Site icon ETHIO12.COM

ፖሊስ በሼኽ አብዱ ያሲን ግድያ ያሳደጉት ልጅ ተጠርጣሪ ሆነ፤ ፖሊስ ተፈላጊውን ምስል አሰራጭቶ “ጠቁሙኝ” ብሏል

ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረው መሃመድ ሽኩር አበባውን ያየ ማንኛውም ግለሰብ ጥቆማ እንዲሰጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቀረበ፡፡ ፖሊስ ዝርዝር ባይናገርም ተጠርጣሪውን በአጭር ጊዜ ለይቶ አደን ላይ መሆኑንንም አመልክቷል።

በአስኮ አዲስ ሰፈር የጁሙዓ ኸጢብና የኪታብ አቅሪ የነበሩት ሸይኽ አብዱ ያሲን ከዒሻን ሰላት ሲመለሱ በተተኮሰቧቸው ከጀርባቸው ጭንቅላታቸው ላይ በጥይት ተመተው ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ነው፡፡

ግድያውን ተክትሎም የአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀሉን ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ለማዋል የክትትልና የምርመራ ቡድኖችን አዋቅሮ አደኑን አጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቋል።

በተደረገው ክትትልም የመኖሪያ አድራሻው ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ነዋሪ የሆነው እና ሟቹ ሼክ ያሲን ያሳድጉት መሃመድ ሽኩር አበባው ሼህ አብዲ ያሲንን በመግደል ወንጀል ተጠርጥሮ እንደሚፈለግ ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ ተጠርጣሪውን እንዴት እንደለየ ባይገልጽም፣ ተጠርጣሪው ግድያው ከተፈጸመ በሁዋላ መሰወሩን የሚያውቁት እየገለጹ ነው።

ስለሆነም ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የተጠረጠረውን  መሃመድ ሽኩር አበባውን ያየ  ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል፡፡ ሼኽ አብዱ የቀብር ስነስርዓታቸው ላይ ወዳጆቻቸውና ተከታዮቻቸው በእርጋታ ፖሊስን የሚያግዝ ጥቆማ እንዲሰጡ ተጠይቆ ነበር። ልጆች ይሳድጉ እንደነበር የተነገረላቸው አባት፣ ያልከፈሉት ብድር ስላለባቸው ዕዳቸውን በመተባበር እንዲከፍሉላቸውም ጥሪ መቅረቡን ቲክቫህ ስለቀብር ስነስርዓቱ ሲዘግብ አመልክቶ ነበር።

Exit mobile version