደቱ ከህወሃት ፍፃሜ ጋር እንዲሆን ወስኗል። ከህወሃት በኋላ የምእራባዊያን ክህደት ወቅቱን ጠብቆ ይመጣለታል። ምእራቦቹ የመከላከያችንን ክብር የረገጡት ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በመካዳቸው ነው። ክህደታቸውን ተገን አድርጎ ነው ቴድሮስ ኢትዮጵያን የካደው። ክህደት ደግሞ በምእራቦቹ ይብሳል። “Betrayal of the West” ብላችሁ ጎግል አድርጉ። ጥንት ጀምሮ የሚታወቁበት ነው። አይደለም አፍሪካን አውሮፓን የሸመጠጡበት የክህደት ታሪካዊ ባህላቸው ነው። የህዋሃት ደጋፊዎች ጫና ኢትዮጵያ ያልመረጠችውን እንድትፈርምላቸው ከማመቻቸት ያለፈ ሚና አይኖረውም። ህወሃት እንደ ቡድን ምናልባትም እዚያ የሚያደርስ እድሜ ያለው አይመስልም።
ኢትዮጵያን የከዳ እሱ ግን እጅጉን የተከዳ ይሆናል!

#የዓባይልጅ ✍️ Esleman Abay

ዋቢዎችና ዝርዝር መረጃ ለመመልከት👇
https://eslemanabay.com/?p=2747
Attacks who..
https://extranet.who.int/ssa/Index.aspx
https://www.facebook.com/AmharaMediaCorporation/videos/3171705183065399/
https://www.facebook.com/WolloInsider/videos/4280310295406793/
https://www.facebook.com/AmharaMediaCorporation/videos/3171705183065399/https://fb.watch/fD9WhSgVmK/https://www.facebook.com/WolloInsider/videos/4280310295406793/
https://eslemanabay.com/?p=2747

Exit mobile version