ETHIO12.COM

የበታችነትና የበላይነት ስቃይ “እኩል የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው”መባሉ ጫጫታ አስነሳ?

ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በግልጽ አላፊነት የማይወሰድበትና ባለቤቱ ግልጽ ወጥቶ የማይመራው መተራመስ ህዝብን ሰላም ነስቷል። የኢኮኖሚ አሻጥርና ደባ ህዝብን እያዛሉት ነው። ከዚህ በላይ ደግሞ ሁሉም ጉዳይ ሕዝብ እንዲበሳጭና ስሜት ውስጥ እንዲገባ በሚያደርግ መልኩ በሚዲያዎች በቅብብል መረጨቱ ምን እየተፈለገ እንደሆነ ግልጽ አይደለም። ህዝብ ደጉን እንዳያይና በብስጭት ክፉን እያሰበ እንዲቆጣ ይገፋል። በገፊና ጎታች ስልት በመናበብ ህዝብ ላይ የሚደፋው መርዝ መቆሚያ ያለው አይመስልም። የመንግስት አካላትና ብልቶቹ የሆኑት ድርጅቶች በከፊል በዚሁ የሴራ ፖለቲካ ውስጥ መነከራቸው ደግሞ ጉዳዩን አሳሳቢ አድርጎታል። ነገሩ ሁሉ ከልኩ በላይ እንዲፈላ የሆነው ወተት አይነት እንዳያደርገው የሰጉ ” እናስተውል” እያሉ ነው። ኢትዮያ መቶ ሃያ ሚሊዮን ህዝብ ይዛ 240 ሚሊዮን ጆሮ ሊኖራት ሱገባ 240 ምላስ አፍርታ ጨንቋታል። ደግነቱ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያለው ወገኖ ሲሰላ ቁጥሩ እዚህ ግባ የሚባል አለመሆኑ እንደሆን ….

ትንሽ ለመጠንቀቅ የፈለጉ ” አውዛጋቢ” ሲሉ ገልጸውታል። እላፊ የሄዱ ደግሞ ” ህዝብን ከህዝብ የሚያጣላ፣ ሰላምን ሳይሆን ዳግም ግጭትን የሚጠነስስ፣ ሃላፊነት የጎደለውና አውዱን የሳተ ወዘተ” ሲሉ ሲዘነጥሏቸው ከርመዋል። ዝንጠላው በሙሉ ወገን የለየና “እኔን ወይም የኔን ብሄር ለማጥቃት ነው ወይም ለመወረፍ ነው” በሚል ስሜት የታጠረ ነው። በተከታታይ መድረክ እየቀያየረ ሲቀርብ የነበረው ውግዘት ሲካሄድ የነበረው በአቶ(ስራ ላይ የሌለን አምባሳደር አምብሳደር ስለማንል ነው አቶ ያልነው) ሬድዋን ሁሴን ላይ ነው። በተቃራኒ አቶ ሬድዋን ያቀረቡትን አስረጂ ንግግር ያደነቁ፣ የወደዱና ከዚህም በላይ ገፍቶ በመሄድ በግልጽ መነጋገር እንደሚገባ ያሰመሩበትም አሉ።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር / ትህነግ ተጎናጽፎት የነበረውን የሽብርተኛነት ማዕረግ ለማንሳት በተጠራ የፓርላማ ስብሰባ ላይ አስረጂ ሆነው የቀረቡት አቶ ሬድዋን ” ኢትዮጵያን ያያዘው ሰበዝ የሁሉም ነው” ሲሉ በንግግራቸው መካከል ማስገባታቸው፣ ” በማንም ወገን ጀርባ ኢትዮጵያ አልታዘለችም” ሲሉ አሳባቸውን ያጠነከሩበትና ትጥቅ ማስፈታትን በተመለከተ ” በትክክል ጠብመንጃ የመልቀም ፍላጎት ካለ ሁሉም ክልል የተበተነው መሳሪያ ሙሉ በሙሉ መለቀም አለበት” ሲሉ እግረመንገዳቸውን መናገራቸው ቅሬታን አስነስቷል። አሳባቸውን በማንሳት የራሳቸውን ትንተና የሰጡ ፣ ሬድዋን የአማራን ብሄረሰብ ለማጥቃት የተጠቀሙበት እንደሆነም ገልጸዋል።

የበላይነት እሳቤና የበታችነት ስቃይ በማንሳት ሁለቱም መዘዝ እንዳላቸው ያስረዱት አቶ ሬድዋን፣ ትህነግ የበታችነት ስሜት ከፈጠረበት ስቃይ ተነስቶ አገሪቱን በመከፋፈል የሰራው ጥፋትና መጨረሻ ላይ የሆነው በበላይነት ስሜት የሚሰቃዩም የትህነግን ዓይነት ጥፋት ሊፈጽሙት እንደሚችሉ አስታውቀዋል። እንግዲህ ይህ ንግግራቸው ነው “የግል አስተአየታቸውን ከአጀንዳ ውጪ ወጥተው አስተጋቡ” በሚል ያስተቻቸው።

የደገፏቸው እንደሚሉት ራሳቸውን ” የሰውነት ውሃ ልክ፣ የታላቅነት ማማ” በማለት በገሃድ የሚጠሩ አክራሪ የአማራ ፖለቲከኞች በአቶ ሬድዋን ንግግር ቢበሳጩ ሊደንቅ እንደማይችል ይገልጻሉ። ጦርነቱን ትህነግ ሲጀምረው “የህ ጦርነት የአንተ አይደልም። አይመለከትህም” ሲሉ የነበሩ ወገኖች የሰላም ስምምነቱን መቃወማቸው አካሄዱን ስለሚያጠራው እዛ ላይ ማተኮርና የሚሰነዘሩ ተቃውሞዎችን መመርመር እይታን ያስተካክላል ሲሉም ይገልጻሉ።

ትህነግ የሽብርተኛነት ማዕረጉ እንዲነሳለት በተጠራው ስብሰባ ላይ ስጋታቸውን የገለጹ የአብን ተወካዮች ” ትህነግ መሳሪያ አስረክቦ ሳይጨርስና ሙሉ በሙሉ የፕሬቶሪያውን ስምምነት ሳይፈጽም ሽብረተኛነቱን ማንሳት አይገባም” በሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ” ነገስ ዳግም ወረራ አለማድረሱን እንዴት እናረጋግጣለን?” የሚል ጥያቄም አንስተዋል። አካሄዱንም በደፈናው የመኮነን መልክ አሳይተዋል። ከሽብርተኛነት ፍረጃው ጋር ያልተያያዙ ጉዳዮችን በማንሳትም ሌሎች አዋጆች ቀድሞ እንደመሻር ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ የፍትህ ሚኒስትሩ ከህግ አንጻር ማብራሪያ ከሰጡ በሁውላ የቀጠሉት አቶ ሬድዋን “ለግንዛቤ” ብለው የስምምነቱን ዋና ነጥቦች አንድ በአንድ አንስተዋል። ከዛም ትህነግ “ህገወጥ ምርጫ አድርጊያለሁ፣ የመሰረትኩት ጦር አግባብ አይደለም፣ መሳሪያ አስረክባለሁ፣ መንግስ የሚያወቀው አዲስ ምርጫ አደርጋለሁ፣ ሰራዊቴን እበትናለሁ …” ማለቱ የስምምነቱ አካል ሲሆኑ ቀሪዎቹን ለማስፈጸውም ሽብርተኛነቱ መነሳቱ አግባብ እንደሆነ በአቶ ጢሞቲዎስ የህን ማብራሪያ እንደተባለው አቶ ሬድዋን አተር አድርገው ገልጸዋል።

ይህን እንደ ማሳያ ካነሱ በሁዋላ ” መከላከያ የሚችለውን ያህል ከባድ መሳሪያ ተረክቧል” አሉ። ትግበራው ሰፊ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ እንደሚቀጥል አስታውቀው ጠመንጃ ለቀማውን አስመልክቶ ” መከላከያ በየስራቻው የጥበቃ ስራ እንዲሰራ አልተፍለገም” ብለዋል። አቶ ሬድዋን ያፍረጡት አንድ ሃቅ ቢኖር መከላከያ በየጉራንጉሩ ቢገባ ለጥቃት የመጋለጡን ጉዳይ ነው። ስለዚህ በመነጋገር የትግራይ ታጣቂዎች የፖሊስ ስራ እንዲሰሩ ከስምምነት ተደርሷል። እሳቸው ቃል በቃል ባይሉትም፣ ሌሎች ክልሎች ጠብመንጃ እያላቸው ትግራይን ሙሉ በሙሉ ከጥብመንጃ አንጋችነት ነጻ ማድረግ ጠማማ አመክንዮ ነው። ስጋትም ሊገባቸው ይችላል። በሁሉም ቦታ የታጠቀው ሃይል መከላከያ ብቻ ቢሆን ኖሮ ይህንኑ በትግራይ ማስፈጸም ቀላል እንደሚሆን አፍቃሪ ትህነጎች በግልጽ የሚናገሩት፣ አቶ ጌታቸውም ቀደም ሲል የጠቆሙት ጉዳይ ነው።

አቶ ሬድዋን ለዚህ ይመስላል ጠብ መንጃ እንዲለቀም ከተፍለገና ከልብ የሚደገፍ ከሆነ በሁሉም ክልል ያለው ከባድ መሳሪያ ከፖሊስ በቀር ሊለቀም እንደሚገባ አመልከቱ። ቀጠሉና ” ሁሉም ቦታ ሰላም እንዲሆን ያስፈልጋል?” ሲሉ ጠየቁና ይህ ከሆነ ሁሉም ክልል በገፍ የፈሰሰውና ጠላቶች ከዶላር ጋር ያሰራጩት መሳሪያ በሙሉ መሰብሰብ አለበት። ትግራይ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልል!!

የሰላም ጉዳይ ላይ ሲናገሩ ላለፉት ሶስት ዓመታት ትምህርት ቤት ያልሄዱ የትግራይ ህጻናትን ማን ያስብላቸው? ከትህነግ ውጪ ያለውን የትግራይ ህዝብ ማን ያስታወሰው? ትግራይ ኢትዮጵያ ነች ከተባለ ይህ ፓርላማ በሚዛናዊነት ሊቆረቆር እንደሚገባው፣ የትግራይ ወኪሎች እዚህ ፓርላማ ውስጥ እንዲመጡ መሰራት ሚዛናዊ እንደሚያደርግ ጠቅለል አድርገው ያነሱት ሬድዋን ” ኢትዮጵያ በማንም ጀርባ አልታዘለችም” ሲሉ ኢትዮጵያ ከተባለ ልክ እንደሌሎች ሁሉ የትግራይን ህዝብ አስፈላጊነት አመልክተዋል።

በጦርነቱ ወቅት ህዝብ ተረባርቦ የኢትዮጵያን አንድነት ማስጠበቀና ወረራውን መቀለበስ እንደተቻለ ያወሱት አቶ ሬድዋን የበታችነትና የበላይነት ስሜቶች ሁለቱም አጥፊ እንደሆኑ አጠንከረው ገልጸዋል። በበላይነት ስሜት ስቃይ ” አንተ እኔን አታክልም፣ አንተ እኔን ካልመሰልክ ” የሚለው አካሄድና በበታችነት ስቃይ ” ከፋፍዬ እገዛሃለሁ” የሚለው አካሄድ እኩል የጥፋት ምንጭ እንደሆኑ አመልክተዋል።

“እናንተ እኔን አልመሰላችሁም “የሚለው እሳቤና በሽታ ከጀርባው መዘዝ እንዳለው በማስጥንቀቅ የተናገሩት አቶ ሬድዋን ” እንከፋፍልህ እንደሚሉት ሁሉ እንጨፍልቅህ የሚሉትም ለህዝብ ሰላም አይሰጡም” ሲሉ በገሃድ ተናግረዋል። በወቅቱ ስብሰባ ላይ “እንጨፍልቅ ወይም የበላይ ነን” በሚል አሳብ ያነሱ ሳይኖሩ እሳቸው ይህን ማለታቸው አግባብ እንዳልሆነ ተደርጎ ተወስዶባቸዋል። እንደውም ” የግል ስሜታቸውን አንጸባረቁ” በሚል ተወቅሰዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የደህንነት አማካሪ የሆኑት አቶ ሬድዋን ስም ባይጠሩም የተናገሩት አማራን እንደሆነ ተደርጎ ሰፊ “ትንተና” እንዲሰጥባቸው ሆነዋል። አማራ ክልል በወቅቱ የትህራይ ክልልን ለመተንኮስም ይሁን ለመውረር የሚያስችል ቁመና ስላልነበረው የአቶ ሬድዋን እይታ ሸውራራ መሆኑንን የገለጹም አሉ። ይሁን እንጂ ሚዛን እንዴት አስጠብቆ መሄድ እንደሚቻል ያመላከቱ የሉም።

አቶ ሬዋን ” የትህነግ ጋር ሰላም ሲፈጠር ለስንቶች ስጋት ሆነ ” ሲሉ የጠየቁት አቶ ሬድዋን፣ ከትህነግ ጋር ሰላም ሲፈጠር ቀዳዳ በሌላ አቅጣጫ ምን እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ልብ ማለት እንደሚገባ አመልክተዋል። እንደ እሳቸው አባባል ብቻ ሳይሆን ከትህነግ ጋር የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በሁዋላ በአገሪቱ መልኩን እየቀያየረ የሚታየው ማተራመስና ነውጥ በርካታ ወገኖችን ” የዚህ ሁሉ ትርምስ ባለቤት ማን ነው” የሚል ጥያቄ እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። ይህንኑ አስመልክቶ ቀደም ሲል በስፋት መዘገባችን ይታወሳል።

ኢትዮጵያን ለመናጥ ቀን በቀን አጀንዳ የሚያወጡትና ይህንኑ አጀንዳ ተከትለው ርብሻውን የሚያቀጣጥሉት እንጂ፣ የአመጹና የረብሻው ባለቤቶች ሚስጢር መሆን፣ በገሃድ ወጥትው ሃላፊነት አለመውሰዳቸው ነገሩን እንቆቅልሽ አድርጎታል። በርካቶች እንደሚሉት ቢሳካና አመጹ ግቡን ቢመታ ቀጣዩ ማን እንደሆነ ህዝብ አለማወቁ ነገሮችን ውስብስብ ያደርጋቸዋል።

ትግራይ ክልል ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ስትመለስ ሌሎችም መሳሪያ እንዲፈቱ ጥያቄ ያነሳሉ የሚሉ አሉ። አንዳንዶች ደሞ ሙሉ በሙሉ የክክሎች ልዩ ሃይል በመከላከያ ስር ሆኖ እንዲበተን አሳብ ያቀርባሉ። ከመደበኛ ፖሊስ ውጭ ሌሎች ሃይሎች ማንም ይሁን ማን ጠብመንጃ እንዳይዝ መደረግ ይገባዋል። ከዚህ ውጭ አንዱ ትጥቅ ፈቺ ሌላው እንዳሻው ታጣቂ ሊሆን አይገባም በሚል የሚሞግቱ አሉ። እነዚህ ወገኖች በድንበር አካባቢ ያሉ ዜጎች ራሳቸውንና ድንበርን መከላከል እንዲችሉ በጥናት የማስታጠቅ ወይም የግላቸውን መሳሪያ በፈቃድ ለሚደገፍ ተግባር ብቻ እንዲጠቀሙበት ማድረግ ያስፈልጋል።

አቶ ሬድዋን ላይ የተሰነዘሩት ነቀፌታዎችን አንዳንድ የሻዕቢያ ደጋፊዎች ባልተለመደ ሁኔታ ሲያራቡና “ትክክለኛ ትችት” ሲሉ ተስተውሏል። በቅርቡ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ሱዳንን ማስጠንቀቂያ የሰጡት ፕሬዚዳንት ኢሳያስም ከትህነግ ጋር የተደረገው ስምምነት ደስታን እንዳልፈጠረላቸው ከማስታወቃቸው ጋር በማያያዝ ” ኦሮማይ” በድጋሚ በሚዲያዎች ሊተረክ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ደራሲ በዓሉ ግርማ የጻፈው ኦሮማይ መጽሃፍ ዳግም ቢተረክ አሁን ላይ ላለው ትውልድና ወቅታዊ እንቅስቃሴ በቂ ግንዛቤ እንደሚሰጥ አስተያየታቸውን የጻፉ ተጨማሪ ማብራራሪያ አልሰጡም።

ኦሮማይ በጋዜጠኛና ደራሲ በዓሉ ግርማ በ1975 ዓ.ም ለኅትመት የበቃ ድርሰት ነው። መጽሐፉ በጊዜው የኢትዮጲያ ኣካል በነበረው በኤርትራ በረሐዎች ይካሄድ በነበረው የቀይ ኮከብ ዘመቻ ዙርያ የሚያጠነጥን ሲሆን ሻዕቢያን ማመን ይቻላል? ወይስ አይቻልም? እንዴት ነው ድራማው የተተወነው የሚለውን ገሃድ በምርጥ ብዕር አስቀምጧል። አገራቸውን እንደ ጥሬ ስጋ የሚያወራርዱ ባለጌ መሪዎችን ያሳያል።

በኢትዮጵያ በበታችነትና በበላይነት ስሜት ስቃይ ሰላማዊውን ህዝብን መከራ ውስጥ የሚከት የፖለቲከኞች ድራማ መሆኑን ህዝብ ሊረዳና ሚዛኑንን ጠብቆ ሊጓዝ እንደሚገባ የሚገልጹ፣ ሚዛናው እይታ፣ አንዱ ላይ የተነቀፈን መጥፎ ተግባር መስሶ ባለመድገም ሰላምን ማስጠበቅ እንደሚቻል ይናገራሉ።

ዛሬ ትህነግ አብጦ የለኮሰው ጦርነት ያስከተለው ውድመትና እልቂት የውስጥ ጥያቄ እያስነሳበት መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ምክንያቶች ትህነግ ዳግም ጦርነት የሚለኩስ ድርጅት የመሆኑ ጉዳይ ስሌቱ ከዜሮ በታች እንደሆነ የትህነግ አፍቃሪዎች ሳይቀሩ እየገለጹ ነው።ምድር ላይ ያለውም እውነታ የሚያሳየው ይህንኑ ነው። ይህን አጋጣሚ ተጠቅሞ አቶ ሬድዋን ” አሮጌ ትርክት” ያሉትንና የትግራይ ህዝብ ሲሰማው የነበረውን ቅስቀሳ ማረም እንደሚገባ ነገሮችን በጥሞና የሚያዩ ይጠቁማሉ።

“ልትወረር ነው፣ ለትጠፋ ነው፣ ተከበሃል..” በሚል የትግራይ ህዝብ ዕድሜ ልኩን የትህነግ ጥገኛ ሆኖ እንዲኖር የሃሰት ትርክት ሲጋት ለኖረው ህዝብ ፍቅር በማሳየትና እንደ ማንኛውም ዜጋ የሚገባውን በልኩ በመስጠት የሃሰት ትርክት ሲነገረው እንደነበር ማሳየት እንደሚገባ አቶ ሬድዋን ገልጸዋል። ንግግራቸውን የተቹ ይህን አስመልክቶ ያሉት ነገር የለም።

አቶ ጌዲዮን ሽብርተኝነት ተነሳ ማለት በወንጀልና በከባድ የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚፈለጉትን ነጻ ማድረግ ማለት እንዳልሆነና በሽግግር ፍትህ ሂደት እልባት እንዲያገኝ እየተሰራ መሆኑን ቢያስታውቁም፣ ኮሚሽኑ ተቋቁሞ እየሰራበት እንደሆነ በገሃድ ቢታይም ከነቀፌታው መንደር የተባለለት ነገር የለም።

Exit mobile version