ያበደው አንድ ጀግና ታወሰው። አባቱ መቃብር ስር የሚርመጠመጡ ሰዎች ነበሩ። አባቱ የአገር ጀግና ነበር። ታልቁ የሩጫ ሰው። እናም በሃውልቱ ስር ከቤተሰብ በላይ ቤተሰብ፣ ከቤተሰብ በላይ አዛዥ፣ ከቤተሰብ በላይ ሃውልት ተንከባካቢና ዕቅድ አውጪ እየሆኑ በሚዲያ ሲቀርቡ፣ ቤተሰብ ተረሳ። መጨረሻ ላይ ቤተሰብ ሃውልቱን በሚፈልገው መልኩ ለማሰራት ሲንቀሳቀስ እኒህ ሰዎች ክልከላ አመጡ። ከብዙ ጭቅጭቅ በሁዋላ ቤተሰብ በዚህ ቆፍጣና ልጅ አቋም መብቱን አስከበረ። ይህ ጀግና ስለጉዳዩና ስለክርከሩ ሲነሳለት የሚለው ” አባቴ ሃውልት ስር ምን እንደሚያርመጠምጣቸው ነው አልገባ ያለኝ” የሚል ምላሽ ነበር የሚሰጠው።
አጤ ምኒሊክ አንዴ ቀና ቢሉ …. አጤ ምኒሊክ አንዴ፣ ላንዳፍታ ቢነሱ … አጤ ሚኒሊክ ለቅጽበት … ቦሰና ይህን ጥያቄ ደጋግም መጠየቅ ከጀመረች ሰነባብታለች። እሳቸው ሞትን አሸንፈው ምስክረነት ካልሰጡ በቀር ነገር የማይገባቸው ” ደረቅ አሳዎች” አሳስበዋታል። ያበደው በቦሰና አሳብ ይስማማል። አጤ ሚኒሊክ ላፍታ ቢነሱስ? ያበደው ዘለለ …. እያርጎመጎመ ተሳደበ። ” ተጣብቶናል” ሲል ስሙን ያልጠራው ትል ልቡናችንን እንደበላው አስታወቀ።
ልብ በሉ። የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ምን ያልሆነ ነገር አለ? ምን ያልተሰራበት ሴራ አለ? ታርኩ ተዛብቷል በሚል ሲያደቡ የነበሩ ጀንበር ስትውጣቸው አየን። አደዋን ከታሪኩ ሳይሆን በያሪኩ ትልቅነት ውስጥ ጼራ የቀፈቀፉ፣ ለሴራ ፖለቲካቸው ሲሉ እየተናበቡ ሃውልቱን ስንቴ አፍርሰው፣ ስንቴ ንደውት፣ ስንቴ ነቅለውት፣ ስንቴ በዶዘር ደረማምሰውት እንደነበር ….
ይህ ሁሉ ምላስ ግን የት ነበር? ይህ ሁሉ ትንተና የት ስርቻ ውስጥ ነበር የታጨቀው? ይህ ሁሉ የሴራ መዓት …. ያበደው ጠየቀ? ቅድሚያ ሰላምታ፣ እንኳን ለ180ኛው ታላቁ የነጻነት ቀን አደዋ መታሰቢያ አደረሳችሁ። ዘንድሮ አደዋ ትግራይም ተከብራል። እሰየው ነው።
“የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ ” ብለውናል። ሃውልቱ ስር ቆመው የድረሱለት ጥሪ አቅርበዋል። የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ሊፈርስ እንደሆነ በሰበር አስተጋብተዋል። ከዳር እከዳር እየተቀባበሉ ” ጋሎች የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ሊያፈርሱት ነው፣ አፈረሱት” ያሉ ወገኖች በየቀኑ አሳባቸውን ሲቀያይሩ ጥያቂ አለመኖሩ ቦሰናን ያሳዝናታል።
” ትናንት እንዲህ አልክ አልሆነም፤ ከትናንት በስቲያ ይህን ብላችሁ ነበር ውሸት ነው ብለን የማንጠይቀው ለምንድን ነው? ትላለች” ቢጨንቃት!! ያበደው በየአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ ሰበር ዜናዎች ውስጥ የሰማቸውን “ስብርባሪ ሰበር ዜናዎች አሰባቸው”
- የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ሊፈረስ ነው
- የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ
- የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ሳይፈርስ ስፍራ ሊቀየር ነው
- ለሊት የአጤ ሚኒሊክ ሃውልትን ለማዛወር ዕቅድ ተይዟል … ያልተባለው ምን ነበር ? ያበደው ጠይቀ። ይህ ሁሉ የሆነው በዚህ አምስት ዓመት ውስጥ ነው። አይዘነጋም። ጊዜው አልራቀም። የተዘባረቀበት ቀለም አልደረቀም። የተተፋበት አንደበትም አልተዘጋም … መካካድ አይቻልም። ጥሁፉም ቪዲዮውም በሰበርና በፎቶ ተዥጎርጉሮ ይገኛል። እንደውን እሙዚየሙ ” ክህደት ማህደር ቤት” ተቀምጧል። ጤነኖች ይማሩበታል። ወደፊት ኢትዮጵያ “የሴራ ዘናዎች ቅሌት” የሚል ዶክመንተሪ ስታዘጋጅ አትቸገርም። ያበደው ሳቀ።
- የአደዋ ድል መታሰቢያ ሲገነባ
- “የአጤ ሚኒሊክና እቴጌ ጣይቱ ሃውልታቸው የለም” በሚል የሰበር ዜናዎች ሚሳይል አየሩን ሞላው። “ተንታኞች” በየሰፈራቸው በቡድንና በግል ” ኦሮሙማና የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት አፈራረስ ” ብለው ደጋግመው ተተረተሩ። ነገዱበት። ለዲጂታል ለመናው ግብዓት አደረጉት። ሁሉም ውሸት ሆነ።
- ሁለቱም ጀግኖች በሙዚየሙ ውስጥ ሲከብሩ ” ቁመታቸውን አሳጠሩት፣ ልክ በዕውቀቱ ስዩምን መሰሉ” የሚለው ሌላኛው ሚሳይል ይተኮስ ጀመር። ከዛ ቀጥሎ “ባዶ እግራቸውን አደረጓቸው፣ የአባ ገዳ ዱላ አሲያዟቸው” የሚለው ሴራ ልውስ አረር መተኮስ ቀጠለ። ብቻ ምን አለፋችሁ… ህዝብ በሌለ የሴራ መላምት ተወዛገበ።
- በሰባና ሰማንያ ዓመት መካከል ያለው አንዳርጋቸው ጽጌ ሳይቀር “የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ” ድራማ ደራሲ ፣ አቀናባሪና መሪ ተዋናይ ሆኖ ከረመ። ሃውልቱን ተደግፎ “ድረሱ” እያለ በእለተ ቀኑ ጥሩምባ ሲነፋ ነበር።
- አንዲ ስለ አደዋ ቀደም ባሉ ጥሁፎቹ ብዙ ብሏል። አንዲ አራዳው ሙዚየም ሲገነባ እሱ ልጅ እየሰራ ነበር። ኢሳት ቢሮ ሚሽት አኑሮ ልጅ ወለደ። ኢሳት የዓመት በዓል ፕሮግራም ሲሰራ አዲሲቱን ሚስቱን እትልቁ ሆቴል ይዞ ሲመጣ ያሽቆጠቆጣት በውድ ልብስ ነበር። የብቸናዋ ውብ ገብስማው አንዲ ጎን ተሰይማ …. ያበደው ቢቀባጥርም ሃዘኑ ሰፊ ነበር። ያቺ ባለቤቱና ልጆቹ “አንዲን ልቀቁልን፣ ባሌን ልቀቁ፣ አባታችን ናፈቀን” ሲሉ ነበር። ከሞት ወደ ህይወት የተዛወረው አንዲ አዲስ አበባ አዲስ ፍቅር …… ስለ ሞራልና ስለ መታመን ለማንሳት ያህል ያበደው ዘላበደ እንጂ ከስር መሰረቱ ቢነገር …..
- የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ ዜናና ትንታኔዎች ቦነኑ። የፖለቲካው እርግጫ ቢጦዝም የአደዋ መታሰቢያ ሙዚየም በኑሮ ውድነት የሚሰቃዩትን ጨምሮ አስደምሟል። ኢትዮጵያ ላይ የተዘራው የዘር ፖለቲካ የሚወቃበት ማዕከል ስለሆነ ለበርካቶች ተስፋ ሆኖላቸዋል። በብዛት የሚሰማው ዜና መገርም ነው። ሙዚየሙ ተወዷል። እውነታው ይህ ቢሆንም “የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ” አዝማቾች አዲስ ዜማ ጀምረዋል። አዲሱን የቴድሮስን አዝማች ብዙዎች አልወደዱትም። እንደው ከሙዚየሙ ጋር ስሙ እንዲነሳ ግራውንድ እንዳደረገ የሰራት ነጠላ ነገር ናት!!
- አዲስ ሰበር
- “ይህ ሃውልት ምን ይሰራል?” የሚሉ ከቀድሞው “የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ” ዜና ባቡር ላይ የተፈናጠሩ እየተሰሙ ነው። ሌላው አስቂኙ ደግሞ ” ሃውልቱ እንዳይታይ ዛፍ እየተተከለ ነው” በሚል ድረስትም ተጀምሯል። የአጤ ሚኒሊክ ሃውልት ፈረሰ ከሚለው ሰበር ዜና አዝማችነት ” ዛፍ ተተከለ” ወደ ሚለው አዲስ አጀንዳ የተከለሱት ” አጤ ሚኒልክ ሊሽፈኑ ነው” በሚል አዲስ የሴራ ነዶ አቀብለዋል።
- ያበደው አንድ ጀግና ታወሰው። አባቱ መቃብር ስር የሚርመጠመጡ ሰዎች ነበሩ። አባቱ የአገር ጀግና ነበር። ታልቁ የሩጫ ሰው። እናም በሃውልቱ ስር ከቤተሰብ በላይ ቤተሰብ፣ ከቤተሰብ በላይ አዛዥ፣ ከቤተሰብ በላይ ሃውልት ተንከባካቢና ዕቅድ አውጪ እየሆኑ በሚዲያ ሲቀርቡ፣ ቤተሰብ ተረሳ። መጨረሻ ላይ ቤተሰብ ሃውልቱን በሚፈልገው መልኩ ለማሰራት ሲንቀሳቀስ እኒህ ሰዎች ክልከላ አመጡ። ከብዙ ጭቅጭቅ በሁዋላ ቤተሰብ በዚህ ቆፍጣና ልጅ አቋም መብቱን አስከበረ። ይህ ጀግና ስለጉዳዩና ስለክርከሩ ሲነሳለት የሚለው ” አባቴ ሃውልት ስር ምን እንደሚያርመጠምጣቸው ነው አልገባ ያለኝ” የሚል ምላሽ ነበር የሚሰጠው።
- አዎ!! ልክ ነው ሃውልት ስር በሴራ መርመጥመጥ ምን ይጠቅማል? ሃውልቱን ነበስ ያለው እታሪኩ ውስጥ ነው። የቆመው ሳይሆን ለቆመው ምክንያት የሆነው ታሪክ ውድ ነው። ማንም ምንም ቢል ይህን ውድ ታሪክ አይፍቀውም። አዋቂ ለመሆን የሚለፋደዱ አሉ። አሁን ላይ ቀንዳቸው ተሰብሯል። ጥላቻቸው መክኗል። ያስቸገሩት ወዳጅ መስለው ሃውልቱ ስር ሴራ የሚገምዱት ናቸው።
- ቦሰና ሃውልቱ እንዳይታይ ዛፍ እየተተከለበት መሆኑንን አንዱ ” ዓለም ዓቀፍ ጋዜጠኛ” አጀንዳ ሰፍሮ መርጨቱን ስትሰማ “አንተ ምን አለብህ ዘርህን ዝራ” ብላ በቆረጣ ወደ ስንዴ ዘር ገባች። ስንዴ በብዛት እየተመረተ ነው። አፋርና ሶማሌ ክልል ጤፍ እያለሙ ነው። አሁን ኢትዮጵያ በዕርግጥ ሰላማዊ የፖለቲካ መፍትሄ ቢበጅላት መመንደጓ የማይታበል ሃቅ ነው።
- ትግራይ አደዋ በዓሉ ተክሯል። ፕሬዚዳንቷ አደዋ ተገኝተው አልቅሰው ተናገሩ። ሁለት ልጆቿን ያጣች እናት ” ያንቺ እቃ ልጆቼን ይመልስልኛል” ብላ ጥያቄ ማቅረቧን አስታወሱ። በዙ እናቶች ባዶ ቀርተዋል። ፕሬዚዳንቷ ከጦርነቱ በሁዋላ ያገኙዋት እንድ እናት የተናገረችውን ሲያነሱ የትህነግ የፖለቲካ አመራሮ፣ ባለስልጣኖች፣ የጦር አዋጊዎች … ሁሉም ይሰሙ ነበር። ምን ተሰምቷቸው ይሁን? መቼም ማን? ለማን? ምን ፈልጎ? እንዴት? የት? መቼ? ጦርነቱን ጀመረ? ምን ውጤት አስከተለ? እናቶች ልጆቻቸውን እየመረቁ ወደ ጦር ሜዳ እንዲልኩ የቀሰቀሱ ምን ተባሉ? ያበደው አነባ። ሲፈልጉ የውጊያ ፊሽካ ይነፋሉ። ሳይሆን በውይይት ጉዳያቸውን ይፈጽማሉ። ደሃ እንደወጣ ይቀራል። መሪዎቹ ያው እንዛው ናቸው። ቧ! አለ ያበደው “ዞሮብናል”
- እባክዎት ላፍታ ቀና ይበሉ። እርስዎ ተነስተው ምስክር ታልሆኑ የሚሆን አልሆነም። ሃውልትዎ ስር የሚርመጠመጡ ልክ የላቸውም።፡ማን እንዳከበረዎ፣ ማን እንዳቀለልዎ መስክሩ። ቋሚው ጥቂት ሚዛናቸው በተሰበረባቸው የተዥጎረጎረ ነው። እርሶዎ በዛ ብልሃትዎ ካልገሰጹ ልክ አይሆንም። ሴራው ለጉድ ነው። አለያም ደብዳቤ …. ያበደው ጤንነት ተሰማው!!
- አሁን ይብቃ። ችግር አለ። አለመጋባባት አለ። ተኩስ አለ። መገዳደል አለ። ጥላቻውና የዘር ፍጅቱ በሚገርም ፍጥነት ተጋራዊ እንዲሆን ቢቆሰቆስም አልሆነም። ይሁን እንጂ በጊዜ ካልበረደ ያሰጋል። ሴራ ቀርቶ ውይይት ይንገስ። ህዝብ ሰልችቶታል። ህዝብ ሰላም ናፍቆታል። ዘርኝነት ይውደም። የኢትዮጵያ አቆርቋዦች ይወደሙ። በጠብመንጃ ሳይሆን በንግግር!! ደጎል መናፈስ ይፈልጋል። ክረምት የመዝናኛ ወቅቱ ስለሆነ ኮንዲሽኑንን ይጠብቃል። ጉልበት ከሌለው በክረምት አሯሯጭ እንጂ ቀማሽ አይሆንም። እናም ልንከባከበው። ቦሰናም እንክብካቤ ትሻለች። አደዋ ሙዚየምን ጎብኙ!! የዘር ፖለቲካ ማራገፊያ ማዕከል ነውና ተንከባከቡት!! ሰላም ይብዛላችሁ!!