Site icon ETHIO12.COM

የትግራይ ክልል ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ድንቅ ውጤት አስመዘገቡ፤ ሰባ ከመቶ አለፉ

የትህግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በለኮሰው ጦርነት እጅግ አስቸጋሪ ዓመታትን ያሳለፉት የትግራይ ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 69.9 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዜናው መነጋገሪያ ሆኗል።

ትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው መነጋገሪያ የሆነው በሌሎች ሰላም ባለባቸው አካባባኢዎችና ክልሎች የሚኖሩ ተማሪዎች ያላገኙት ውጤት በትግራይ መመዝገቡ ነው።

ከፍተኛ አድናቆት የተሰጣቸው የትግራይ ክልል ተማሪዎች ፈተናውን ያለፉት ቀደም ሲል በክልሉ በወጉ የተዘረጋው የትምህርት አሰጣጥ ጥሩ መሰረት የጣለ እንደሆነ አንዳንዶች በማህበራዊ ገጾቻቸው እየገለጹ ነው። ያም ሆነ ይህ ትግራይ ካስለፈችው የጦርነት ዓመታት በመውጣት በአጭር ጊዜ የተማሪዎች ዝግጅት ይህ ውጤት መመዘገቡ በርካታ የጥናት መነሻ ሊሆን እንደሚችልም እየተጠቆመ ነው።

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር ዓቀፍ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከመግለጹ ውጪ ስለተማሪዎቹ ትጋትና ልዩ ውጤት ያስታወቀው ነገር የለም።

የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በክልሉ ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዚህም መሠረት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 69 ነጥብ 96 በመቶ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።

ከተመዘገበው ውጤት 657 ከፍተኛው ነጥብ መሆኑንም አመልክተዋል።


Exit mobile version