Site icon ETHIO12.COM

አባይ ቲቪ በህግ ተከሶ መቀጣት ይገባዋል፤ ጥላሁን ብሎ አዝናኝ ኮሜዲያን – የልቃሚዎች ስብስብ

ጥላሁን እልፍነህ የሚባለው ጋጠወጥ ከድሮም ጀምሮ ከአንገት በላይ እጥረት ያለባቸው ጓደኞቹ ሁሉ ድምር እንደሆነ ለማወቅ ብዙም ምርምር አያስፈልግም። አንዴ እንደዚህ ሆነ።

ብሄራዊ ቲያትር ፊት ለፊት ወደ ፒያሳ የሚሄድ ሚኒባስ ያዘና ከፊቴ ተቀመጠ። ታክሲው ሳይሞላ ያጣድፈዋል። “ህዝብ የሚጠብቀው እኔን ነው” ሲል የሜጋ አንፊ ቲያትርን በጣቱ መንካት እየከጀለው ወተወተ። ደጋሞ “ህዝብ የሚጠብቀው እኔን ነው። የሚጋፋው እኔን ብሎ ነው” እያለ ሲለፍለፍ ” አንዱ አንተን ሲያዩ ለመውጣት ካልሆነ በቀር ለመግባት አይጋፉም” ብሎ እዚህ ላይ የማይጻፍ ለጥፎበት …. የኢትዮጵያ የ”አርቲስቶች” ጉዳይ ሲከፍቱት ብዙ ጠረን ያለው፣ አስመሳይ ሃይማኖተኞች፣ መርመጥመጫው ድቤ ሰፈር የሚውሉ …

“ለመንደርደሪያ ያህል ይህን ካልኩ ከቶማስ ጃጃው ያገኘሁትን ልኪያለሁና አንብቡት ” ሲል አንባቢ ልኮልን አትመነዋል። መልካም ንባብ።

በአባይ ቲቪ በዓሉን አስመልክቶ በቀረበው ዋሸው እንዴ የኮሜዲያን ጨዋታ ፕሮግራም ላይ የማህበረሰብን መልካም ባህልና እሴትን የሚጥስ የሴቶችን ልጅ ስብዕና ክብር መብት የሚዳፈር ጥቃት እንዲደርስባቸው የሚያበረታታ ስራ ተሰርቷል።

የኮሜዲያኖቹ ስራ እንደ ቀልድም ሊወሰድ የማይገባው ከወዲሁ በጥንቃቄ ሊታይ ሊታረም ብቻ ሳይሆን በሕግ ሊጠየቅም የሚገባው አደገኛ የጥፋት የነውር ልምምድም ነው። ፕሮግራሙ ላይ ፍልፍሉ የተባለው ኮሜዲ ‘ይቅርታ ሴት ደፍሬ አውቃለሁ…’ ሲል፥ ጃሉድ ቀለል አድርጎ ‘የምን ይቅርታ ነው ? ፈጣሪውንስ ሚዳፈር አለ አይደል እንዴ ? ይሄማ ኖርማል ነው…’ ይላል(በእርግጥ ጃሉድ ዕድል ከተሰጠው ሌላም ይላል)። ጃሉድን ተከትሎ የተናገረው ጥላሁን እልፍነህ ደግሞ ከሁሉም የከፋ ነው። ሴት ልጅን ‘ ስንት ነገር አለ አይደል ይሄማ ኖርማል ነው። የእኔ አባት ጨምሮ አብዛኛው ወንድ ጠልፎ’ና ደፍሮ ነው ያገባው….’ ብሎ ከመናገሩ በተጨማሪ
ደፈራ ደፈራ ደፈራት
መሬት አስተኝቶ እያንፈራፈራት
እኛ እስከምናውቀው ከጥንት ጀምሮ
ሁሉም ሰው ያገባው አስገድዶ ደፍሮ….’
ብሎ በመዝፈን ለሴት ልጅ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ ያለውን ንቀት የራሱንም ነውረኛ ባህሪን በደንብ ገልጦ አሳይቷል።

በነገራችን ላይ ጥላሁን እልፍነህ የተባለው ኮሜዲ ከዚህ በፊትም የሚታወቀው
” ጎበዙ ይሮጣል ለዝና ለሐገሩ
ነጋዴው ይሰራል ለእድገት ለብሩ
አራሹም ይደክማል ለሰብል ለዘሩ
ሌላው ይሯሮጣል ለደግ ለጥሩ

የእኔ ግን ሌላ ነው
ወዲነው ምስጢሩ
ዳሌ ጥሩ ጥሩ።”
አይ ኮበሌ
ክፉ አመሌ ሲል ነው።

የጥላሁን እልፍነህ የከዚህ ቀደም
አይ ኮበሌ
ክፉ አመሌ
ስራ
ውስጣዊ ማንነቱን ያሳየበት ለዳሌ መዝፈንና ለዳሌ መኖር ዋና ተልዕኮው ስለመሆኑ የሚናገር መሆኑን ስለመድፈር ኖርማልነት የተናገረውና የዘፈነው ከበቂ በላይ ማረጋገጫ ነው። እርግጥ ነው አባቴ ጠልፎና ደፍሮ ነው ያገባው ማለቱ ጥላሁን ዛሬ የሆነውን የሆነው እንዲሁ ፈልጎት አይደለም ሊባል ይችላል። የሆነው ቢሆን ግን ጉዳዩን ሳያወግዙት ማለፍ የሚቻል አይሆንም።

የሴት ልጅ መደፈርን ኖርማል እያስመሰሉ በሴቶች ላይ ጥቃት እንዲደርስ መቀስቀስ የማህበረሰብን መልካም ባህልና እሴትን የሚጥስ ጉዳይ ሊወገዝ እንጅ ሊበረታታ አይገባም። እነ ነውር ጌጡ ኮሜዲያኖች ብቻ ሳይሆኑ ፕሮግራሙን ያስተላለፈው የአባይ ቴሌቪዥንም በዚህ ጉዳይ ሊወገዝና በሕግ ሊጠየቅም ይገባዋል።

Exit mobile version