በመጪው አዲስ ዓመት ሰላም፣ እርቅና አብሮነት እንዲጎለብት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ፡፡
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ብሔራዊ የጸሎት መርሐ ግብር በወዳጅነት አደባባይ አካሂዷል፡፡ የጸሎት መርሐ ግብሩ አዲሱን 2016 ዓመተ ምህረት በይቅርታና በእርቅ መቀበልን ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ጉባኤው የጳጉሜን ቀናትን የጸሎትና ንስሐ መርሐ ግብር በማውጣት ቤተ እምነቶች ለሀገር ሰላምና አንድነት እንዲጸልዩ ማውጁ ይታወቃል። በዛሬው ዕለትም የጸሎት መርሐ ግብሩ ማጠቃለያ የተካሄደ ሲሆን፤ በስነ-ስርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶችን፣ የመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የጸሎት መርሃ ግብሩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሐፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ ኢትዮጵያ ዘመናትን ተሻግራ በጽናት የቆየችው በሕዝቧቿ መካከል ባለው ጠንካራ አንድነትና አብሮነት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አንዳንድ አካላት ይህን የሕዝቦች ትስስር ለመሸርሸር የሃሰት ትርክቶች እንደሚያሰራጩም ጠቅሰዋል፡፡ በመሆኑም በመጪው አዲስ ዓመት ሰላም፣ እርቅና አብሮነት እንዲጎለብት ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና ሊወጣ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አገር የሚገነባው በትውልድ ቅብብሎሽ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከዚህ አኳያ የኃይማኖት ተቋማት በስነ ምግባር የታነጸ ዜጋ በማፍራት ረገድ የጀመሩትን ሰራ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይት መፍታት አንደሚገባም እንዲሁ፡፡ አዲሱ ዓመት የሰላም የእርቅና አብሮነት እንዲሆን የኃይማኖት አባቶች በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች
- የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋልየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከንግድ ባንክ 300 ቢሊዮን ብር ዕዳ እንዳለበት ተገለጸ። የዕዳ ጫናውን ለማቃለል የባንክ ወልዱም ጭምር ተፅእኖ እያሳደረ መሆኑም ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል… Read more: የኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ኃይል 300 ቢሊዮን ብር የንግድ ባንክ ዕዳ አለብኝ አለ፤ ዕዳውና የክፍያው ጫና እንደከበደውም አስታውቋል
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ አስታወቁ። “ቅጥፈት ነው” ያሉትና በፕሬዚዳንቱ ስምና ፊርማ የተሰራጨው ደብዳቤ የሚሊሻ ሃይሉ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ ሰጥተዋል። በተለይም በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሮማናት አደባባይ ላይ የተለመደው አይነት… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን