ለመንግስት ሁሉ አቀፍ የሰላም አሳብ ቀረበለት፤ የእርቅ ኮሚሽን በመጪው ዓመት ህገ መንግስት እስከመቀየር የሚያደርሰውን ስራ ይጀምራል

ስማቸውን ካሰራጩት ደብዳቤ ግርጌ የዘረዘሩ ሰላሳ አምስት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በመጪው አዲስ ዓመት የ”ሰላም ጥሪ ” ሲሉ ባሰራጩት ጽሁፍ መንግስት ሁሉን አቀፍ መድረክ እንዲያመቻች ጠየቁ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ እርቅ ኮሚሽን ሲያሰባስብ የቆየውን ግብአት አደራጅቶ በመጪ አዲስ ዓመት ሁሉ አቀፍ የዕርቅ ማድረክ እንዲያዘጋጅ ማስታወቁን ተከትሎ የቀረበው ጥሪ ነው።

በሽግግር ፍትህ ፖሊሲ እንዲታዩ ዕቅድ ተይዞባቸው ከአራት ወረዳዎች፣ እንዲሁም በውልቃይት ጠገዴ ባለው የባልቤትነት ጥያቄ የተነሳ ከሃሜት ለመዳን ካለመከናወኑ በቀር በመላው አገሪቱ ግብዓት በመስብሰብ የትነተና ስራ ብቻ እንደቀረ ባለፈው ሳምት ኮሚቴው ማስታወቁ ይታወሳል። እርቅን ከፍትህ ጋር አስተሳስሮ አገሪቱን በየጊዜው ለውዝግብና እልቂት የሚዳርገውን ትርክት ለመቋጨት የተቋቋመው ኮሚሽን የተጋብር ስራውን በአዲሱ ዓመት ማግስት እንደሚያስጀምር የሚታወስ ነው።

ተጠያቂነትን ለማስፈን ፍትህ ሚኒስቴር

ኮሚቴው ” ለዘላቂ ሰላምና ለአገረ መንግስት ግንባታ የራሳቸዉ መሰረታዊ አስተዋፅኦ እንዳላቸዉና የሽግግር ፍትህ ዋነኛዉ ትኩረት ተፈፀሙ የሚባሉ ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ላይ መሆኑንና በእነዚህ ሂደቶች ክስ የሚኖር መሆኑን በመግለፅ በአገራዊ ምክክር ላይ ግን በአብዛኛዉ ክስ የሌለ መሆኑ ልዩ ያደርጋቸዋል ሲሉ ከተቋማዊ አደረጃጀት አነፃርም የሽግግር ፍትህ በሁለት አይነት እንደሚደራጀና እነዚህም እዉነት ኮሚሽንና ፍርድ ቤት ላይ የሚተገበሩ ሲሆን አገራዊ ምክክር በአገራዊ ምክክር ኮሚቴ መሰል ቡድኖች እንደሚደራጅና በጥቅሉ አገራዊ ምክክር በሽግግር ፍትህ አማራጮች እንደ አንድ አማራጭ መካተቱንም አያይዘዉ አዉስተዋል” ሲል በጋዜጣ መግለጫው ወቅት መናገሩን ፍትህ ሚኒስቴር በገጹ አመልክቷል።

እነዚሁ ድርጅቶች ላቀረቡት ጥሪ የመንግስት ምላሽ ለጊዜው አልታወቀም። በኢትዮጵያ ህዝብ ሰላም እንዲሰፍን መናፈቅ የእለት ተዕለት ስራው ሆኗል። የዚያኑ መጠን ሚዲያዎችና ማህበራዊ አውዶች ምንጩ ከማይታወቅ መረጃ በተጨማሪ በተቀነባበረና በተናበበ የፈጥራ ዜና የአገሪቱን ሰላም በስፋት እያወኩ እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተገለጸ ነው።

ድርጅቶቹ የጥላቻ ንግግርና የተዛቡ መረጃዎችን ማሰራጨት እንዲቆም፣ ህዝብን በጅምላ መፈረጅ አግባብ እንዳልሆነ ጨምርው ካነሱዋቸው አሳቦች በተጨማሪ በዋናነት ያነሷቸውን አሳቦች ከስር የመለከቱ። መግለጫቸውንም ያንብቡ።

 • አገር አቀፍ የሰላም መድረክ ይመቻች
 • ገለልተኛ ምርመራና ተጠያቂነት ይስፈን
 • ፆታዊ ጥቃቶች ተገቢው ትኩረት ይሰጣቸው
 • የተጋላጭ እና ግፉአን ጥበቃ ማዕቀፍ ይዘርጋ
 • ሕዝባዊ ተሳትፎ ይረጋገጥ
 • የቅድመ ግጭት መጠቆሚያ እና መከላከያ ስርዓት (Early warning System) ይኑር
 • የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ሳይስተጓጎል ይቀጥል
 • የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት ይቁም
 • የሲቪክ ምኅዳሩ ጥበቃ ይደረግለት
 • ባለድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን ይወጡ ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ጥሪያቸውን ዛሬ በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል በሰጡት መግለጫም አመልክተዋል።
See also  ብልጽግና አዲስ አበባ አበራ፤ ባልደራስ ተከትሏል

ድርጅቶቹ በአሳብ ተመሳሳይ ይዘት ይዞ በስፋት ሲሰራ ከቆየው ከአገር አቀፍ የምክክር መድረክ በተለየ አዲስ የምክክር መድረክ እንዲመቻች የጠየቁበትን ምክንያት ይፋ አላደረጉም። ድርጅቶቹ አብዛኞቹ በስም መኖራቸው ጭምር የማይታወቅና ቀደም ሲል ተዘግተው ወይም በህግ ገለልተኛ አይደላችሁም በሚል በር የተዘጋባቸውና ከለውጡ በሁዋላ ህልውናቸውን ዳግም የገኙ ድርጅቶች ናቸው። ዛሬ የተሰጠውን ሙሉ መግለጫ ከላይ ያንብቡ።


 • የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበር
  በማራቶን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሻል እጅግ የሚደነቅና ያልተለመደ ነው። ባለሙያዎቹ ወይም አሰልጣኞቹ የሮጠችበትን ፍጥነት በሰዓትና ርቀት ከፋፍለው ቢያቀርቡት ምን አልባትም ወንዶችን የሚገዳደር ፍጥነት ተጠቅማ ሮጣለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቴክኒክ ዳይሬክተርና የአትሌቶች ኮሚሽን ሰብሳቢ የነበሩት የዛሬው የተከበሩ ዱቤ ጅሎ አይነቱን ሯጮችን አዝረክርኮ ማሸነፍ የሚያስችላትን ሃይል አሳይታለች። የበርሊና ባለ ማዕረግ ትዕግስት!! ተግስት … Read moreContinue Reading
 • ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል
  “ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም ያለው እዚህ ነው። ለሰራተኞች እንደ ቤተሰብ ዝግጅት አድርገናል። ኑ” ሲሉ የተሰሙት አምስት መቶና ሶስት መቶ ሄክታር ሰሊጥና ማሽላ ያመረቱ ባለሃብቶች ናቸው። የዞኑ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እንዳሉት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ስለሚጠበቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሰራተኛ ሃይል ያስፈልጋል። የዞኑ አርባ … Read moreContinue Reading
 • የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር
  “ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ መረጃ በሰጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ አየር ማረፊያውን ሆን ብለው እንዳልያዙ አመልክተዋል። እሳቸው ተናገሩ የተባለው በጀርመን ድምጽ እየተሰማ በለበት ሰዓት በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውጊያ መደረጉን ሳያስተባብል ከተማዋን ለመያዝ የገባው ሃይል መደምሰሱን አሃዝ ጠቅሶ አመልክቷል። አገር መከላከያም … Read moreContinue Reading
 • “የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”
  የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ) የሚለው የቆየ ተረት ልብን የሚያደማ ኩነትን ማሳያ ነው። እቺ መከረኛ ሚስት ባልዋ በእናቷ ልጅ ወንድሟ ተገደለ። ሟች ባል፣ ገዳይ ወንድም … ኢህአፓ “ሃይማኖት ነው” በሚል ሲገልጸው በነበረው ትግል በቀይና ነጭ ሽብር ስም እናቶች የወላድ መካን ሆነዋል። ጧሪ ያጡና ባዶ ቤት ሃዘን … Read moreContinue Reading
 • በአማራ ክልል የተነሳው ጦርነት በሰላም ሊቆጭ እንደሚችል ተሰማ
  በአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የሚቋጭበት አግባብ ተስፋ ሰጪ ደረጃ መድረሱ ተሰማ። የኢትዮ12 የዜና አቀባዮች እንዳሉት ሰላም ወደድ የሆኑ ዜጎች ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያደረጉ ያለው ጥረት ውጤታም እየሆነ መሆኑንን ነው ያመለከቱት። በሰላም ጥረቱ ውስጥ የሚሳተፉትን ወገኖችና የሰላም ንግግር አመቻች የሆኑትን ክፍሎች ሳይጠቅሱ የዜናው ሰዎች እንዳሉት ጥረቱ ብዙ መንገድ … Read moreContinue Reading

Leave a Reply