ቀደም ባሉት ዓመታት የትህነግ ሰዎችና አብረዋቸው የሚሰሩ ሚስጢረኞች፣ እንዲሁም የሚታወቁ ባለ ብሮች ብቻ የሚያውቋቸው የግል እስር ቤቶች በአዲስ አበባና በአንዳንድ ክልልሎች እንደነበሩ ይታወሳል። በነዚህ እስር ቤቶች የሚታሰሩ በድርድር ከፍለው የሚለቀቁ ሲሆን እንደ አሁኑ ሚዲያ ባለመፍላቱ ይፋ አይሆንም ነበር። ይሁን እንጂ በሾርኔ በሚታወቁ አምዶች ፍንጭ ይሰጥ ነበር።
በወቅቱ ደህንነቱ የራሱ ልዩ እስር ቤቶች እንዳሉት ቢታወቅም የግል እስር ቤቶቹ ግን በመንግስት መዋቅር ስራ ባሉ ወይም በነበሩ ከፍተኛ ባለስልጣኖች የሚተዳደር ሃላፊነቱ የተወሰነ ግብር የማይጠበቅበት የግል የንግድ ተቋም እንደ ነበር። ታስረው በድርድር የወጡ ምስክርነታቸውን የሰጡበት ጉዳይ እንደነበርም አይዘነጋም።
አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ “ የአቶ መለስን ሌጋሲ ሳይሸራረፍ አስፈጽማልሁ” ብለው ጠቅላይ ሚኒስትር በሆኑ በዓመታቸው በፓርላማ “ የግል እስር ቤት ያለበት አገር ነው። ምን አድርግ ነው የምትሉኝ” ሲሉ ይህንኑ ጉድ ፓርላማ ላይ አስታውቀው እጅ በአፍ ማስጫናቸው አይዘነጋም። ዛሬ አቶ ጌታቸው ይህ የትህነግ አመል መቀለ ላይ በስፋት መተከሉን አጋልጠዋል።

“አፈቀላጤው” ርዕሰ መስተዳድር በትግራይ የኩዴታ ስጋት ውስጥ
ሰላማዊ ሰልፉ ሌላ እንደምታ እንዳለው የሚገልጹ እንደሚሉት ጉዳዩ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን መብላት ነው። ይህ በተቃውሞ ሰልፍ ስም አስተዳደሩን ለመብላት የተደረጃው ስብስብ ከጀርባ የሚመራው ባኮረፉ የትህነግ ሰዎች እንደሆነም ተመልክቷል።
“ትግራይ እዚህ ደረሳለች” ሲሉ የሚገልጹ የሰሙትን ማመን ተስኗቸዋል። ትግራይ ውስጥ ያለው ጣጣ ተሰፍሮ የሚያልቅ አልሆነም። በፖለቲካው ቋንቋ ትግራይ እንደ ክልል አትቆጠርም። ተበጣጥሳለች። የበጣጠሷት ደግሞ “ ዋስትናዋ ነን” እያሉ የሚምሉት የትህነግ ሰዎች ናቸው። ህጓ ፈርሷል። ደንቧ ወላልቋል። ነዋሪዎቿ ዋስትና ቢስ ሆነዋል። ሕዝቡን ለጦርነት ቀስቅሶ የማገደው ትህነግ ዛሬ ተቧድኖ የጎበዝ አለቃና ዘራፊ ሆኗል። ይህ ሁሉ የተሰማው ከአቶ ጌታቸው ረዳ አንደበት ነውና ማስተባበል እንደማይቻል “ይሰመርበት” ያሉ ገልጸዋል። ለዚህ ይመስላል ትናንት ባተምነው ዜና አንድ እናት “ ምኑም አያምርም” ሲሉ ሃዘን ውስጥ ሆነው አስተያየታቸውን የሰጡት።
ወረዳዎች እና በታችኛው እርከን ያሉ አስተዳደራዊ መዋቅሮች የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል እንዳይሆኑ የተደራጀ ንቅናቄ እንዳለም በግልጽ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው የፌደራል መንግሥት ለትግራይ የአንድ ዓመት በጀት ብቻ መድቦ በመጀመሪያ ዙር 3 ቢሊየን ብር መቀበሉን አስታውቀው አንድ ታላቅ ሚስጢር ይፋ አድርገዋል። “ከ3 ቢሊዮኑ ለሲቪል ሠራተኛው የከፈልነው የአራት ወር ደሞዝ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ሙሉ በሙሉ ለሲቪል ሰራተኛው ሳናወጣ ከ270 ሺህ በላይ ወታደሮችን ምግብ ማቅረብ ስለነበረብን ነው” ሲሉ አሁንም ትግራይ 270 ሺህ ወታደር እንዳላታ አመል፤ክልተዋል።
ለዚህ ይመስላል ሰለ ወልቃይት ሲናገሩ “በሃይል ማስመለስ እንችላለን” ብለዋል። ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸው ወቅታዊ ሁኔታውን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም በትግራይ በኩል ያሉ ግዛቶችን በኃይል እናስመልስ የሚሉ ወገኖች እንዳሉ ይፋ አድርገዋል። “በኃይል ማስመለስ ይቻላል። ነገር ግን የፕሪቶሪያው ስምምነት ከእነ ብዙ ችግሮቹና እጥረቶቹ ከተቀበልን በኋላ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በፌደራል መንግሥት ዘንድ የስምምነቱ አፍራሽ ተደርገን እንዳንቆጠር መጠንቀቅ ያስፈልገናል” ብለዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ መሪ “ አቶ ጌታቸው በኩዴታ ጣጣ ውስጥ ናቸው” በሚል አስቀድመን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖችን ጠቅሰን እንዳልነው እሳቸው ጉዳዩን አረጋግጠውታል። በዜናችን “አኩራፊ የትህነግ አመራሮች” እንዳልነው ቃል በቃል ባያጠቅሱትም፣ አቶ ጌታቸው አስተዳደሩ የማያውቃቸው የግል እስር ቤቶች ከፍተው ህዝብ እየገረፉ ገንዘብ የሚቀበሉ የመዋቅር ሰዎች መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል።
አንዳንድ ወረዳዎችና የታች መዋቅሮች ከትግራይ ክልል አስተዳደር ውጭ ናቸው። አይታዘዙም፣ የሚባሉትን አይሰሙም። የጸጥታ ጉዳይ ቅንጦት ሆኗል። ይህን ለማረም የሚሰራ ስራ ትህነግን የማጥፋት ተደርጎ ተወስዷል። ዝርፊያው በታጠቁና መዋቅር ውስጥ ባሉ ወገኖች ነው። አቶ ጌታቸው ምንም ሳያስቀሩ የትግራይን ወቅታዊ ቁመናና የህዝቡን ስቃይ በይፋ ተናግረዋል።
“ ሲንጋፖር ትሆናለች፣ ጦርነት ባህሏ በመሆኑ ኮሽ ሳይል በሰላም ትኖራለች” እያለ ስለትግራይ ሲዘምር የነበረው ትህነግ የትግራይን ህዝብ ቁብ ነገር ለሌው ጦርነት ዳርጎ ካስፈጀና አካለ ጉዳተኛ ካስደረጋቸው በሁዋላም የሚጸጸት አልሆነም። የትግራይ ነዋሪዎች እንደሚሉት አስገድዶ መድፈር የየዕለት ተግባር ነው። መግደል ስራ ሆኗል። ይህ ሁሉ እየሆነ ለስልጣን ዳግም እርግጫው ተጀምሯል። መፈራረጁና በሰፈር ተቧድኖ ለሌላ እልቂት ማሟሟቅ ላይ የሚገኙ ለመሆናቸው የሚያመላክቱ ጉዳዮች መኖራቸውን አቶ ጌታቸው ” እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም ” ሲሉ እንቅጩን ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ለመገናኛ ዘዴዎች መግለጫ ሲሰጡ የተገኘው የቪኦኤ ዘጋቢ እንዳለው እሳቸው የሚመሩት ጊዜያዊ አስተዳደር መንግሥትንና ፓርቲን ለመለየት ወስኖ እየሰራ መሆኑ አልተወደደም።
አቶ ጌታቸው የሚመሩት አስተዳደር የጀመረውን አዲስ ያሉትን የአሰራር ሂደት በ”ፀረ-ህወሓት ” እንቅስቃሴ የፈረጁ የፓርቲው አመራሮች እንዳሉ ተናግረዋል። አቶ ጌታቸው አንዳንድ የክልሉ ወረዳዎች የጊዜያዊ አስተዳደር አካል እንዳልሆኑ በመግለፅም አዲስ ማህተም ለመጠቀም ፍቃደኛ እንዳልሆም ብለዋል። ይህ መዋቅር እንዳይዘረጋ የማደናቀፍ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል። በስም ቦታዎቹን ባይዘረዝሩዋቸውም ንግግራቸው በትግራይ ማዕከል የሚባል ነገር አለመኖሩን፣ “እኛ የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል አይደለንም” ያሉ ቡድንተኞች አካባቢያቸውን የማስተዳደር ስራ መጀመራቸው ትግራይ ቅርጽ ማጣቷን አመላካች ነው።
አቶ ጌታቸው ” በተደራጀ መልኩ የሚደረግ እንቅስቃሴ አለ፤ በዞን እና በወረዳዎች ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅር እንዳይኖረው የሚሰሩ አሉ። በዚህም ዋናው የሚጎዳው ህዝቡ ነው። ጠቃሚው ነገር የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ጨርሰን ከፌዴራል መንግሥት ጋርም ከነልዩነታችን መተማመናችንን ወደላቀ ደረጃ በማሳደግ በህዝብ የተመረጠ ፓርቲ ስልጣን የሚይዝበት ሁኔታ መፍጠር ነው። በዚህ ሂደት ግለሰቦች በተደራጀ መልኩ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ አለ ፤ እንደ ፓርቲ ጉዳዩ እንቅፋት መሆኑን አንስተን ወደ ግምገማ እንገባለን ” በማለት ሊሆን ይገባል ብለው የሚያምኑትን ምኞታቸውን ገልጸዋል።
“በጀት መድበው የጊዜያዊ አስተዳደሩን ስራ ለማደናቀፍ የሚሰሩ አካላት አሉ” ያለቱ አቶ ጌታቸው “አደናቃፊ” ሲሉ በጥቅሉ የጠቀሷቸውን ቡድኖችም ይሁኑ ግለሰቦች ማንነት አላነሱም። በመግለጫው ወቅት ይህ ስለመጠየቁም የቪኦኤ መረጃ አላብራራም። በጓሮ የሚወጡ መረጃዎች ግን ዶክተር ደብረ ጽዮን የሚመሩት ሃይል ከተጠቀሰው ጉዳይ ጋር ስሙ በስፋት ይነሳል።
“የትግራይ ህዝብ ዳግም ወደ ጦርነት እንዳይገባ ሁሉም አይነት ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ እንሰራለን። በአማራ ክልል ሆነው የትግራይን ህዝብ ማጥፋት የሚፈልጉ አካላትን ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመተባበር አደጋ መፍጠር ወደማይችሉበት ደረጃ ለማውረድ ያለ ጥርጥር እንሰራለን ” ማለታቸው በተለይ የሻዕቢያን ሃይል ይሁን ሌላ አሁንም አላብራሩም። ፕሬዚዳንት ኢሳያስን ያላስደሰተው የሰላም ስምምነቱን ያስታወሱ እንደሚሉት ሻዕቢያ ከትግራይ ሙሉ በሙሉ ለቆ እንዲወጣ የፌደራል መንግስት ጥያቄ ማቅረቡን ከዚህ ጋር ያያይዙታል።
አቶ ጌታቸው በፕሪቶሪያ ስምምነት እና በሀገሪቱ ህገመንግስት መሰረት የትግራይ ክልል አስተዳደር ወደ ቀድሞው የመመለስና ተፈናቃዮችን ወደ ቄያቸው ዳግም የማስፈር ጉዳይን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመርህ ደረጃ መስማማታቸውን ገልጸዋል። ይህ ሂደት በመጓተቱ በነዋሪው ህዝብ እና ተፈናቃዮች ላይ ችግሩ አሁንም መቀጠሉን አመልክተዋል። አቶ ጌታቸው በመርህ ደረጃ ስምምነት ተደረሰበት ያሉትን ጉዳይ አስመልክቶ አማራ ክልል ጥብቅ አቋም እንዳለው ያስታውሳሉ።
አቶ ጌታቸው በመግለጫቸው በክልሉ መንግሥት የማያውቃቸው እስር_ቤቶች መኖራቸውን ይፋ አድርገዋል። “ መንግሥት የማያውቃቸው እስር ቤቶች አሉ። ይሄን ጉዳይ የሚያከናውኑና የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፀሙትን ማሰር ጀምረናል። በዘመቻ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንይዛቸዋለን። ሰዎችን በመጥለፍ ገንዘብ የሚቀበሉ አሉ ፤ ኤርትራውያንን በመያዝ ብር እየተቀበሉ ናቸው። እነሱን ብቻ ሳይሆን የክልሉ ተወላጆች፣ሀብታም ቤተሰብ ያላቸውን እየያዙ ናቸው ፤ እነዚህ በመንግሥት መዋቅር ስም የሚንቀሳቀሱ ናቸው ፤ ሰላዮች ነን የሚሉ፣ በተለያዩ አደረጃጀቶች ስም የሚሰሩ ናቸው። ለማጣራት ረጅም ጊዜ ወስዶብናል ከዛሬ ጀምሮ ግን በሚቀጥሉት ቀናት ፍርድ የሚያገኙበት ስራ እንሰራለን። የራሳቸው እስር ቤት አቋቁመው ሰዎችን እየደበደቡ ገንዘብ እየተቀበሉ የሚሰሩ በስም የምናውቃቸው ሰዎች አሉ። ” ሲሉ አስደንጋጭ የሆነውን ሌላ የትግራይ መልክ ገልጸዋል። ቀደም ሲል ለዕርቅ ልመና ወደ ትግራይ የሄዱ እናቶች እግር ላይ ወድቀው በለቅሶ “ለሰላም እጃችሁን አንሱልን፤ ታረቁ” ሲሉ የተመለሰውን መልስ ለሚያስቡ ዛሬ ትግራይና ሰላማዊ ነዋሪዎቿ የገቡበት የመከራ አረንቋ ለሌሎችም በአስቸኳይ ትምህርት የሚሆን ሆኗል።
በትግራይ ያለው የፀጥታ ችግር ከፍተኛ መሆኑን ያሳወቁት አቶ ጌታቸው ረዳ “ወጥቶ መግባት ቅንጦት ሆኗል ብለዋል። ” እንኳን ለህዝቡ ታጅበን ለምንሄድ ባለስልጣናትም ዋስትና የሚሰጥ የፀጥታ ሁኔታ የለም ፤ ይሄን ለማስተካከል ከስራ ውጭ የነበሩ የፀጥታ አካላትን ወደ ስራ የመመለስ ስራ እየተሰራ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ባለፈው ህዝቡን በማስተባበር ፀጥታ ለማስፈን ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል። አክለውም ከምንም በላይ የሁሉም ችግር ዋናው ምንጩ ፖለቲካዊ እንደሆነ ገልጸዋል።
ከእርዳት ምዝበራ ጋር በተያያዘ እስካሁን 482 እርዳታ መዝብረዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የገለፁት አቶ ጌታቸው እስካሁን እርዳታ ባለመጀመሩ ተፈናቃዮች በተለየ መንገድ ችግር ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ከጦር አካል ጉዳተኞች ጋር በተያያዘም ሰልፍ እየወጡ ያሉት መንግሥት በአግባቡ ስራውን ባለመስራቱና የክልሉ የበጀት አቅም አነስተኛ በመሆኑ የተነሳ እንደሆነ ያስረዱት አቶ ጌታቸው መንግስታቸው በአግባቡ እንዳልሰራ የጠቀሱትን አላብራሩም። የበጀት ማነስን ቢያነሱም የቀመር ችግር ስለመኖሩ ቅሬታ አላነሱም።
በክልሉ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጠርተውት ስለነበረው የተቃውሞ ሰልፍ አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ በክልሉ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንዳለ አመልክተዋል። ፈንጂዎችም በብዛት መገኘታቸውን ተናግረዋል።
ሰልፍ ማድረግ መብት ቢሆንም ለህዝብ ደህንነት ሲባል የሚካሄደው ሰልፍ ጊዜው እና ቦታው እንዲቀየር ከሰልፍ መሪዎች ጋር እንደሚነጋገሩ አስታውቀዋል።
” መንግሥት የፀጥታ ኃይል ማሰማራት እችላለሁ በሚልበት ሰዓት እና ቦታው ሰልፍ ማካሄድ የተለመደ ነው ” ያሉት አቶ ጌታቸው ” አሁን ገና ተነጋግረን አልጨረስንም ፤ ስለ አካሄዱ የምንነጋገርበት ነገር አለ፤ የፀጥታ ችግር አለ ፤ ከፍተኛ የሆነ የፈንጂዎች መሰባሰብ ስራ፣ ለሁከት ከጎረቤት አካባቢ የመጡ መኖራቸው ስለተድረሰበት የፀጥታ አካላት የሚያጣሩት ይሆናል። ሰልፍ የጠሩት አካላት ረብሻ ይፈጥራሉ ሳይሆን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅመው ረብሻ በመፍጠር ትግራይን ዳግም ወደ ሁከት ለማስገባት ያቀዱ ኃይሎች አሉ ” ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።
ዜናው ከቪኦኤ፣ ቲክቫህና ሚዛናዊ አስተያየት በመስጥት ከሚታወቁ የማህበራዊ አምደኞች መረጃ የተካተተበት ነው።
- የበርሊን ማራቶን ባለማዕረግ ትግስት እነ ዱቤ ጂሎ ቢሳተፉ ታዝረከርካቸው ነበርበማራቶን ከሁለት ደቂቃ በላይ ማሻሻል እጅግ የሚደነቅና ያልተለመደ ነው። ባለሙያዎቹ ወይም አሰልጣኞቹ የሮጠችበትን ፍጥነት በሰዓትና ርቀት ከፋፍለው ቢያቀርቡት ምን አልባትም ወንዶችን የሚገዳደር ፍጥነት ተጠቅማ ሮጣለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቴክኒክ ዳይሬክተርና የአትሌቶች ኮሚሽን ሰብሳቢ የነበሩት የዛሬው የተከበሩ ዱቤ ጅሎ አይነቱን ሯጮችን አዝረክርኮ ማሸነፍ የሚያስችላትን ሃይል አሳይታለች። የበርሊና ባለ ማዕረግ ትዕግስት!! ተግስት … Read moreContinue Reading
- ለወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ አንድ ሚሊዮን የጉልበት ሰራተኛ ይፈለጋል፤ ከአንድ ነጥን አንድ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ሰሊጥ ይጠበቃል“ከየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል አስተማማኝ ሰላም ያለው እዚህ ነው። ለሰራተኞች እንደ ቤተሰብ ዝግጅት አድርገናል። ኑ” ሲሉ የተሰሙት አምስት መቶና ሶስት መቶ ሄክታር ሰሊጥና ማሽላ ያመረቱ ባለሃብቶች ናቸው። የዞኑ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እንዳሉት አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ ኩንታል የሰሊጥ ምርት ስለሚጠበቅ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሰራተኛ ሃይል ያስፈልጋል። የዞኑ አርባ … Read moreContinue Reading
- የጎንደርን ከተማ ምን አይነት ተኩስ እንደሌለ ተገለጸ፤ ጎንደር ተይዛለች ተብሎ ነበር“ጎንደር ከተማን ሙሉ በሙሉ ይዘናታል” ሲሉ ስማቸው እንዳይገለጽ ጠይቀው ለጀርመን ድምጽ መረጃ በሰጡ የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ ቃል አቀባይ አየር ማረፊያውን ሆን ብለው እንዳልያዙ አመልክተዋል። እሳቸው ተናገሩ የተባለው በጀርመን ድምጽ እየተሰማ በለበት ሰዓት በተመሳሳይ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ውጊያ መደረጉን ሳያስተባብል ከተማዋን ለመያዝ የገባው ሃይል መደምሰሱን አሃዝ ጠቅሶ አመልክቷል። አገር መከላከያም … Read moreContinue Reading
- “የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ፣ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ”የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ) የሚለው የቆየ ተረት ልብን የሚያደማ ኩነትን ማሳያ ነው። እቺ መከረኛ ሚስት ባልዋ በእናቷ ልጅ ወንድሟ ተገደለ። ሟች ባል፣ ገዳይ ወንድም … ኢህአፓ “ሃይማኖት ነው” በሚል ሲገልጸው በነበረው ትግል በቀይና ነጭ ሽብር ስም እናቶች የወላድ መካን ሆነዋል። ጧሪ ያጡና ባዶ ቤት ሃዘን … Read moreContinue Reading
- በአማራ ክልል የተነሳው ጦርነት በሰላም ሊቆጭ እንደሚችል ተሰማበአማራ ክልል የተቀሰቀሰው ጦርነት በሰላማዊ መንገድ የሚቋጭበት አግባብ ተስፋ ሰጪ ደረጃ መድረሱ ተሰማ። የኢትዮ12 የዜና አቀባዮች እንዳሉት ሰላም ወደድ የሆኑ ዜጎች ችግሩን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያደረጉ ያለው ጥረት ውጤታም እየሆነ መሆኑንን ነው ያመለከቱት። በሰላም ጥረቱ ውስጥ የሚሳተፉትን ወገኖችና የሰላም ንግግር አመቻች የሆኑትን ክፍሎች ሳይጠቅሱ የዜናው ሰዎች እንዳሉት ጥረቱ ብዙ መንገድ … Read moreContinue Reading