Site icon ETHIO12.COM

ሌሊሴ ደሳለኝና ዘሃራ ኡመር አሊ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትና ምክትል ሆነው ተሾሙ

ምክር ቤቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝን ሹመት መርምሮ አፀደቀ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝን እና ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዛህራ ኡመር አሊ ሹመትን መርምሮ አፀደቀ፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት 13ኛ መደበኛ ጉባዔውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ እያካሄደ በሚገኘው 13ኛ መደበኛ ጉባዔ በዕጩነት የቀረቡ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ሌሊሴ ደሳለኝ እና ምክትል ፕሬዚዳንት ወይዘሮ ዛህራ ኡመር አሊ ሹመትን መርምሮ በአብላጫ ድምፅ አጽድቋል፡፡

FBC

Exit mobile version