Site icon ETHIO12.COM

50 ሀገራት በሱዳን ያሉ ዜጎቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል እንዲወጡ ይፋዊ ጥያቄ አቀረቡ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤዴታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የውጭ ሀገር ዜጎችን ከሱዳን ለማስወጣት በሚደረገውን ጥረት አስመልክቶ ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በሱዳን የተከሰተውን ግጭት አስመልክቶ የውጭ ሀገር ዜጐች ከሱዳን ለማስወጣት እየተደረገ ያለውን ጥረትና ስደተኞችን እየተቀበለች መሆኑን ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲካ ማህበረሰብ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በሰጡት ማብራሪያ፣ በሱዳን የተከሰተውን ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም የኢትዮጵያ መንግስት ጥሪ ማቅረቡን ገልጸዋል። ችግሩ በሰላም እንዲቋጭ የአለም አቅፉ ማህበረሰብን ጥረት ይጠይቃል ብለዋል።

የሱዳንን ጦርነት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞችን የአለም አቀፉ ማህበረሰብ መደገፍ እንዳለብት ጠቁመዋል። ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኞችን ኢትዮጵያ እያስተናገደችም ነው።

በሱዳን ያሉ የውጭ ሀገር ዜጐችን በኢትዮጵያ በኩል ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት ኢትዮጵያ ድጋፏን እያደረገች ነው፣ የአለም አቀፉ ማህበረሰብ፣ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብና የአለም አቀፍ ተቋማት ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል። የችግሩን ክብደት በመገንዘብ ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት ማገዘ እንደሚገባ አሳስበዋል።

50 ሀገራት በሱዳን ያሉ ዜጐቻቸውን በኢትዮጵያ በኩል እንዲወጡ ይፋዊ ጥያቄ ማቅረባቸውንም ገልጸዋል።

(ኢ ፕ ድ) በሞገስ ጸጋዬ

Exit mobile version