Site icon ETHIO12.COM

እስክንድር ነጋ ተፈታ፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ብሏል

“አገር ውስጥ ፖለቲካ ለመስራት አልቻልኩም” በሚል መንግስት እንዳዋከበው ገልጾ ራሱን ሸሽጎ የነበረው እስክንድ ነጋ ባህርዳር ከተማ 9ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከቆየ በሁዋላ መፈታቱ ታውቋል።

እስክንድር ምስራቅ ጎጃም ቡሬ መያዙን ለተሰበሰቡ ሰዎች ሲናገር የሚያሳይ ቪድዮ ላይ ” ትግሉ ይቀጥላል” ሲል ክንዱን ጨብጦ ተሰብስበው ሲያዳምጡት ለነበሩት መልዕክት አስተላልፏል። “ይቀጥላል” ያለው ትግል ግን ምን መልክ እንዳለው በቪዲዮው አልተገለጸም።

እስክክንድ ነጋ በነጠላ ጫማና በቁምጣ ሆኖ በተወሰኑ ሰዎች መካከል ቆሞ ሲናገር ቡሬ ምን ሊያደርግ እንደሄደ፣ ምን ሲሰራ እንደቆየና አካባቢውን ለምን እንደመረጠው ይፋ ላደረገም። ፖሊስ ሲይዘው “የት ነበርክ፣ ራስህን ለምን ሰውረህ ቆየህ” የሚል ጥያቄ መጠየቁን ከሱ ጋር ግንኙነት ያላቸው እንደተናገሩ ገልጾ ዘመዴ የሚባለው የመረጃ ቲቪ ተንታኝ በቴሌግራም ገጹ አስፍሯል።

ሃብታሙ አያሌው የሚባለው የ360 አባል ደግሞ “አነሳሱን ተመልከቱ ጽናቱን ያሳያል የእጅ ምልክቱ በራሱ በእስክንድር ውስጥ ያለውን በራስ መተማመን እና ብርታት የሚያሳይ ነው:: ኔልሰን ማንዴላ በእስር በነበረ ጊዜ የተነሳውን ፎቶ የሚስተካከል የፅናት ማሳያ ነው” ሲል እስክንድር ሲያዝ የተሰራጨውን ምስል አድንቋል።

ቡሬ ከጎጃም ወደ ወለጋ የሚወስድና አሁን ላይ መከላከያ እርምጃ ወስዶ ያጸዳው አካባቢ እንደሆነ ይታወቃል።

Exit mobile version