Site icon ETHIO12.COM

ኢትዮጵያ በበጋ 3 ሚሊዮን ሄክታር ስንዴ ልታመርት ነው፤ አፋር አንድ ወረዳ ብቻ 8 ሺህ ሔክታር መሬት የበጋ ስንዴ ያመርታል

“ይህ ዜና” አሉ አቶ ወዳጆ ሃይሉ” ይህ ዜና ለኢትዮጵያ ሰበር ዜናዋ ሊሆን ይገባ ነበር” ይህ አስተያየት የተሰጠው በተያዘው ዓመት በበጋ ስንዴ ምርት ሶስት ሚልዮን ሄክታር መሬት እንደሚታረስ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ነው። በዚሁ መሰረት በአፋር ዱብቲ ወረዳ ብቻ ስምንት ሺህ ሄክታር የበጋ ስንዴ የማምረቱ ስራ በይፋ መጀመሩ ይፋ ሆኗል።

ከጥጥ ምርት ውጪ የማያወቅው አፋር አዋሽ ወንዝን ጠልፎ አትክልትና ፍራፍሬ ምርት መጀመሩ አርብቶ አደሩን ህዝብ ተረጋገቶ በአንድ አካባቢ ህይወቱን እንዲመራ ያደርገዋል። ነዋሪነታቸውን አውሮፓ ያደረጉት የግብርና ባለሙያ በላኩት አጭር መልዕክት እንዳሉት፣ ይህ አገሩን ለሚወድ ሁሉ ታላቅ ዜና ነው። በርካታ ችግሮች ቢኖሩም የስንዴን ምርት ለማሳደግ የሚሰሩ ስራዎችንም ማገዝና ማበረታታት ከዜጎች ሁሉ ይጠበቃል።

“አፋርን እጅግ አወደዋለሁ። ህዝቡ እጅግ ቀናና ኢትዮጵያዊ ነው። ይህ ህዝብ አምራች ሆኖ ራሱን በአንድ አካባቢ ለማኖርና በጋራ የመንግስትን አገልግሎት ጤናና ትምህርትን ጨምሮ ለማግኘት መታደሉ አኩርቶኛል” ያሉት አስተያየት ሰጪው፣ ዜናው እጅግ እንዳስደሰታቸው ጠቅሰው አገር የሚወዱ ሁሉ ሊያበረታቱት የሚገባ ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል።

” ሟርትና የሟርት ዜና ነብሳችንን በላው፣ የሞትና ውድመት ዜና አፈዘዘን” ያሉት አቶ ወዳጆ፣ ” ኢትዮጵያዊያን ከሟርት ይልቅ የልማት ዜናን አጉልተው ሊቀባበሉት፣ ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ገንቢ ዜናዎችን ማስቀደም ይገባቸዋል። በሟርት ዜናዎች መልካም ውጤት ማየትና መሻሻል አይገኝም” ሲሉ ምክር ሰዝረዋል።

በርካታ ተስፋ ሰጪ ጉዳዮች መኖራቸውን ያመልከቱት እኚሁ ባለሙያ “ልዩነትና የፖለሪካ ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ ጫና ማሳደር ይገባል። ነገር ግን ሟርትና ሞትን በአገር ላይ በማውጅ እልፍ የሚል ችግር የለም” ሲሉ ሚዛንን መጠበቀ፣ ተስፋን ማጉላት ለአፍታም ቢሆን ሊረሳ እንደማይገባው አመልክልተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን የልማት ሥራዎችን ለመገምገም እና የበጋ ስንዴ ምርት ሥራን ለማስጀመር አፋር ክልል መግባታቸውን ተከትሎ አቶ ወዳጆ በላኩት አጭር ጽሁፍ ሶስት ሚሊዮን ሄክታር የበጋ ስንዴ እንደሚመረት መስማታቸው ማስታወሻውን እንዲጽፉ መነሻ ሆኖላቸዋል።

በዜናው በዱብቲ ወረዳ ብቻ በ8 ሺህ ሔክታር መሬት ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት ዝግጅት ማጠናቀቁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በተያዘው ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በ3 ሚሊየን ሔክታር ላይ የበጋ ስንዴ ለማምረት ዕቅድ ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ግብርና ሚኒስቴር ከቀናት በፊት ማስታወቁ አይዘነጋም። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ይህንኑ ደግምው አስታውቀዋል።

በዋናነት በአርብቶ አደርነት የሚታወቀው እና በግብርና ግብዓቶች የቀዳሚ ድጋፍ መዳረሻ ያልሆነው የአፋር ክልል÷ በአሁኑ ወቅት በሀገር አቀፉ የግብርና ምርታማነት ላይ በስንዴ፣ በጥጥ እና በሙዝ ምርት አስተዋፅዖው እጅግ ከፍ ያለ ደረጃ መደርሱ ተመልክቷል።

አሁን ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የስንዴ ምርት መዛባት፣ የምግብ ምርት ዋጋ መናርና በተለያዩ አካባቢዎች ያለውን የድርቅ ዜና መመከት የሚቻለው ለም አካባቢዎች ላይ በስፋት በማምረትና መስኖ በመጠቀም በመሆኑ መንግስት ለዝግጅት ሶስት ሚሊዮን ሄክታር የበጋ ስንዴ ለማምረት መነሳቱ በሁሉም መስፈርት ድጋፍ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው።

በኢትዮጵያ ከለውጡ በሁዋላ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ትራክተሮች፣ ኮምባይነሮች፣ የውሃ መሳቢያ ሞተሮች፣ የመስኖ ግድቦችና መስለ የምርት ማሳደጊያ መሳሪያዎች ለአርሶ አደሮች እየተበረከተ መሆኑንን ተጠቃሚዎች ይናገራሉ።

በተመሳስይ የግብርና ድጋፍ ዜና ግብርና ሚኒስቴር ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ መኪናዎች እና ሌሎች ቁሶችን ለክልሎች አስረክቧል፡፡

በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ካንትሪ ዳይሬክተር እና የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹ በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡትን ምርጥ ተሞክሮዎች በላቀ ደረጃ ለማስቀጠልና የግብርና ልማት ተግባራትን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማከናወን የሚረዱ ናቸው ተብሏል፡፡

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ÷ ከ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ የተደረገባቸው መኪናዎችና ሞተር ሳይክሎች እንዲሁም ሌሎች የአቅም ግንባታ ድጋፎች ለክልሎች፣ ለወረዳዎችና ለመልካሳ ግብርና ምርምር ማዕከል መበርከታቸውን ተናግረዋል፡፡

ተሽከርካሪዎቹና የስነ-ምግብ ምርምር ላቦራቶሪዎች በየወረዳዎቹና ተቋማቱ የታቀዱትን ተግባራት በወቅቱ በማከናወን ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖራቸው ጠቁመዋል፡፡


Exit mobile version