Site icon ETHIO12.COM

ዘራፊው ማን ነው? ተመድ ከሽራሮ መጋዘን ለ100 ሽህ ሰዎች የሚሆን የምግብ እርዳታ መዘረፉን አስታወቀ

ተመድ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ምግብ ስርቆትን እየመረመርኩ ነው አለ!

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ምግብ ስርቆትን እየመረመርኩ ነው አለ።የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከሽራሮ መጋዘን ለ100 ሽህ ሰዎች የሚሆን የምግብ እርዳታ መዘረፉ ተነግሯል።በኢትዮጵያ የሚደርሰውን ምዝበራ ለመግታት አፋጣኝ እርምጃዎች ሊወሰድ ይገባል ተብሏል።የተባበሩት መንግስታት የምግብ እርዳታ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ የነፍስ አድን ሰብዓዊ እርዳታን መሰረቁን ገልጿል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ክላውድ ጂቢዳር አሶሼትድ ፕረስ አገኘሁት ባለው ደብዳቤ “በአንዳንድ ገበያዎች የሚካሄደው መጠነ ሰፊ የምግብ ሽያጭ በጣም ያሳስበናል” በማለት የተዘረፈው እህል ገበያ ላይ መዋሉን ጠቁመዋል።”ይህም መልካም ስምን ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ለተቸገሩ ሰዎች ግብአቶችን ለማሰባሰብ አቅማችንን ያሰጋል” ብለዋል።

አክለውም “በሀገሪቱ ውስጥ የሚደርሰውን ምዝበራ እና ዝርፊያ ለመግታት አፋጣኝ እርምጃዎች መወሰድ አለባቸው” ብለዋል።ደብዳቤው ከቀናት በፊት የተጻፈና በድርቅ እና ግጭት ከሀገሪቱ 120 ሚሊዮን ህዝብ 20 ሚሊዮን ለሚሆኑት የሰብዓዊ እርዳታ ለሚያቀርቡ አጋሮች የተላከ ነው ተብሏል።

ጂቢዳር አጋር ድርጅቶች ተመሳሳይ ሁነት ገጥሟቸዋል ከሆነ መረጃ እንዲያጋሩም ጠይቀዋል።ደብዳቤው ስለ “ዝርፊያው” ዓይነት አይጠቅስም።ሆኖም ሁለት የእርዳታ ሰራተኞች እንደተናገሩት እርዳታው ከሽራሮ መጋዘን የተዘረፈና ለ100 ሽህ ሰዎች የሚሆን ነበር።

[Alain]

Exit mobile version