“አልዘምትም” ወይም “ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ” ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!

በጥቅሉ ከመጓተት ዝንባሌ መራቅ ያስፈልጋል። አልፎ አልፎ ልዩነቶች ሲፈጠሩ በምክክር አስተካክሎ ማለፍ ይመከራል። ነገር ግን “No More” እያሉ በማላገጥ የሰላም ተቆርቋሪ መሆን አይቻልም። ያለፈው አልፏል፣ ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ አያስፈልግም። ሆኖም ከዚህ በኋላ በግልፅና በቀላሉ “አልዘምትም” ወይም “ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ” ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!

( Yesuf Ibrahim – ዩሱፍ ኢብራሂም የአብን ስራ አስፈጻሚ )

በተቃራኒው የሚያስረዳ ይህ ነው የሚባልና የሚታወቅ ወገን በሌለበት አግባብ የአማራ ህዝብ ችግሮች በራያና በወልቃይት ዙሪያ ብቻ የታጠሩ አይደሉም እያሉ መናገር ከንቱ ድግግሞሽ ነው። በአማራ ላይ በየአካባቢውና በየጊዜው የሚፈፀሙ unprovoked ጥቃቶች ተባብሰው ቀጥለዋል፣ ይህ በሁሉም ወገን ላይ ከፍተኛ የስነልቦና ጫና ያሳደረ ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል። የህዝቡ መሰረታዊ ጥያቄዎችም ቢሆኑ ገና ምላሽ አላገኙም!

ሆኖም የአማራ ትግል በአስቸጋሪ አቀበት ላይ ደረጃ በደረጃ እንደ መውጣት የሚቆጠር ሲሆን የጊዜውንና የአሰላለፉን ሁኔታ ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

የአማራ ማህበረ-ፖለቲካ ሁኔታ ምን እንደነበረ እና አሁን ምን ላይ እንደሚገኝ በመረዳት ቀጣዩን ፍኖት መትለም ይገባል። በዚህ ረገድ ለሃምሳ አመታት ያክል ከገባበት ቅርቃር ለመውጣት ምን ያክል ጊዜና ስራ እንደሚጠይቅ ማወቅ ያስፈልጋል። ይህ የፍላጎት ጉዳይ ሳይሆን የራስንና የጠላትን አቅም የማስላትና የማወቅ ጉዳይ ነው። የምንፈልገውን ሁሉ ማድረግ ብንችል የምንወራከብበት ምክንያት አይኖርም ነበር!

የትህነግ ስብስብ በቅርቡና በድንገት እንደ ክረምት-አግቢ የተከሰተ ኃይል ሳይሆን በአማራ ላይ የተንሰራፋውን የጥላቻ ትርክት፣ ሥርዓትና መዋቅር ያቋቋመ እና አማራን ለማጥፋት በእቅድ የተደራጀ እና የሰለጠነ ኃይል ነው።

ትህነግ የአማራ ህዝብ በሌለው ነገርና ባልፈፀመው ጉዳይ ላይ ሁሉ ከሳሽና ፈራጅ ሆኖ መኖር የሚፈልግና ከዳር እስከዳር ሀገር እያተራመሰ ወቀሳውን ጠቅልሎ አማራ በራፍ ለይ የሚወረውር ግብዝ ኃይል ነው። ያለፈውን እንኳ ብንዘነጋው አሁንም “ከአማራ ጋር የማወራርደው ቀሪ ሂሳብ አለኝ” ማለቱ ይታወሳል።

በጥቅሉ ከመጓተት ዝንባሌ መራቅ ያስፈልጋል። አልፎ አልፎ ልዩነቶች ሲፈጠሩ በምክክር አስተካክሎ ማለፍ ይመከራል። ነገር ግን “No More” እያሉ በማላገጥ የሰላም ተቆርቋሪ መሆን አይቻልም። ያለፈው አልፏል፣ ለጊዜው በዚህ ጉዳይ ላይ ልዩ ትኩረት ማድረግ አያስፈልግም። ሆኖም ከዚህ በኋላ በግልፅና በቀላሉ “አልዘምትም” ወይም “ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ” ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!

በየግንባሩ ተሰልፈው ከጠላት ጋር የሚዋደቁትና ዋጋ የሚከፍሉት ወንድሞችና እህቶቻች ግራ ቀኙን የማያዩና የፖለቲካ መረዳት የሌላቸው ጠመንጃ ነካሾች አይደሉም!

Leave a Reply