Site icon ETHIO12.COM

በኦሮሚያ የሰብአዊ መብት የጣሱ አስር አመራሮች ታሰሩ

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ ሃርወዩ በምትባል ቀበሌ ሁለት ወጣቶች ላይ ኢሰብአዊ ርምጃ የወሰዱ የተባሉ ባለስልጣናት መታሰራቸው ተሰምቷል።

በአከባቢው ሰሞኑን ሁለት ወጣቶች እጅ እግራቸውን የፊጢኝ ወደኋላ ታስረው ሲደበደቡና ሲሰቃዩ የሚያሳይ ምስል በማኅበራዊ መገናኛ ተለቅቆ መነጋገሪያ ሆኗል። ጃሮ ዳሌ እና ጋርቦሌ ዋቆ በተባሉ ሁለት ወጣቶች ላይ የተፈፀመው የደቦ ፍርድ በሚል በሰብአዊ መብት ጥሰት ተተችቷል ።

የያቤሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጎቡ ጫና እንደተናገሩት፤ በዚህ ሰብአዊ መብትን በጣሰው ድርጊት የተሳተፉት ከቀበሌ አስተዳዳሪ እስከ የአከባቢውን ሰላም እንዲያስጠብቁ የታጠቁ ሚሊሻዎች ያሉት ናቸው ብለዋል ።
በመሆኑም ወጣቶቹን ይዘው ያለ ፍርድ አስረው በማሰቃየት ድርጊት የተጠረጠሩ እስከ ዛሬ የቀበሌ አስተዳዳሪ እና ታጣቂ ሚሊሻዎችን ጨምሮ ዐሥር ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ለፍረድ እየቀረቡ ነው ሲሉ ገልፀዋል ።

አንደ ኃላፊው ገለጻ ለችግሩ መነሻ የሆነው በቀበሌው 6 ኩንታል የርዳታ እህል ጠፍቶ በገበያ መሸጡና በዚህም ስርቆት ሁለቱ ወጣቶች መጠርጠራቸው ነው ። ሁለቱ ለድብደባ እና ስቃዩ የተዳረጉት ወጣቶች አንዱ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን፤ ሌላኛው ደግሞ እረኛ ነው ተብሏል ።

የወረዳው አስተዳዳሪ ድብደባው የተፈፀመባቸው ሁለቱ ወጣቶች አሁን በደህና ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙና እነሱን የሚያስከስስ መረጃ አለመኖሩንም አንስተዋል ። ስለጉዳዩ የተጠየቀው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በጉዳዩ ላይ መረጃ እያሰባሰብኩ ነው ብሏል፡፡
(ዶይቸ ቬለ)

Are Tigray mercenaries fighting in conflict-ravaged Sudan?
Mercenaries from Ethiopia’s Tigray People’s Liberation Front are fighting alongside Sudanese army regulars against fighters of the Rapid Support Forces (RSF), the paramilitary group is claiming. The RSF which has been battling …
Sudan’s RSF Accuse Tigray People’s Liberation Front of Backing SAF
Sudanese warring party Rapid Support Forces has officially accused the Tigray People’s Liberation Front Fighters of fighting in Sudan in support of the Sudanese Armed Forces (SAF). Civil war broke out in …
የኢትዮጵያን – “መከራዋን ካልተሸከምንላት ኢትዮጵያዊነቱ ምኑ ላይ ነው” አብይ አሕመድ
“ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ” እያሉ በስሟ ሲምሉ የነበሩ ብዙዎች ነበሩ፤ ከልባቸው ለቃላቸው ታምነው ልጅ የሆኗት ግን ጥቂቶች ብቻ ናቸው። አንዳንዶች በስሟ የሚገዘቱት እንጀራዋን ለመብላት እንጂ መከራዋን ለመካፈል አይደለም፤ በተቃራኒው እንጀራዋን በልተው ተረከዛቸውን አነሡባት" ሲሉ …
አቡነ አብርሃም “እንዳይረፍድብን” ሲሉ ለመጸጸት እንኳን ዕድል እንዳይታጣ አስጠነቀቁ
"ወገኖቼ እንማርና እናስተምር፣ ወንጀልን እንጸየፈው፣ እንጥላው፣ ወንጀልን ተጸይፈን ወንጌልን እንውደደው፣ በወንጌል እንኑር፣ ወንጌል ሕጓም ስርዓቷም ያማረች ናት፤ ወንጌላዊ መኾን መልካም ነው፣ ወንጀለኛ መኾን ግን ሐጥያት ነው ብለዋል፡፡ እህትና ወንድም፣ እናትና አባትን አጎሳቁሎ …
Exit mobile version