Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ የሠመመን መድሃኒት ሰጪ ባለሙያዎች ቁጥር ከ200 አይልቅም

በ80 መቶ የሚሆኑ የካንሰር ታማሚዎች የአኔስቴዢያን ባለሞያዎች ቢያስፈልጋቸውም በሃገሪቱ 200 የ ሰመመን መድሃኒት ሰጪ ባለሙያዎች ብቻ መኖራቸው ተገልፃል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ World Anesthesia Day ወይም /ዓለም አቀፍ የሰመመን ቀን/ በኢትዮጲያ ጥቅምት 7 ይከበራል፡፡

“የማህበረሰብ ግንዛቤ በአንስቴዢያ ምን መምሰል አለበት” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጲያ ጥቅምት 7 እንደሚከበር ኢትዮ ኤፍኤም ሰምቷል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ World Anesthesia Day (የሰመመን ቀን) ለ177 ጊዜ “የአንስቴዢያ እና ካንሰር ህክምና” በሚል መሪ ቃል ቀኑ ታስቦ ይውላል፡፡

በዛሬው እለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአኔስቴዢያን ባለሙያዎችን በተመለከተ ሰፋ ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ሊከናወኑ እንደሚገባ ተመካልቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም


Exit mobile version