ETHIO12.COM

ለመንግስት ሁሉ አቀፍ የሰላም አሳብ ቀረበለት፤ የእርቅ ኮሚሽን በመጪው ዓመት ህገ መንግስት እስከመቀየር የሚያደርሰውን ስራ ይጀምራል

ስማቸውን ካሰራጩት ደብዳቤ ግርጌ የዘረዘሩ ሰላሳ አምስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በመጪው አዲስ ዓመት የ”ሰላም ጥሪ ” ሲሉ ባሰራጩት ጽሁፍ መንግስት ሁሉን አቀፍ መድረክ እንዲያመቻች ጠየቁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን ሲያሰባስብ የቆየውን ግብአት አደራጅቶ በመጪ አዲስ ዓመት ሁሉ አቀፍ የዕርቅ ማድረክ እንዲያዘጋጅ ማስታወቁን ተከትሎ የቀረበው ጥሪ ነው።

በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ እንዲታዩ ዕቅድ ተይዞባቸው ከአራት ወረዳዎች፣ እንዲሁም በውልቃይት ጠገዴ ባለው የባልቤትነት ጥያቄ የተነሳ ከሃሜት ለመዳን ካለመከናወኑ በቀር በመላው አገሪቱ ግብዓት በመስብሰብ የትነተና ስራ ብቻ እንደቀረ ባለፈው ሳምት ኮሚቴው ማስታወቁ ይታወሳል። እርቅን ከፍትህ ጋር አስተሳስሮ አገሪቱን በየጊዜው ለውዝግብና እልቂት የሚዳርገውን ትርክት ለመቋጨት የተቋቋመው ኮሚሽን የተጋብር ስራውን በአዲሱ ዓመት ማግስት እንደሚያስጀምር የሚታወስ ነው።

ተጠያቂነትን ለማስፈን ፍትህ ሚኒስቴር

ኮሚቴው ” ለዘላቂ ሰላምና ለአገረ መንግስት ግንባታ የራሳቸዉ መሰረታዊ አስተዋፅኦ እንዳላቸዉና የሽግግር ፍትህ ዋነኛዉ ትኩረት ተፈፀሙ የሚባሉ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ መሆኑንና በእነዚህ ሂደቶች ክስ የሚኖር መሆኑን በመግለፅ በአገራዊ ምክክር ላይ ግን በአብዛኛዉ ክስ የሌለ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል ሲሉ ከተቋማዊ አደረጃጀት አነፃርም የሽግግር ፍትህ በሁለት አይነት እንደሚደራጀና እነዚህም እዉነት ኮሚሽንና ፍርድ ቤት ላይ የሚተገበሩ ሲሆን አገራዊ ምክክር በአገራዊ ምክክር ኮሚቴ መሰል ቡድኖች እንደሚደራጅና በጥቅሉ አገራዊ ምክክር በሽግግር ፍትህ አማራጮች እንደ አንድ አማራጭ መካተቱንም አያይዘዉ አዉስተዋል” ሲል በጋዜጣ መግለጫው ወቅት መናገሩን ፍትህ ሚኒስቴር በገጹ አመልክቷል።

እነዚሁ ድርጅቶች ላቀረቡት ጥሪ የመንግስት ምላሽ ለጊዜው አልታወቀም። በኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም እንዲሰፍን መናፈቅ የእለት ተዕለት ስራው ሆኗል። የዚያኑ መጠን ሚዲያዎችና ማህበራዊ አውዶች ምንጩ ከማይታወቅ መረጃ በተጨማሪ በተቀነባበረና በተናበበ የፈጥራ ዜና የአገሪቱን ሰላም በስፋት እያወኩ እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው።

ድርጅቶቹ የጥላቻ ንግግርና የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት እንዲቆም፣ ህዝብን በጅምላ መፈረጅ አግባብ እንዳልሆነ ጨምርው ካነሱዋቸው አሳቦች በተጨማሪ በዋናነት ያነሷቸውን አሳቦች ከስር የመለከቱ። መግለጫቸውንም ያንብቡ።

ድርጅቶቹ በአሳብ ተመሳሳይ ይዘት ይዞ በስፋት ሲሰራ ከቆየው ከአገር አቀፍ የምክክር መድረክ በተለየ አዲስ የምክክር መድረክ እንዲመቻች የጠየቁበትን ምክንያት ይፋ አላደረጉም። ድርጅቶቹ አብዛኞቹ በስም መኖራቸው ጭምር የማይታወቅና ቀደም ሲል ተዘግተው ወይም በህግ ገለልተኛ አይደላችሁም በሚል በር የተዘጋባቸውና ከለውጡ በሁዋላ ህልውናቸውን ዳግም የገኙ ድርጅቶች ናቸው። ዛሬ የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ከላይ ያንብቡ።


Exit mobile version