ETHIO12.COM

የድርቅን አደጋን ለፖለቲካ ፍጆታ – የጌታቸው ረዳ መግለጫ ዓላማው ሌላ ነው

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ የፌዴራል መንግሥቱና ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ ለመግታት እጃቸውን እንዲዘረጉ፣ በክልሉ ያለው ድርቅ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱንና ችግሩ ከ1977 በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ እጅግ የከፋ እንደሆነ አድርገው ያሰራጩት መግለጫ ተቀባይነት የሌለውና መሰራታዊ ጭብጡን የሳተ እንደሆነ መንግስት አስታወቀ።

የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ድርቅን ከፖለቲካ ጋር አዋህዶ በህዝብ ስም መጠቀሚያ ማድረግ ነውር እንደሆነ ዝርዝር ዳታ በማቅረብ አመልክተዋል። ድርቁ በተባለው ደረጃ ቢኖር እንኳን በዓለም ዓቀፍ መመዘናዎች መነሻነት ሊያውጅ የሚችለው የፌደራሉ የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤት እንደሆነ ጠቁመዋል።

አቶ ጌታቸው በማህበራዊ ገጻቸው ባሰራጩት ይ”ድረሱልን” ጥሪ “በትግራይ ረሃብ እና ሞት እያንዣበበ ነው” ብለዋል። የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ በበኩላቸው የአደጋ ስጋት ምክር ቤት አራት ዞኖች ላይ የድርቅ ሽግር መኖሩን ይፋ አድርጎ ከየትኛውም ክልልና ተረጂዎች በላይ እርዳታ ወደ ትግራይ መጓጓዙን ቁጥር ጠቅሰው አመልክተዋል።

በታጣቂ ስም በመቶሺህ የሚቆጠሩ ባለሙያዎችን አንድ ቦታ በማሰባሰብ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍጆታ በሚመደብ ሃብት የሚቀልብ የክልል መንግስት፣ ህዝብን አስተባበሮ ወደ ልማትና ስራ ከመግባት ይልቅ በግምገማ ወራት የሚፈጅ አስተዳደር ይህን የማለት ሞራል እንደሌለውና በህዝብ ስም የፖለቲካ አጀንዳ ማቀነቀን እንደማይቻለው ጠቁመዋል።

አቶ ጌታቸው “አጋጣሚውን በመጠቀም ወልቃይትን በሃይል እናስመስል የሚል ቡድን አለ” በሚል ቀደም ሲል በሰጡት መግለጫ ሲጠቁሙ መንግስት ከሰጠው በጀት ላይ ለታጣቂዎች ቀለብ የሚውለውንም ይፋ አድረገው ነበር። “ከ3 ቢሊዮኑ ለሲቪል ሠራተኛው የከፈልነው የአራት ወር ደሞዝ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ለሲቪል ሰራተኛው ሳናወጣ ከ270 ሺህ በላይ ወታደሮችን ምግብ ማቅረብ ስለነበረብን ነው” ሲሉ የክልሉን በጀት እንዴት እንደሚሰራበት ማስታወቃቸው አይዘነጋም። ሙሉውን የአቶ ጌታቸውን የቀደመ መግለጫ ከስር ያንብቡ።


“ከ3 ቢሊዮኑ ለሲቪል ሠራተኛው የከፈልነው የአራት ወር ደሞዝ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ለሲቪል ሰራተኛው ሳናወጣ ከ270 ሺህ በላይ ወታደሮችን ምግብ ማቅረብ ስለነበረብን ነው” ሲሉ አሁንም ትግራይ 270 ሺህ ከክልሉን በጀት የሚቀለብ ሰራዊት እንዳላት ተናግረዋል።

 


እርዳታ ከአጋር ድርጅቶች ጋር ሲሰጥ ዓላማውን እንደሚስት አጠንክረው የተናገሩት ዶክተር ለገሰ ቱሉ ” እርዳታ በተቋረጠ ወቅት ሳይጓደል መንግስት ከየትኛውም ክልል በተሻለ ደረጃ ለትግራይ ሲያቀርብ ነበር” ሲሉ የኋላውን በማስታወስ ተናግረዋል። በትግራይ የርዳታ እህል ከተረጂ ጉሮሮ በመዝረፍ መሸጥ የዕለት ተዕለት ተግባር እንደሆነ ማረጋገጫ ማግኘቱን ጠቅሶ የዓለም አቀፉ የምግብ ድርጅትና የአሜሪካ እርዳታ ድርጅት ድጋፋቸውን አቋርጠው እንደነበር ይታወሳል። በጦርነቱ ወቅት የትህነግ ታጋዮች የርዳታ መጋዘን በመዝረፍና የህጻናትን አልሚ ምግብ ሳይቀር እንደሚጠቀሙ በይፋ በማስረጃ ሲቀርብ ጦርነቱ ከቆመ በሁዋላ በሌብነት አሳበው ድጋፍ ያቆሙት ተቋማት በወቅቱ እንዳልሰማ ሆነው ሲያልፉ እንደነበር የሚታወስ ነው።

ዶክተር ቱሉ በደፈናው እርዳታን ለፖለቲካ ትርፍ ማዋል በሚል አጋሮችን ጠቀስ አድርገው ቢያልፉም አሁን ላይ ሰብዓዊ ድጋፍን በተመለከተ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ድጋፍ አደጋዎች በአማራ፣ ትግራይ፣ አፋርና ሌሎች ክልሎች 3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ዜጎች የድርቅ አደጋ አንዲሁም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዜጎች የጎርፍ አደጋ እደደረሰባቸው ገልጸዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ የትግራይ ክልል መሪ አቶ ጌታቸው እላፊ ሄደዋል።

ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከዓለም አቀፍ ረጂ ተቋማት ጋር በመተባበር 1 ሚሊየን 725 ሺህ ኩንታል ወይም በገንዘብ ሲገመት ከ15 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ የሚሆን ሰብዓዊ እርዳታ መቅረቡንም ዶክተሩ ይፋ አድርገዋል። አቶ ጌታቸው ከ1977 ድርቅ ጋር ያዛመዱት የትግራይ ድርቅ በሰፊ ዳታና መረጃ አላቀረቡትም። ወይም መንግስት በግልና ከአጋር ድርጅቶች ጋር ያቀረበውን እርዳታ መጠን ጠቅሰው የእጥረቱን መጠን አላሳዩም።

መንግሥት ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽ እያደረገመሆኑን ያመለከቱት ዶክተር ለገሰ ፣ ከሰሞኑ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተሰጠው መግለጫ ፈፅሞ የተሳሳተ መሆኑን አመልክተዋል። ይሁን እንጂ ክልሉ በዚህ ደረጃ መንግስትን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ለመንጀል የሄደበትን አግባብና ምክንያት ይፋ አላደረጉም። በደፈናው ግን ድርቅን ለፖለቲካ መተቀሚያ ማድረግ እንደሆነ አመልክተዋል።

“ፖለቲካና ስብዓዊ ድጋፍን ማገናኘት ተገቢነት አይደለም” ሲሉም እርድታን በአገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን አገሪቱ ባላት የውሃና የመሬት ሃብት ሰፊ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንን ገልጸው የትግራይ ክልል ባለሙያዎች ሳይቀሩ በመቶሺህ ሰዎችን አስቀምጦ በህዝብ በጀት ከመቀለብና ለወራት ግምገማ ከመቀመጥ በሌሎች የአገሩቱ ከልሎች እንደሚደረገው ወደ ልማት ርብርብ እንዲደረግ አሳስበዋል። ይህን ከማድረግ ይልቅ በሕዝብ ሽፋን የሚደረግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ተቀባይነት እንደሜለውም አስታውቀዋል።

በየትኛውም ክልል ከሰላም መደፍረስ አኳያ በሰብዓዊ አቅርቦት ላይ መስተጓጎል ተፈጥሮ ካልሆነ በስተቀር በረሃብ ምክንያት የሞተ ሰው አለ የሚል ግምገማ የለም” ሲሉም የኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩ አክለው ገልጸዋል።



Exit mobile version