Site icon ETHIO12.COM

በኢትዮጵያ ፣በግብጽና በሱዳን መካከል በካይሮ ሲካሔድ የቆየው 3ኛው ዙር ድርድር ተጠናቀቀ

በግብጽ ካይሮ ሲካሔድ የቆየው ሶስተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት እና አለቃቀቅ ደንቦች እና መመሪያዎች የሶስትዮሽ ድርድር ተጠናቀቀ።

ለሁለት ቀናት በተካሔደው መድረክ የሶስቱ ሃገራት ተወካዮች ጠንካራ ድርድር ማድረጋቸው ተገልጿል።

በድርድሩ ላይ በኢትዮጵያ በኩል በሚኒስትር ማዕረግ ዋና ተደራዳሪ በአምባሳደር ስለሺ በቀለ ፣ በግብጽ በኩል የውሃ ሃብትና መስኖ ሚኒስትሩ በፕሮፌሰር ሃኒ ሰዊላም እንዲሁም በሱዳን በኩል በተጠባባቂ የመስኖና ውሃ ሃብት ሚኒስትር በዳወልበይት አብደልራህማን የተመሩ አባላት ተሳትፈዋል።

የሶስቱ ሃገራት ተደራዳሪዎች ወደጋራ መግባባት በሚያደርሱ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ተወያይተዋል።

በመጨረሻም ቀጣዩን ዙር ድርድር ለማካሔድም በፈረንጆቹ ወር ዲሴምበር 2023 አዲስ አበባ ላይ ለመገናኘት ተስማምተዋል።

ኢትዮጵያ በአባይ ውሃ አጠቃቀም ላይ ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ስምምነት ላይ ለመድረስ በቁርጠኝነት እንደምትሰራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።


Exit mobile version