Site icon ETHIO12.COM

” የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል ” አቡነ ማቲያስ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ” የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል ” ሲሉ በ11ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸው ተናገሩ።

ፓለቲከኞቾም ባልዋሉበት እና ባልተፈቀደላቸው ቦታ በቤተክርስቲያን ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንዲቆጠቡ አሳስበዋል። ቅዱስነታቸው ” የዘመናችን ትውልድ ከተግባር ይልቅ አስመሳይ ሆኖ መታየትን ከቅድስና ይልቅ ነውረ ኃጢአትን፤ ከትሕትና ይልቅ ትዕቢትን የተለማመደ ለሃይማኖትም ሆነ ለማኅበረ ሰብ ጤና ያልተመቸ ትውልድ እንደሆነ በግልጽ ይታያል ሲሉ ተግሳጽ አሰምተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቀነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት 11ኛ ዓመት በዓለ ሢመታቸውን አስመልክቶ ምን አሉ ?

Exit mobile version