Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮ- ኬኒያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዛሬ በይፋ የኤሌክትሪክ ሽያጭ ተጀምሯል

– በዓመት እስከ አንድ መቶ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማስገባት አቅም ያለው ሲሆን ከኬንያ አሌፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኤላክትክ የማስተላለፍ አቅም አለው፡፡

የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር እና የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያ ዛሬ በይፋ የኤላክትሪክ ሽያጭ ጀምሯል፡፡

በማስተላለፊያ መስመሩ ላይ ኃይል የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ ከጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ሲከናወን ቆይቷል፡፡

ዛሬ በይፋ ኃይል ማስተላለፍ የጀመረው የኢትዮ – ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር በዓመት እስከ አንድ መቶ ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ማስገባት አቅም ያለው ሲሆን ከኬንያ አሌፎ ከታንዛኒያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ላሉት ሀገራት እስከ ሁለት ሺህ ሜጋ ዋት ኤላክትክ የማስተላለፍ አቅም አለው፡፡

የኢትዮ- ኬንያ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርና ኮንቨርተር ጣቢያ ፕሮጀክት ለአማካሪ ድርጅቱ፣ ለካሳ ክፍያና የተሰረቁ መሰረተ ሌማቶችን ለመተካት የወጣውን ወጪ ጨምሮ ወደ አምስት መቶ ሚሊየን የአሜሪካ ዶሊር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

ከዚህ ውስጥ 214 ነጥብ 5 ሚሉዮን ዶላሩ ለኮንቨርተር ስቴሽኑና ለግራውንድ ኤላክትሮድ መስመር የግንባታ ሥራ እንዲሁም 120 ሚሉዮን ዶላሩ ደግሞ ለማስተላለፊያ መስመሩ የዋለ ነው፡፡

የኢትዮ- ኬኒያ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራ “CET” በተሰኘ የቻይና ኩባንያ የተከናወነ ሲሆን የኮንቨርተር ማከፋፈያ ጣቢያውና የግራውንድ ኤላክትሮድ መስመሩ ደግሞ ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ ተከናውኗል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የተዘረጋው የማስተላለፊያ መስመር እና የፕሮቴክሽንና የዳታ ኮሙዩኒኬሽን መስመር (ኦፕቲካሌ ግራውንድ ፋይበር) 440 ኪል ሜትር ርዝመት ያለው ሲሆን 994 የከፍተኛ ኃይሌ ተሸካሚ የብረት ታወሮች አሉት።

ኢትዮጵያ የምታስተላልፈው ኃይል ያልተቆራረጠና አስተማማኝ እንዲሆን የሚያግዙ ተግባራትን ያጠናቀቀች ሲሆን በኬንያ በኩል ተመሳሳይ ሥራዎች ተሰርተው በቅርቡ ወደተግባር እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡

የማስተላለፊያ መስመሩ ከደቡብ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የወላይታ፣ ጋሞ እና ኮንሶ ዞን እንዲሁም ከኦሮሚያ ብሔራዊ ክሌሊዊ መንግስት የቦረና ዞን አቋርጦ ነው ወደ ኬንያ ኃይል የሚያስተላልፈው።

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ከሱዳን እና ከጅቡቲ ጋር የኃይሌ ሽያጭ እያካሔደች ሲሆን ከሶማሌላንድ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የኤላክትሪክ ኃይሌ ሽያጭ ለማከናወን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርማለች።
ባለፈው ዓመት ለሱዳን እና ለጅቡቲ ኤክስፖርት ከተደረገው የኤላክትሪክ ኃይሌ 95 ነጥብ 4 ሚሉየን የአሜሪካን ዶሊር ገቢ ተገኝቷል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

Exit mobile version