Site icon ETHIO12.COM

ምዝበራ የጎላባቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ይፋ ሆኑ፤ 4 ቢሊዮን ብር ያህል ባክኗል

– የጎላ ችግር ካለባቸው ውስጥ የፌደራል ስነምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን፣ የፌደራል ፖሊስና የኢንፎርሜሽንና መረብ ደኅንነት አገልግሎት ይገኝበታል

የፌደራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት ዳምጤ የ2014 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲትን በተመለከተ ተቋማቸው ያካሄደውን የኦዲት ሪፖርት፣ ማክሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

ለፓርላማው የቀረበው የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ሪፖርት እንደሚያመለክተው፣ የ2014 ዓ.ም. በጀት አፈጻጸምን በተመለከተ በተደረገው የኦዲት ሥራ ስድስት ተቋማት አስተያየት ለመስጠት ያልተቻለባቸው ሲሆኑ፣ 19 ተቋማት ደግሞ የጎላ ችግር ያላባቸው ሆነው በመገኘታቸው ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል፡፡

ሒሳባቸው የጎላ ችግር ያለበት በመሆኑ ተቀባይነት የሚያሳጣ አስተያየት ከተሰጠባቸው ተቋማት መካከል

የፌዴራል ዋና ኦዲተር አስተያየት ለመስጠት አልቻልኩባቸውም ካላቸው ተቋማት መካከል

ከአንድ ዓመት እስከ ስድስት ዓመት ዕድሜ ያለውና ለመንግሥት ገቢ መደረግ የነበረበት 13.4 ቢሊዮን ብር ውዝፍ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ዕዳ መኖሩ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የተሟላ ወጪ ሳይቀርብ በወጪ መዝግበው የተገኙ መሥሪያ ቤቶች

በሌላ በኩል ከደንብና ከመመርያ ውጪ ያላግባብ ክፍያ ከፈጸሙ ተቋማት መካከል

የግዥን ሕግ የጣሰ ክፍያ 592.4 ሚሊዮን ብር

የመንግሥት የግዥ አዋጅ ደንብና መመርያ ያልተከተሉ ግዥዎችን የፈጸሙ 82 ተቋማት በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን፣ ከእነዚህ መሥሪያ ቤቶች የተገኘው የግዥን ሕግ የጣሰ ክፍያ 592.4 ሚሊዮን ብር ነው፡፡ ተቋማቱ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሠረት በተከፋይ ሒሳብ ተመዝግበው የተገኙ ነገር ግን ዝርዝር ማስረጃ ባለማቅረቡ የሒሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ እንዳልቻለ ያቀረቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ተቋማት መካከል

ከተደለደለላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶችም በሪፖርቱ የተጠቀሱ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በ2014 ዓ.ም የተፈቀደላቸውን በጀት መጠቀም ሲገባቸው ባለመጠቀማቸው የተገኘው አጠቃላይ ገንዘብ 35 ቢሊዮን ብር መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

በጀት ሥራ ላይ ካላዋሉ መሥሪያ ቤቶች

ዋና ኦዲተሯ በጀት ተከፈቀደ በኋላ አለመጠቀም የታቀዱ ሥራዎች ሳይከናወኑ ሊቀሩ ስለሚችሉና ተቋማትም ዓላማቸውን እንዳያሳኩ ስለሚያደርጋቸው፣ የበጀት ዝግጅትና የአጠቃቀም ጥንቃቄ እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡

የተሽከርካሪ አጠቃቀምና አያያዝን በተመለከተ በሚያብራራው የኦዲት ሪፖርት በመንግሥት ተቋማት ውስጥ

የኦዲት ሪፖርቱ ከተሰጠ በኋላ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፓርላማ አባል አቶ ሙሉቀን አሰፋ፣ ‹‹በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አስተባባሪነት በሚመሩ የሜጋ ፕሮጀክቶች ጉዳይ የገንዘብ አሰባሰብና አወጣጥን በተመለከተ የመንግሥት የፋይናንስን አዋጅ ደንብና መመርያ ተከትሎ እየተሠራ ስለመሆኑ ኦዲት አድርጋችሁ ከሆነ የኦዲት ሪፖርቱ ቢገለጽልን፣ ካላደረጋችሁ ደግሞ ኦዲት ላለማድረግ ምክንያታችሁ ምንድነው?›› በማለት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተሯ ወ/ሮ መሠረት ለተነሳው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ ‹‹ኦዲት ኣላደረግንም፣ ያላደረግንበት ምክንያት ምንድነው? የፌደራል ዋና ኦዲተር ተግባርና ኃላፊነት የመጀመሪያው በተከበረው ምክር ቤት የፀደቀውን በጀት የክዋኔ ኦዲት ማድረግ፤›› ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪ ደግሞ የመንግሥት ተቋማትም ይሁኑ የልማት ድርጅቶች በአዋጅ በተሰጣቸው ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት የክዋኔ ኦዲት እንደሚደረግና ሪፖርት እንደሚቀርብ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ስለዚህ ቅድሚያ በተሰጠን ሥልጣንና ኃላፊነት መሠረት እንሄዳለን፡፡ አሁንም ግን እነዚህን ፕሮጀክቶች በተመለከተ የተመዘበረና የጠፋ ነገር ካለ በኦዲት የሚታለፍ ተቋም ስለሌለ፣ የፕሮጀክቶቹ ስምና የጎደለው ገንዘብ በግልጽ ከቀረበልን ለማየት ዝግጁ ነን፤›› ብለዋል፡፡ (ሪፖርተር)

በተዘጋው የበጀት ዓመት የባከነው ገንዘብ ይህም ማለት የተሟላ ወጪ ሳይቀርብ በወጪ የተመገበው፤ ከደንብና ከመመርያ ውጪ ያላግባብ ክፍያ የተፈጸመው፤ የግዥን ሕግ የጣሰው ክፍያ፤ የሒሳቡን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ ያልተቻለበት እና ከተደለደለላቸው በጀት በላይ የተጠቀሙ መሥሪያ ቤቶች በአጠቃላይ የባከነው ብር 3 ቢሊዮን 841 ሚሊዮን ብር ነው።

ከሁሉ የሚያስደንቀው ሒሳባቸው የጎላ ችግር ያለባቸው ተብለው ከተጠቀሱት መሥሪያ ቤቶች በቀዳሚነት የተጠቀሰው የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሆኑ ነው። መሥሪያ ቤቱ የድርጅቱ መፈክር አድርጎ የሚጠቀመው “ከሙስና የጸዳች ኢትዮጵያ” የሚል መሆኑ ይታወቃል።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Exit mobile version