እስክንድር ቡሬ ከተሸሸገበት በፓሊስ ተያዘ

ለወራት ድምጹንና አድራሻውን አጥፍቶ የከረመው እስክንድር ነጋ ቡሬ ከተማ መያዙ ታውቋል። አቶ እስክንድር “በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ” ሲሉ ከአሜሪካ ሲመለሱ ለፓርቲያቸው ደብዳቤ ጽፈው መሰወራቸው ይታወሳል።

“ለወራት ከሕዝብ ዕይታ ተሰውሮ የነበረው አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም የባልደራስ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር ሆኖ ያገለገለው እስክንድር ነጋ በጎጃም ክፍለ ሃገር በቡሬ ከተማ ተያዘ” በሚል ወዳጆቹ በተለያዩ የክብር ስሞች ጠርተው ዜናውን አራብተዋል።

ከእስክንድር ቡሬ ከተማ መያዝ ጋር ተያይዞ በኦፊሳል የተሰጠ ምንም አይነት መረጃ የለም። እስክንድር ሰውነቱ ላይ መጎሳቆሉን የተሰራጩት ፎቶዎች ያሳያሉ። አብረውት በቁጥጥር ስር የዋሉት ሁለት ሰዎች ማንነትና ግንኙነታቸውን አመልክቶ እስካሁን በይፋ የተገለጸ ነገር እየለም።

ፖሊስ ቁጥጥር ስር አውሎ ወደ ባህር ዳር ከወሰደው በሁዋላ ወደ አዲስ አበባ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መተላለፉም ታውቋል። “ሰበር የእስር ዜና” በሚል ሙክታሮቪቺ በቴሌግራም ገጹ “…ከእስክንድር ጋር በቅርብ እንደሚገናኙ መረጃ እንዳለው የማውቀው ጋዜጠኛ ጌጥዬ ያለውም ይህንኑ አረጋግጦልኛል” ዘመድኩንን ጠቅሶ ጽፏል። በጽሁፉ ማብቂያ “…እኛ ግን በመርሀ ግብራችን መሠረት ውሎአችንን እንቀጥላለን” ሲል ዘመድኩን ማናገሩን አስፍሯል። መርሃ ግብር የተባለው ጉዳይ ግን አልተብራራም።

እስክንድር ነጋ “መንግስት ጫና እያደረሰብኝ ነው” በማለት ከሚመራው ድርጅት ጋር መቀጠል እንደማይችል ገልጽ ባሰራጨው ጽሁፍ ወዴትና ለምን ራሱን ለመሸሸግ እንዳሰበ ይፋ አላደረም። በደፈናው በፓርቲው አመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ከአሜሪካ መልስ አስታውታውቆ የነበረው እስክንድር ፖሊስ ሲይዘውም ሆነ ከያዘው በሁዋላ ህጋዊ ከሆነ አካል ይፋዊ መግለጫ አልተሰጠም።

የባልሰዳስ ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ እስክንድር በእጅ ጽሁፋቸው መግለጫ አዘጋጅተው በፌስቡክ አሰራጭተው ራሳቸውን ለጊዜው ባልገለጹበት ቦታ መሸሸጋሸው ሲገለጽ ወዲያውኑ በአዎንታዊና አሉታዊ መልኩ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ነበር።

በመግለጫው አቶ እስክንድር “ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ” ሲያደርጉ እንደቆዩ እና አሁን ያለው ጫና ግን በፖለቲካ እንደከበዳቸው ገልጸዋል። 

አቶ እስክንድር “ጨቋኝ” ነው ሲሉ በከሰሱት መንግስት ምክንያት “በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ” ብለዋል።

See also  ሶስተኛው የህዳሴ ግድብ ሙሌት ተጀመረ

እስክንድር ነጋ “ካሉበት ለፓርቲው ፅፈውታል” በተባለው ደብዳቤ ሌላ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ አላሰፈሩም።  ይልቁኑም ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣ አባላትና አመራሮች እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት አምሃ ዳኘው ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበው ነበር።

መንግስት አድርሶብኛል ያሉትን ጫና ሳያብራሩ በአጭር የፌስቡክ ጽሁፍ ድምጻቸውን ያጠፉት አቶ እስክንድር፣ እስር ላይ ይቆዩ አይቆዩ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም።

እስክንድር ሙሉ በሙሉ የፓርቲ እንቅስቃሴ ውስጥ አስገብቶ የፖለቲካ ድርጅት መሪ ከሆነ በሁዋላ አንድ የምርጫ ዘመን ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ተወዳድሮ መሸነፉ ይታወሳል።

Leave a Reply