Site icon ETHIO12.COM

ጉተሬዝና አልሲሲ – ሲናበቡ

Image processed by CodeCarvings Piczard ### FREE Community Edition ### on 2019-09-23 13:04:28Z | http://piczard.com | http://codecarvings.com&#ÿ“e"ý^

“ግብፅ ሆይ በእኛና በኢትዮጵያ መሀከል በተደረገው ስምምነት ጉዳይ የየትኛውንም ሀገር ጣልቃ ገብነት በፍፁም የማንቀበል መሆኑን አውቀሽ ፣ ስለኛ ቀጠና ሰላም መረጋገጥ ያለውን ጉዳይ ለእኛ ትተሽ አርፈሽ በጦርነት እያለቁ ያሉት ጎረቤቶችሽን ፍልስጤም ጋዛ ፣ ሱዳን እና ሊቢያ ላይ አተኩሪ ስለእኛ አይመለከትሽም ። ” 

አስተያየት – Biniam Chifraw Sisay

የወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፕሬዚዳንት አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የግብፅ ባለስልጣናት ሊናበቡ የሞከሩት ነገር ትዝብት ላይ ጥሏቸዋል።

ፍልስጤማዊያን ያ ሁሉ ውርጅብኝ ሲወርድባቸው ሁለቱ አካላት ትንፍሽ አላሉም! ፕሬዚዳንቱ ሶማሊያና ኢትዮጵያ ከሰሞኑ የገቡትን እሰጣ እገባ ቁጭ ብለው ይፍቱ ማለታቸው ለሰላማዊ ውይይት ሁሌም በሩን ክፍት ያደረገው የኢትዮጵያ መንግስት ከእሳቸው በፊት ባወጣው መግለጫም ይህን ጉዳይ ማንፀባረቁን ልብ ማለት ያስፈልጋል!

የሶማሌላንድ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የግብፁን ፕሬዝዳንት የሽለላ ንግግር ተከቶሎ ባወጣው የመልስ መግለጫ “ግብፅ ሆይ በእኛና በኢትዮጵያ መሀከል በተደረገው ስምምነት ጉዳይ የየትኛውንም ሀገር ጣልቃ ገብነት በፍፁም የማንቀበል መሆኑን አውቀሽ ፣ ስለኛ ቀጠና ሰላም መረጋገጥ ያለውን ጉዳይ ለእኛ ትተሽ አርፈሽ በጦርነት እያለቁ ያሉት ጎረቤቶችሽን ፍልስጤም ጋዛ ፣ ሱዳን እና ሊቢያ ላይ አተኩሪ ስለእኛ አይመለከትሽም ። ” ብሏታል። ይሄ መልስ በተዘዋዋሪ ለጉተሬዝም ይሆናል..!!!

የሶማሊላንድ ፕሬዚዳንት የሆኑት ሙሳ ቢሂ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጋር የጀመሩትን የተጠናከረ ግንኙነት ዋሽንግተን ዲሲ ላይ ከአሜሪካ ጋር እንዲደግሙት ቀነ ቀጠሮ ተቆርጧል ። ይሄን ጉዳይ እነ ግብፅ እንዲሁም ጉተሬዝ ባላየና ባልሰማ አልፈውታል። እንደ ቀጠናዊ ስጋትም አይመለከቱትም…!!! የሙሳ ቢሂ ጉብኝት ከአሜሪካ ጋር ጉልህ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ማድረግን ያካትታል…!!! አሜሪካ በርበራ ኤርፖርት አካባቢ የምታቋቋመው የጦር ሰፈር ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓቱ አንድ አካል ተደርጎ ተዘጋጅቷል። ይሄም በፔንታጎን ውስጥ ይካሄዳል። እንግዲህ ኢትዮጵያን እናቆማለን እያሉ የሚፎክሩት ግብፅና ሌሎች የሰፈራችን የጦርነት አፍቃሪዎች አሁን ምን ይሉ ይሆን…?

ኢ-ፍትአዊ አካሄድን ከጥንት ጀምሮ የማትቀበለው ኢትዮጵያ ዛሬም እውነትንና አብሮ የመልማት ቀጠናዊ እሳቤን ይዛ ወደፊት እየገሰገሰች ነው..! በኢትዮጵያም ሆነ በሶማሌላንድ ህዝብና መንግስት በኩል በጋራ መልማትን መሰረት ያደረገና የትኛውም የዓለም ሀይል ሊበጥሰው የማይችል እንደ ብረት የጠነከረ ቁርኝት ተፈጥሯል። ወዲህ ኢትዮጵያን የባህር በር ባለቤት የሚያደርግ በሌላ በኩል ለሶማሌላንድ የሀገርነት እውቅና የሚያስገኘውና ከሀገራችን ጋር በልማት የሚያስተሳስረው የድል ብስራት ከሳምንታት በኋላ ለመላው ዓለም ይፋ ይሆናል። ያኔ እነ ግብፅ ለሶስተኛ ጊዜ በአብቹ መሸነፋቸውን ማመን ባይፈልጉ እንኳን እንዲያምኑ ይገደዳሉ…!!!

Exit mobile version