ሀምሌ 10/2013 (ኢዜአ) ጨፌ ኦሮሚያ በክልሉ የፍትህ ተደራሽነትና ትክክለኝነትን ለማረጋገጥ ያግዛል ላለው የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ምስረታ እውቅና የሚሰጥ አዋጅ አጸደቀ።
ጨፌው የ2014 የክልሉ በጀት 124 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አጽድቋል።
ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደው የሚገኘው 14ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀኑ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ምስረታ እውቅና የሚሰጥ አዋጅን ማጽደቅን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ ከቀበሌ ጀምሮ የሚመሰረትና የክልሉ ሕዝብ በቀደመው ባህሉና ወጉ መሰረት ፍትህ እንዲያገኝ ያግዛል ነው ተብሏል።
ፍርድ ቤቶቹ በተለይ በመደበኛ ፍርድ ቤቶች በፍትህ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ፈተና የሆነውን ሀሰተኛ ምስክርነት ለመቀነስ እንደሚረዳም ተገልጿል። በዋናነት የክልሉ ሕዝብ የቀደመ ባህላዊ የፍትህ አሰጣጥ ሂደትን ተከትሎ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን ለመፍታት ያስችላልም ተብሏል።
ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት የህግ ተመራማሪው አቶ ሚልኪ መኩሪያ እንደሚሉት ፍርድ ቤቶቹ የፍትህ ተዳራሽነትን የበለጠ ያጠናክራሉ። ከዚህ በፊት በአብዛኛው የክልሉ ነዋሪዎች ፍትህ ለማግኘት ረጅም ጉዞ በማድረግ ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረጉ ነበር ነው ያሉት።
በአዋጁ መሰረት የሚቋቋሙ ፍርድ ቤቶች የክልሉ ሕዝብ ፍትህን በቅርበትና በእውነት ላይ ተመስርቶ እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል። ፍርድ ቤቶቹ የመጀመሪያና በፍርድ ሂደቱ ያልረካው አካል አቤት የሚለበት ሁለተኛ እርከን ፍርድ ቤት እንዲኖረው ሆኖ እንደሚደራጅም ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈ ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ አምስት አባላት ያሉትና አባላቱም ለስምንት አመታት የሚያገለግሉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። እነዚህ ፍርድ ቤቶች ከመደበኛና ከማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ጎን ለጎን የሚሰሩ ሲሆን ለክልሉ ህዝብ ትልቅ ጥቅም የሚሰጡ እንደሆነም ገልጸዋል።
በዚሁ መሰረት አዋጁ በጨፌው አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል። በተመሳሳይ ጨፌው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ከተወያየበት በኋላ ሪፖርቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የኦሮሚያ ክልል የአስር ዓመት እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጎ እቅዱን አጽድቆታል። በመጨረሻም የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉን ኦዲተር ጀነራል እቅድ አፈጻጸም፣ የ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት እንዲሁም የ2014 ዓ.ም በጀት ላይ ውይይት በማድረግ አጽድቆታል።
በዚህም የክልሉ የ2014 በጀት 124 ቢሊዮን ብር ለካፒታልና ለተለያዩ ወጪዎች እንዲውል አጽድቋል። በጀቱ 19 ቢሊዮን ብር ለተለያዩ ወጪዎች፣ 29 ቢሊዮን ለካፒታል በጀትና 73 ቢሊዮን ብር ለወረዳዎችና ለከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እንዲሁም 600 ሚሊዮን ብር ለተጠባባቂ በጀት ተይዟል።
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን ህብረቱ አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁመግቢያ ሽግግር ፍትህ ጉልህ የመብት ጥሰቶች በተፈፀመባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን እና ተበዳዮችን ለመካስ ጥቅም ላይ ሲውል ቆይቷል፡፡ በሀገራችንም የሽግግር ፍትህ አስፈላጊነት ታምኖበት ፖሊሲ ሲዘጋጅ… Read more: ዋና ዋና የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ይዘቶች – ሲጨመቁ