Site icon ETHIO12.COM

“360 እና መሰል የጠላት ተላላኪዎችን ከህዝባችን ላይ እናራግፋለን…!”

ከአማራ ፖለቲካ Ethio 360 እና መሰል አወናባጅ የፖለቲካ ጨዋዎችን ማራገፍ ያስፈልጋል። እነዚህ ሰዎች የአማራ ህዝብ ስትራቴጂክ ጥያቄዎች እንዳይደመጡ እና በደራሽ አጀንዳዎች ብቻ ተወስኖ ሲራኮት እንዲውል ሆነ ብለው የሚሰሩ የጠላት ወኪሎች ናቸው። የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ሜንስትሪም እንዳይደረጉ እና በዩቱብ ለቅሶ ብቻ ታጥረው እንዲቀሩ ከጠላት ጋር ተናበው የሚሰሩ ለመሆናቸው እስካሁን የመጡበትን የኋላ ታሪክ መፈተሽ የተገባ ነው። የአማራን ህዝብ ሌጅትሜት ጥያቄዎች እንዳይደመጡ ያደረጉት እንደ ኢትዮ 360 ዓይነት ወሬ አመላላሾች ናቸው። አንዳንድ የዋህ የእኛ ሰዎች እርስ በርስ አትጋጩ ይላሉ። እነዚህን ሰርጎ ገቦች መታገል እና ከህዝባችን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ማድረግ የእርስ በርስ ትግል ሳይሆን የጠላትን አንድ እጅ መቁረጥ ማለት ነው። በእነዚህ ሰዎች ያተገባ ቅስቀሳ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች በሌሎች ብሔረሰቦች ዘንድ በጥርጣሬ ከመታየቱ በተጨማሪ የአማራ ህዝብ ዋና ዋና አሳቢዎችም ትግሉን እየተው እንዲሸሹ ሆኗል። ኢትዮ 360 እና መሰል የጠላት ተላላኪዎችን ከህዝባችን ላይ እናራግፋለን…!

ሐብታሙ አያሌው የተባለ ሚጥጥዬ ጭንቅላቱን ለወያኔ ያከራዬ ሰው ስሜን ጠቅሶ ሰዎች እርምጃ እንደሚወስዱብኝ እያወራ ነበር ብለው የሚከተለውን ቪድዮ ላኩልኝ። for ever ጎንደር አይሄድም ብሏል። ለዘላለም ጎንደር አይሄዳትም ማለቱ መሰለኝ። ተመልከት እንግዲህ እኔን የጎንደሩን ባላባት ጎንደር መሄድ ሊከለክለኝ ሲዳዳው።

ጎንደር ቋራ ሆቴል ቴራስ ላይ ሆኘ ቁልቁል ባለ ቁንዳላውን ህልመኛ እየተመለከትኩኝ በወቅቱ እንደ ሃብታሙ ያሉ ነገር አመላላሾች አባቴን እንዴት እንደተዋከቡት አስብና አዝናለሁ። ህልመኛው ቋረኛ ነገር አወሳዋሹን ሰይፉን አንስቶ ሲፋለም ውሎ ደክሞት ወደ መቅደላ ተራራ ሲወጣ ወደኋላ ዞሬ አስበውና ከንፈሬን እመጣለሁ። ብዙ ቀን ከካሳ ሃውልት ጋር ተፋጥጨ አምሽቻለሁ። ህልምህ ምን ነበር? ማን ምን ብሎ አሰናከለህ? ራዕይህ እውን ቢሆን ኖሮ ዛሬ የት ነበርን? እያልኩኝ ሽጉጡን በግራ ጎራዴውን በስተቀኝ ሻጥ ያደረገውን ሃውልት እስትንፋስ እንዳለሁ አድርጌ እጠይቃለሁ። ለህልሜ ስንቅ፣ ለመንፈሴ ብርታትን እሸምታለሁ። ጎንደር ቀዳሚዋ፣ ጎንደር ጅንኗ የመሄዴ አንዱ ትርፍ ይኸ ነው። እናማ ጎንደር እንዴት for ever እቀራለሁ ለማለት ነው።

የሐብታሙን ቅስቀሳ በቀላሉ አልመለከተውም። እነማን ጋር እንዲህ አይነት ነገሮች እንደሚዶለቱ ሁሉ መረጃው አለን። እነዚህ ሰዎች መጀመሪያ ስም ያጠፋሉ። ስም አጥፍተው ዝም አይሉም። ግድያ ይፈፅማሉ። ገድለው ዝም አይሉም። ባንዳ ምናምን የምትል የእነሱ የሆነች ባህሪን ይቀቡሃል። ይኸ አዙሪት የተለመደ ነው። ከሰኔ 15 እስከ…!

እነ ሃምታሙ እስካሁን ከሰሯቸው ስም ማጠልሸቶች ውስጥ 90% በላይ የጎንደር ሰዎች ላይ ትኩረት አድርገው የተሰሩ ናቸው። ለምን ለሚለው መልሱ ወያኔዎች ናቸው የሚያውቁት። እነሱ ቩቩዚላ ናቸው። የሃብታሙ እና የወያኔ ትውውቅ ጀብሎ ሆኖ ነው እየሰራ ይጀምራል። ወያኔ ሃብታሙን ከጀብሎ ላይ አንስታ የሰፈር ወሬ አቀባይ አደረገችው። ሰው የልምዱ ውጤት ነው እንዲሉ ይኸው ልምዱ ጠቅሞት እስካሁን ድረስ በርትቶ ወሬ አመላላሽነቱን ገፍቶበታል።

ሀብታሙ አያሌው እና ሚድያው ከአምባቸው መኮንን እስከ ምግባሩ ከበደ፣ ከደስዬ ደጀን እስከ አገኘሁ ተሻገር፣ ከሙሉዓለም ገብረመድህን እስከ ታማኝ በየነ፣ ከሻምበል በላይነህ እስከ አያሌው መንበር፣ ከመላኩ አለበል እስከ ቀለመወርቅ ምህረቴ፣ ከኮማንደር ዋኘው እስከ ዶክተር ሂሩት፣ ከዶክተር ጌታቸው ጀንበር እስከ ኮሎኔል ደመቀ፣ ከጣሂር መሃመድ እስከ መልካሙ ሹምዬ፣ ከቹቹ አለባቸው እስከ ይርጋ ሲሳይ፣ ከዘላለም ልጃለም እስከ ኮሚሽነር ዋጋው፣ ከጌታቸው ሽፈራው እስከ ሙሉቀን ተስፋው፣ ከደሳለኝ ጣሠው እስከ ደሳለኝ አስራደ፣ ከመላኩ ፈንታ እስከ አሸተ ደምለው…ድረስ አንድ በአንድ ዘምተውብናል። ሆነ ብዬ ያለፍኳቸው እንዳሉ ሆነው ዘርዝሬ ያልጨረስኳቸው ብዙ የጎንደር ልጆች የዘመቻው ሰለባ ናቸው። የእነ ሃብታሙ ፍላጻ ያላረፈበት አንድስ እንኳን የጎንደር ፖለቲከኛ ማን ነው? ህዝቤ ሆይ እስቲ ይቺን ቀላል ጥያቄ መልስልኝ። አንድስ እንኳን የእነሱ ጥቁር ምላስ ያልጎበኘው ጎንደሬ ጥራ ብትባል ማንን ትጠራለህ። ለምን በዚህ ደረጃ እንድንናገር ይፈልጋል ጎበዝ። ልብ አድርጉ እንግዲህ ይኸ ሁሉ ጎንደሬ ለዘመቻ ሲመቻች ምክንያታቸው ምን እንደሆነ አንባቢ ይፍረደው። የወያኔዎች የጎንደር ኤሊት አስቸገረን ትርክት ከጀብሎ ላይ ካነሳችው ሰውዬ ጋር በቀጭን ክር ይተሳሰር ከሆነ ፍርዱን ለእናንተ ትቻለሁ።

ከሃብታሙ አያሌው ንግግር ፈገግ ያሰኘኝ ነገር “ጋሻው መንግስት ጎንደር ላይ ለምን ብዙ ሰው መግደል አልቻለም ብሎ ተበሳጭቶ ነው የጻፈው” ያላት ነገር ነች። እኔ ጎንደሬ ነኝ፣ ጎንደሬ ስሆን አማራ እሆናለሁ፣ አማራ ስሆን ደግሞ ኢትዮጵያዊ። በቋራው ግልገል እየማልን ጎንደሬ ኢትዮጵያዊ ሆነን ነው ያደግነው። በምንም ልንቀይረው አንችልም። ጎንደሬነቴን Proud አደርግበታለሁ። ጎንደሬ አማራ ኢትዮጵያዊ ነኝ ለማለት ወደኋላ አልልም። ከመሰረቴ ተነቅዬ ስር የሌለው ዛፍ ልሆን እንዴት ይቻለኛል። ጎጠኛ ምናምን የሚለው ሰንካላ ታፔላ ጎንደሬ ነኝ እንዳልል ሊያደርገኝ አይችልም። ጎጥህን እዛው ፈልግ። ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ከመግባታችን በፊት የፌስቡክ አካውንቴ ጋሻው መርሻ ዘ-ጎንደር ነበር የሚለው። ፓርቲ ውስጥ ገብቸ ኃላፊነት ስቀበል ዘ-ጎንደር የሚለውን ኤዲት አደረኩት። በብዙ ምክንያት…!

ጦርነት ሰው ሲበላ ተመልክቻለሁ። ጦርነት ሃብት ሲጨረግድ አይኔ ብረቱ አይቷል። ጦርነትን የማውቀው በስማ በለው አይደለም። የጦርነትን ግሳንግስ በእጀ ዳብሸ፣ በአይኔ ተመልክቸ፣ በስሜቴ አጣጥሜዋለሁ። በዚህም የተነሳ የሰላም አማራጮች ሳይሟጠጡ ወደ ግጭት መሄድን እፈራዋለሁ። እኔ ከሰሞኑ በነበረው ውጥረት ጎንደርም ሆነ ሌላው የአማራ ክፍል ላይ አንዲትም ደም እንዳትፈስ ፈልጌ የበኩሌን ጥረት አድርጌያለሁ። በደንብ የማውቀውን እና ለሃብታሙ ዘመቻ ያጋለጠኝን የጎንደሩን ጉዳይ ብቻ ለምሳሌ ላንሳ። በአጋጣሚ መከላከያን የሚመሩት የአካባቢው ሰዎች ናቸው። እነ ጀኔራል ሙሉዓለምን፣ ጀኔራል ሃብታሙ እና ጀኔራል ማርዬን ፋኖዎች ያውቋቸዋል። ለፋኖዎቹም ሆነ ለእኛ ጓደኞቻችን ናቸው። አንዳንዱ ነገር አይጻፍም። ሰዎችን ርቀት ድረስ ሄዶ ለማስረዳት ሲሞከር ያልተገባ መረጃ ይወጣል። ሃብታሙ አያሌው በጦርነቱ ወቅት አሰላለፉ በጠላት ጎራ ስለነበረ ይህንን ሊረዳ አይችልም። የእሱ እውቀት ስለ እነ ጀኔራል ታደለ ወረደ እና TDF እንጅ ስለ እነ ጀኔራል ማርዬ እና ፋኖ ግንኙነት እና አንድነት አይደለም። ለማንኛውም ወንድማማቾች ናቸው። በደንብ ይተዋወቃሉ። ይህንን እኔ የማውቀውን ሩብ ያክል እንኳን ሃብታሙ አያውቅም። ምንነቱም ሊገባው አይችልም።

ለማንኛውም የፋኖ አባላት ለእኔ ወንድሞቸ ናቸው። ብዙዎቹ የፋኖ አመራሮች የቅርብ ጓደኞቸ ናቸው። እነዚህ ልጆች ከዚህ እንዲደርሱ ብዙ ጥረት ተደርጓል። ብዙ ኢንቨስት ተደርጎባቸዋል። ስለሆነም በአጉል ቅስቀሳ ከወንድሞቻቸው ጋር ጦር እንዲማዘዙ እና እንዲባክኑ አንሻም። የእውነተኛው ውጊያ ሲመጣ አብረን እንሰለፋለን። ፋኖ አጋዬ የሚመራው ጦር ጀኔራል ማርዬ ከሚመራው የመከላከያ ሰራዊት ጋር፣ ፋኖ ባዬ ቀናሁ የሚመራው ፋኖ ጀኔራል ሃብታሙ ከሚመራው መከላከያ ሰራዊት ጋር ወዘተረፈ… የእርስ በርስ ውጊያ እንዲከፍት በግሌ አልሻም። የአማራን ህዝብ ነጻ ለማውጣት ውጊያ የግድ ሲል ጀኔራል ማርዬም፣ ፋኖ አጋዬም፣ ጀኔራል ሃብታሙም (ጀኔራል ሃብታሙ እያልኩኝ የምገልፀው አንተን አይደለም፣ ደፋር ስለሆንክ ጀኔራል ነኝ ብለህ እንዳትመጣ ብቻ) እኔም እንደ ትናንቱ ሁሉ በአንድነት እንሰለፋለን። እርግጠኛ ሆኘ የምነግርህ ያኔ አንተ ከእኛ ጋር አትሰለፍም። ሰልፍህ አማራዊ አይደለምና ከእኛ ጋር ትሰለፍ ዘንድ አይሆንልህም። ይዋጣልን እያላችሁ ከምትቀሰቅሱት ውስጥ አንዳችሁም እንኳን ጦር ግንባር ዝር እንደማትሉ እኛም፣ ፋኖዎችም፣ መከላከያም እናውቃቹሃለን። የማትዋጉትን ጦርነት አትቀስቅሱ ነው ያልናችሁ። በወንድሞቻችን ደም ተራምዳችሁ የምታሳኩት ምንም ዓላማ አይኖርም ነው ያልናችሁ። ወንድሞቻችን ከእናንተ ይልቅ ለእኛ ይቀርባሉ፣ እኛም ለእነሱ እንቀርባለን ነው ያልነው። የደም ነጋዴ መሆናችሁን ገና አልተናገርንም። መናገር ስንጀምር በእርግጠኝነት ትደበቃላችሁ…!

ወያኔ ወረራ ሲፈፅምብን ከጓደኞቸ ጋር ለወራት በዱር በገደል ተንከራተናል። ከቋራ እስከ መተማ፣ ከሁመራ እስከ በረከት፣ ከአዲ ጎሹ እስከ አብደራፊ፣ ከወፍአርግፍ እስከ ደባርቅ፣ ከጠለምት እስከ ጋይንት፣ ከመንዝ እስከ ደሴ፣ ከቦረና እስከ ጋሸና ህዝባችን ለማንቃት ወጥተን ወርደናል። በዚህን ጊዜ እነ ሃብታሙ ይኸ ጦርነት የእናንተ ጦርነት አይደለም አትዋጉ እያሉ “የባንዳነት” ትንተና እየሰጡ ነበር። ከወያኔ አፈቀላጤዎች ጋር በዙም እየተሰበሰቡ ወልቃይትን እንዴት መረከብ እንደሚችሉ ሲያሴሩ ውለው ያድሩ ነበር።

በአንጻሩ የመንግስት ሰዎች ሳይቀር ፈርተው ሚድያውን ሁሉ ሲሸሹት እኛ ከእነ ጌታቸው ረዳ ረጅም ምላስ ጋር ተጋፍጠናል። እነ ሃብትሽ ግን ወያኔ በርቺልን እያሉ በጎን ደግሞ አትዋጉ እያሉ የወገን ተዋጊ ኃይል ያስከዱ ነበር። የምተርከው የብዙ ዓመት እድሜ የቆዬ ጉዳይ ስላልሆነ ህዝቤ በሚገባ ያስታውሰዋል። ይኸ አሳፋሪ ታሪክ ከአንድ ዓመት በፊት የነበረ ታሪክ ነው።

መንግስት በክፍያ እንደሚያሰራን የሚያወራው ሃብታሙ እውነቱን ቢያውቀውም ብልፅግና ግን በቀለጠ ጦርነት ውስጥ ሆነን በቡድን እንኳን አንድ ክላሽ እንዲሰጡን ጠይቀን ፈቃደኛ አልነበሩም። መንግስት ክላሽ ከልክሎናል እናቁም አላልንም። ራሳችንን አደጋ ላይ ጥለንም ቢሆን ትግላችን አላቆምንም። በኋላ በራሳችን መንገድ ነገሩን ፊክስ ብናደርገውም ቅሉ። ይህን ፅሁፍ የሚያነቡ ሰዎች ህያው ምስክሮች ናቸው።

አበው ሲተርቱ “በጅብ ቆዳ የተሰራ ማሲንቆ ቅኝቱ ሁሉ እንብላው እንብላው ነው” ይላሉ። እኔ ወጣቶች ፎረም፣ ወጣቶች ሊግ እያልኩኝ ሳማ በመጨፍጨፍ ቦንቦሊኖ በሻይ እየተመፀወትኩኝ ወጣትነቴን አላባከንኩም። እንደ እድሜ አቻዎቸ ሁሉ በትምህርት ቤት ነው ያሳለፍኩት። እንደ ATM ማሽን በካርድ የሚሰራው ሃብታሙ ሁሉም ሰው ገንዘብ ካልነከሰ በራሱ አስቦ የሚንቀሳቀስ አይመስለውም። ቀደም ብዬ ሰው ሁሉ የልምዱ ውጤት ነው ያልኩት ለዚህ ነው። እውነት ለመናገር የአማራ ምሁራን መማክርት ሆስት ባደረገው እና ከ5000 ያላነሰ ህዝብ በታደመበት ስብሰባ ከአዲስ አበባ ባህር ዳር የአየር ትኬት ቆርጦልኝ ደርሰን ተመልሰናል። የመንግስት ገንዘብ ምን እንደሚመስል ያየሁት ያኔ ብቻ ነው።

ሃብታሙ አያሌው ለጎንደር ያለው ጥላቻ ከወያኔ ነው የሚቀዳው በሚለው ፅሁፌን ልቋጭ። ሃብታሙ የሰሊጥ ብሔርተኞች የምትለውን ቃል ከጌታቸው ረዳ ተቀብሎ ምላሱ ላይ ለብዙ ጊዜ አስቀምጧት ነበር። በእርግጥ ለሰሊጥ መታገል ትንሽ ነገር አይደለም። ለሊጥ የታገሉ አሉና። በተረፈ ባለፈው የምዕራብ ጎንደር ዞን አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ እፈልጋለሁ ባለበት ማስታወቂያ ላይ ሃብታሙ አያሌው ወደ ምዕራብ ጎንደር እንዳትሄዱ ለውትድርና ሊያፍሷችሁ ነው ያለ ቀን ነው ከአለቆቹ የባሰ የጎንደር ጥላቻ ውስጥ እንደገባ የገባኝ። ልብ አድርጉ በዚህ ያልተገባ ቅስቀሳ በዞኑ የነበረ የአንድ ጉልበት ሰራተኛ የቀን ውሎ ከ250 ብር ወደ 500 ብር ሊያድግ ችሏል። ይህ የጉልበት ሰራተኛ ጭማሪ ብዙ በእርሻ ላይ የተሰማሩ ወገኖቻችንን ለኪሳራ ዳርጓል። ይኸ ሰውዬ ነው እንግዲህ ጎንደርን ሞቸ ነው የምወዳት ሊለን የሚዳዳው።

በመጨረሻም የምነርነግርህ ነገር ቢኖር አንድን አካባቢ በጅምላ እየጠሉ እና እያጎሳቆሉ አማራነት የለም። አማራ የሚባለው ከምድር ጫፍ እስከ ጫፍ ያለው ሁሉ ነው። በዚህ ልክ እንዳንነጋገር ከከፍታችን ባታወርዱን ምን አለበት።

አንባቢ ሆይ ፍርድ ትሰጥ ዘንድ ለሃብታሙ የጥላቻ ቅስቀሳ መነሻ የሆነውን ፅሁፍ ኮሜንት መስጫ ላይ አያይዠዋለሁ።

ጋሻው መርሻ = የግል አስተያየት

ከአማራ ፖለቲካ Ethio 360 እና መሰል አወናባጅ የፖለቲካ ጨዋዎችን ማራገፍ ያስፈልጋል። እነዚህ ሰዎች የአማራ ህዝብ ስትራቴጂክ ጥያቄዎች እንዳይደመጡ እና በደራሽ አጀንዳዎች ብቻ ተወስኖ ሲራኮት እንዲውል ሆነ ብለው የሚሰሩ የጠላት ወኪሎች ናቸው። የአማራ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄዎች ሜንስትሪም እንዳይደረጉ እና በዩቱብ ለቅሶ ብቻ ታጥረው እንዲቀሩ ከጠላት ጋር ተናበው የሚሰሩ ለመሆናቸው እስካሁን የመጡበትን የኋላ ታሪክ መፈተሽ የተገባ ነው። የአማራን ህዝብ ሌጅትሜት ጥያቄዎች እንዳይደመጡ ያደረጉት እንደ ኢትዮ 360 ዓይነት ወሬ አመላላሾች ናቸው። አንዳንድ የዋህ የእኛ ሰዎች እርስ በርስ አትጋጩ ይላሉ። እነዚህን ሰርጎ ገቦች መታገል እና ከህዝባችን ላይ እጃቸውን እንዲያነሱ ማድረግ የእርስ በርስ ትግል ሳይሆን የጠላትን አንድ እጅ መቁረጥ ማለት ነው። በእነዚህ ሰዎች ያተገባ ቅስቀሳ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች በሌሎች ብሔረሰቦች ዘንድ በጥርጣሬ ከመታየቱ በተጨማሪ የአማራ ህዝብ ዋና ዋና አሳቢዎችም ትግሉን እየተው እንዲሸሹ ሆኗል። ኢትዮ 360 እና መሰል የጠላት ተላላኪዎችን ከህዝባችን ላይ እናራግፋለን…!

Exit mobile version