Site icon ETHIO12.COM

” የሎንግ ኦነግ ሸኔን መክዳት ከዜና በላይ ነው” – የሸኔ የሎጂስቲክ መረጃ መንግስት እጅ ገባ

“ዜናውን እንደተለመደው የዘገቡት ሚዲያዎች ጉዳይ አስገርሞኛል” ይላሉ የአውስትራሊያው ነዋሪ። “አሁን እኮ የሸኔ የሎጂስቲክ፣ የምልመላና የስምሪት ሙሉ መዋቅር እኮ ነው መንግስት እጅ የገባው” ሲሉ ያክላሉ። ይህ ዜና “እጅ ሰጠ” በሚል መደብዘዙ እጅግ እንዳስገረማቸው የሚናገሩት “እጅ ሰጠ” የተባለውን የኦነግ ሸኔ ከፍተኛ ባለስልጣን ጠንቀቀው ስለሚያውቁ ነው።

“ሎንግ በሚለው ቅፅል ስሙ የሚታወቀው በምስራቅ ጉጂ ዞን የሸኔ የሎጂስቲክስና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ገመዳ ዱጎ ለመከላከያ ሠራዊት እጁን ሰጠ” የሚለው ዜና ሲሰማ ያነጋገርናቸው የቀድሞ የኦነግ መካከለኛ አመራር ” በዜናው ባልደሰትም። ትልቅ ኪሳራ ስለመሆኑ ጥርጥር የለውም። ውጤቱን በቅርቡ እናየዋለን” ሲሉ ተደምጠዋል። ሎጅስቲክ መሳሪያ፣ ገንዘብ፣ ቀለብ፣ ልብስ፣ ህክምና፣ መድሃኒት ወዘተ ታዋጊዎቹ ባሉበት ሁሉ የሚደርስበት አግባብ ነውና የዚህ መስመር ባለቤት መንግስት እጅ መግባት እንደተለመደው አይነት ዜና አይደለም።

አሁን ላይ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሌሉ አስታውቀው አስተያየት የሰጡት እኚሁ ሰው እንዳሉት ” ሎጂስቲክ የአንድ አደረጃጀት የጀርባ አጥንት ነው። የራሱ መረብና የግንኙነት እርከን አለው። መንግስት እንግዲህ እጁ ያስገባው ይህንን ነው፣ መረቡን አውቀውታል ማለት ነው። ይህ ደግሞ አደጋው ሰፊ ነው”

በምስራቅ ጉጂ እና አካባቢው ሲንቀሳቀስ በነበረው የሸኔ ቡድን ላይ ሠራዊቱ እየወሰደ በሚገኘው የተቀናጀ ወታደራዊ እርምጃ የቡድኑ ከፍተኛ አመራሮች እጃቸውን እየሰጡ እንደሚገኙ የክፍለጦር ዋና አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ገብሬ ጋሞ ማስታውቃቸውን የመከላከያ ዜና ቢያስረዳም፣ አስተያየት ሰጪው ” ገመዳ ዱጎ ቀደም ሲል ንግግር አድርጎ፣ ስምምነት ደርሶ፣ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ እግሩን ሳይነቅል አቀብሎ ስለማጠናቀቁ አሁን ላይ የመንግስት ሃይል እየውሰደ ያለው እርምጃና የሸኔ ሃይል መዳከም ምስክር ነው። ስለዚህ በንደት በውጊያ መሃል እጅ ሰጠ የሚለው አያስኬድም”

በኬንያ ያለው ኤምባሲ ይህን በማመቻቸት ከፍተኛ ስራ እንደሚሰራ እውቀቱ እንዳላቸው በማመልከት አስተያተቻውን ሲያጠቃልሉ ” ሃያ አምስት ዓመት በላይ ኦነግን ሲያገለግል፣ በፖለቲካ፣ ምልመላና ሎጂስቲክ ጉዳዮች ሃላፊ የሆነ ሰው ሲከዳ ይዟቸው የሚሄዳቸው በርካታ ጉዳዮች አሉ። ይህን በቅርቡ በዝርዝር የመናየው ይሆናል። ለሁሉም ግን ሁሉም ወደ ስምምነት ቢያመሩ ይበጃል” በማለት ነው።

ሠራዊቱ ሰበቦሩ እና ዳዋ በሚባሉ አካባቢዎች በጠላት ላይ በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ድል መቀዳጀቱን ዋና አዛዡ ገልፀው፤ የሠራዊቱን ብርቱ ክንድ መቋቋም ያቃተው የሸኔ ታጣቂ ቡድን ላይ ተፅዕኖ መፍጠር መቻሉን ገልፀዋል።

በዚህም ሎንግ በሚለው ቅፅል ስሙ የሚታወቀው በምስራቅ ጉጂ ዞን የቡድኑ የሎጂስቲክስ እና የፖለቲካ ዘርፍ ላፊ ገመዳ ዱጎ ለሠራዊቱ እጁን ሰጥቷል ብለዋል።

ሠራዊቱ አስቸጋሪና ፈታኝ በሆኑ መልክዓ ምድሮች ላይ ግዳጁን በብቃት ከመወጣቱም ባሻገር፤ የቡድኑን እኩይ ዓላማ በመበጣጠስ እና ጠላትን እፎይታ በመንሳት ተገደው እጃቸውን እንዲሰጡ እያደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል።

ለሠራዊቱ እጁን የሰጠውና በጉጂ ዞን የሸኔ የሎጂስቲክስ እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበረው ገመዳ ዱጎ (ሎንግ)፥ ዓላማ በሌለው እና ህዝብን በሚጎዳ ተግባር ላይ መሳተፉ ጥቅም እንደሌለው እና እንደማያዋጣ በማመን ለሠራዊቱ እጁን መስጠቱን ተናግሯል።

በ1987 ዓ.ም የሽብር ቡድኑን እንደተቀላቀለ የሚናገረው የቡድኑ ከፍተኛ አመራር፥ ላለፉት በርካታ ዓመታት ህዝብን በማሰቃየትና በመዝረፍ ላይ የተሰማራው ሸኔ በሠራዊቱ በተወሰደበት እርምጃ እየተበታተነ እና አመራሩም ጭምር በሀሳብ እየተፈረካከሰ እንደሚገኝ አብራርቷል።

ቡድኑ አሁን ላይ ህዝብን ከመዝረፍ ውጪ ምንም ዓላማ ስለሌለው እጁን መስጠቱን ገልፆ፤ በየጫካው ተበታትነው የሚገኙ የቡድኑ ታጣቂዎች ለሠራዊቱ እጃቸውን በመስጠት ወደ ሠላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቧል። ዜናው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገፅ ከተገኘው መረጃ ላይ ዳብሮ የቀረበ ነው።

Exit mobile version