Site icon ETHIO12.COM

አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!

ያበደው አንድ ጀግና ታወሰው። አባቱ መቃብር ስር የሚርመጠመጡ ሰዎች ነበሩ። አባቱ የአገር ጀግና ነበር። ታልቁ የሩጫ ሰው። እናም በሃውልቱ ስር ከቤተሰብ በላይ ቤተሰብ፣ ከቤተሰብ በላይ አዛዥ፣ ከቤተሰብ በላይ ሃውልት ተንከባካቢና ዕቅድ አውጪ እየሆኑ በሚዲያ ሲቀርቡ፣ ቤተሰብ ተረሳ። መጨረሻ ላይ ቤተሰብ ሃውልቱን በሚፈልገው መልኩ ለማሰራት ሲንቀሳቀስ እኒህ ሰዎች ክልከላ አመጡ። ከብዙ ጭቅጭቅ በሁዋላ ቤተሰብ በዚህ ቆፍጣና ልጅ አቋም መብቱን አስከበረ። ይህ ጀግና ስለጉዳዩና ስለክርከሩ ሲነሳለት የሚለው ” አባቴ ሃውልት ስር ምን እንደሚያርመጠምጣቸው ነው አልገባ ያለኝ” የሚል ምላሽ ነበር የሚሰጠው።

አጤ ምኒሊክ አንዴ ቀና ቢሉ …. አጤ ምኒሊክ አንዴ፣ ላንዳፍታ ቢነሱ … አጤ ሚኒሊክ ለቅጽበት … ቦሰና ይህን ጥያቄ ደጋግም መጠየቅ ከጀመረች ሰነባብታለች። እሳቸው ሞትን አሸንፈው ምስክረነት ካልሰጡ በቀር ነገር የማይገባቸው ” ደረቅ አሳዎች” አሳስበዋታል። ያበደው በቦሰና አሳብ ይስማማል። አጤ ሚኒሊክ ላፍታ ቢነሱስ? ያበደው ዘለለ …. እያርጎመጎመ ተሳደበ። ” ተጣብቶናል” ሲል ስሙን ያልጠራው ትል ልቡናችንን እንደበላው አስታወቀ።

ልብ በሉ። የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ምን ያልሆነ ነገር አለ? ምን ያልተሰራበት ሴራ አለ? ታርኩ ተዛብቷል በሚል ሲያደቡ የነበሩ ጀንበር ስትውጣቸው አየን። አደዋን ከታሪኩ ሳይሆን በያሪኩ ትልቅነት ውስጥ ጼራ የቀፈቀፉ፣ ለሴራ ፖለቲካቸው ሲሉ እየተናበቡ ሃውልቱን ስንቴ አፍርሰው፣ ስንቴ ንደውት፣ ስንቴ ነቅለውት፣ ስንቴ በዶዘር ደረማምሰውት እንደነበር ….

ይህ ሁሉ ምላስ ግን የት ነበር? ይህ ሁሉ ትንተና የት ስርቻ ውስጥ ነበር የታጨቀው? ይህ ሁሉ የሴራ መዓት …. ያበደው ጠየቀ? ቅድሚያ ሰላምታ፣ እንኳን ለ180ኛው ታላቁ የነጻነት ቀን አደዋ መታሰቢያ አደረሳችሁ። ዘንድሮ አደዋ ትግራይም ተከብራል። እሰየው ነው።

“የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ ” ብለውናል። ሃውልቱ ስር ቆመው የድረሱለት ጥሪ አቅርበዋል። የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ሊፈርስ እንደሆነ በሰበር አስተጋብተዋል። ከዳር እከዳር እየተቀባበሉ ” ጋሎች የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ሊያፈርሱት ነው፣ አፈረሱት” ያሉ ወገኖች በየቀኑ አሳባቸውን ሲቀያይሩ ጥያቂ አለመኖሩ ቦሰናን ያሳዝናታል።

” ትናንት እንዲህ አልክ አልሆነም፤ ከትናንት በስቲያ ይህን ብላችሁ ነበር ውሸት ነው ብለን የማንጠይቀው ለምንድን ነው? ትላለች” ቢጨንቃት!! ያበደው በየአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ ሰበር ዜናዎች ውስጥ የሰማቸውን “ስብርባሪ ሰበር ዜናዎች አሰባቸው”

Exit mobile version