Site icon ETHIO12.COM

የጣሪያና ግድግዳ ግብርን በተመለከተ

የጣሪያና ግድግዳ ግብር ማለት መንግስት በሚያለማው መሰረተ ልማት እና የህግ ማሻሻያ ምክንያት በመሬት እና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው ይጨምራል። መሬትና መሬት ነክ ንብረቶች እሴታቸው በመጨመሩ ምክኒያት የአከባቢ መንግስታት የሚሰበስቡት ገቢ የቤት ግብር ወይንም የጣራና ግድግዳ ግብር በመባል ይታወቃል፡፡

የጣሪያና ግድግዳ ግብር ጥቅም:-

1. ከተሞች ከጣሪያና ግድግዳ ግብር የሚሰበስቡት ገቢ መሰረቱ የተረጋጋና አስተማማኝ የገቢ ምንጭ በመሆኑ፣

2. የማይለዋወጥና የማይሰወር የግብር አይነት መሆኑ፣

3. ለቁጥጥር አመቺና ከታክስ ለመሸሽ የማይመች የግብር መሰረት መሆኑ፣

4. ይህ ግብር ለከተሞች የመሰረተ ልማት እድገት የጀርባ አጥንት እንደሆነ የሚነገርለት ከተማ ተኮር ግብር መሆኑ፣

5. ለከተሞች መሰረታዊ የመሰረተ ልማት ችግሮችን ፍላጎት የሚያሟላ መሆኑ

6. ከፋዮች በከፈሉት ልክ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያደርግ መሆኑ፣

የሌሎች አገሮች ተሞክሮ:-

የጣሪያና ግድግዳ ግብር (የቤት ግብር) በሃገራችን ባሉ የክልል ዋና ከተሞችን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን አገራት ለብዙ ዓመታት እየተተገበረ ያለ የግብር አይነት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ባሉ ሃዠአገሮች ያሉ ከተሞች የጣሪያና ግድግዳ ግብር ከአጠቃላይ ገቢ ያለው ድርሻ ሲታይ:-

– በፔሩ – የሊማ ከተማ ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 57.5%

– በፊሊፒንስ-ማኔላ ከተማ የንብረት ግብር ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 59.2%፣

– በዛምቢያ – ሉሳካ ከተማ የንብረት ግብር ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 74.6%፣

– በኮሎምቢያ – ቦጎታ ከተማ የንብረት ግብር ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 57.5 %፣ በቱኒዚያ-ቱኒስ ከተማ የንብረት ግብር ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 57.1%፣

– በኬኒያ- ናይሮቢ ከተማ የንብረት ግብር ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 20% ሲሆን፣

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የቤት ግብር ከአጠቃላይ ግብር ገቢ ያለው ድርሻ 0.08% እንደሆነ ያሳያል:: ይህም ከሌሎች ከተሞች ጋር ሲነጻጸር እጅግ በጣም ዝቅተኛ እና እዚህ ግባ የማይባል እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

የጣራና ግድግዳ ግብር በአገራችን በህግ በተደገፈ በዘመናዊ መልኩ መተግበር የጀመረው በ1937 ዓ.ም ነው:: በመጀመሪያው በከተማ ውስጥ የንብረት ግብር ይጣል የነበረው በማናቸውም የማይንቀሳቀስ ንብረት በመሬትና በህንፃዎች ላይ ነበር::

ከዚህም በተጨማሪ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ህገመንግስት አንቀጽ 49 መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስልጣን ይዘት እና ወሰን ለመደንገግ በወጣው የፌደራል ቻርተር አዋጅ 361/1995 መሰረት በከተማው ውስጥ የከተማ ቦታ ኪራይ ና የቤት ግብር ይወስናል ይሰበስባል ይላል::

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኝ 1,020,528 መኖሪያ ቤት ውስጥ 891,628 የግል ቤቶች ናቸው። ከዚህ ውስጥ ግብር እየከፈሉ ያሉት 182,842 ባለይዞታዎች ብቻ ናቸው፡፡ በዚህም የከፋዮች ቁጥር ብቻ ሳይሆን የሚሰበሰበውም ገቢ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ይህም ከተማው ከዘርፉ ሊያገኘው የሚገባውን ትልቅ ገቢ አሳጥቶት ቆይቷል::

የክፍያ ጫናውን ለማቅለል ሲባል የዚህ ዓመት ክፍያ ያልከፈሉ የቤት ግብር ከፋዮች በጥናቱ በተለየው የአንድ ሜትር ካሬ የቤት ስፋት ወርሀዊ ኪራይ ግምት ወይም ዓመታዊ የኪራይ ግምት መጠንን ለመኖሪያ ቤት በ50% እና ለመሥሪያ ቤት ደግሞ በ75% ላይ ብቻ ግብሩን በማስላት እንዲከፍሉ ይደረጋል::

አዲስ አበባ አስተዳደር

Exit mobile version