የትህግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ በለኮሰው ጦርነት እጅግ አስቸጋሪ ዓመታትን ያሳለፉት የትግራይ ተማሪዎች በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 69.9 በመቶ የሚሆኑት ማለፋቸው ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ዜናው መነጋገሪያ ሆኗል።
ትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸው መነጋገሪያ የሆነው በሌሎች ሰላም ባለባቸው አካባባኢዎችና ክልሎች የሚኖሩ ተማሪዎች ያላገኙት ውጤት በትግራይ መመዝገቡ ነው።
ከፍተኛ አድናቆት የተሰጣቸው የትግራይ ክልል ተማሪዎች ፈተናውን ያለፉት ቀደም ሲል በክልሉ በወጉ የተዘረጋው የትምህርት አሰጣጥ ጥሩ መሰረት የጣለ እንደሆነ አንዳንዶች በማህበራዊ ገጾቻቸው እየገለጹ ነው። ያም ሆነ ይህ ትግራይ ካስለፈችው የጦርነት ዓመታት በመውጣት በአጭር ጊዜ የተማሪዎች ዝግጅት ይህ ውጤት መመዘገቡ በርካታ የጥናት መነሻ ሊሆን እንደሚችልም እየተጠቆመ ነው።
በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ሀገር ዓቀፍ ፈተና ከወሰዱት ውስጥ 69 ነጥብ 9 በመቶ የሚሆኑት 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከመግለጹ ውጪ ስለተማሪዎቹ ትጋትና ልዩ ውጤት ያስታወቀው ነገር የለም።
የቢሮው ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፥ በክልሉ ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ የፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን አስታውሰዋል።
በዚህም መሠረት ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 69 ነጥብ 96 በመቶ የሚሆኑት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማምጣታቸውን ገልጸዋል።
ከተመዘገበው ውጤት 657 ከፍተኛው ነጥብ መሆኑንም አመልክተዋል።
- Ethiopia Working To Secure New Development Bank MembershipThe Ministry of Foreign Affairs disclosed that Ethiopia is working hard to become member of BRICS’ New Development Bank. In a media briefing regarding the country’s diplomatic activities over the week, Spokesperson of the Ministry Nebiyu Tedla, indicated that Ethiopian delegation led by State Minister of Foreign Affairs Ambassador Mesganu Arga participated in the consultation… Read more: Ethiopia Working To Secure New Development Bank Membership
- የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”በአላማጣ ከተማ በተለየ መልኩ የትግራይ ክልል ታጣቂዎች በከተማዋ ውስጥ እንደሚንቀሳቀሱ ነዋሪዎች መመስከራቸውን ቢቢሲ አስታወቀ። ይህ የተገለጸው ከአለማጣ እና አካባቢው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከሃምሳ ሺህ በላይ ማሻቀቡ ይፋ እየሆነ ባለበት ወቅት ነው። መንግስት ሰላማዊ ዜጎችን ማህበራዊ ዕረፍት መንሳት አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሶ ” መንግስታዊ ሃላፊነትን መወጣት ፍርሃት አይደለም” ቢልም የትግራይ አመራሮች ሂደቱ ከመንግስት ጋር በተደረገ ስምምነት እየተከናወነ… Read more: የትግራይ ክልል ታጣቂዎች ዳግም ዝርፊያ እያፈጸሙ ነው፤ የተማሪዎች መጽሃፍትን “የአማራ ክልል ናቸው እየሉ ቀደዋል”
- በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነውለዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር 6 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙንna ለዚህም ተግባራዊነት ከሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊየን በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተገለጸ። 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለተከላ ተዘጋጅቷል። More stories የኤርትራ መንግሥት በእስራኤል በተፈጠረው ግጭት ሞሳድ ድጋፍ አድርጓል አለ ፤ ተመድ የኤርትራዊያንን በጅምላ መባረር ነቀፈSeptember 6, 2023 የአሜሪካ ዜጎች አሁኑኑ ዩክሬንን ለቀው እንዲወጡ… Read more: በዘንድሮው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ሰባት ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ችግኝ ልትተክል ነው
- አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠአፍሪካ ህብረት የውጭ ምንዛሬ አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንደሚያዘዋውር ተጠቅሶ በህብረቱ ስም የወጣው ዜና ሃሰት፣ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን መንግስት አስታወቀ። መረጃው ቀድሞውንም ዜናው “ሴራ” ነው በሚል አስተያየት ከሰጡ ወገኖች ጋር የሚስማማ ሆኗል። ቀሲስ በላይ መኮንን አፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢው ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ነገሩ ሲነቃ ከተሰወሩ ግለሰቦች ጋር ተገኝተው በሃሰተኛ ሰነድ 6.5… Read more: አፍሪካ ህብረት ” የውጭ ምንዛሪ ሒሳቡን ወደ ሌላ ሀገር ሊያዘዋውር ነው” የሚለው ዜና ሃሰት መሆኑን አረጋግጠ
- አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎችባንኩ የክፍያ ሰነድ ቀረበለት። ማጣሪያ ጥያቄ ለህብረቱ አቀረበ። ሃሰት ሆኖ ተገኘና ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ያዘ። ጉዳዩ ወደ ህግ አመራ። አሁን ምኑ ነው አፍሪካ ህብረትን ስጋት ላይ ጥሎት አካውንቱን ወደ ሌላ አገር እንዲወስድ ያስገደደው? ከሆነም ህብረቱ ይህን አቋሙን ለምን በይፋ ከማስታወቅ ይታቀባል? ነገሩ በዚህ ደረጃ አሳሳቢ ከሆነ ቢያንስ ሁለት መስመር መግለጫ እንዴት ማውጣት ተሳነው …. ብዙ መወያያ… Read more: አፍሪቃ ህብረት ምን አሰጋውና “ገንዘቤን ወደ ሌላ አገር ለማዛወር እያሰብኩ ነው” ሲል ተንሿከከ፤ የጾምና የፍስክ ዜናዎች