Site icon ETHIO12.COM

የኛ ምርጫ!

የተመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን ተከትሎ የአንዳንድ ድርጅቶችን ዕጩወች ለመመልከት ሞክርያለሁ።
ከአገር አቀፉ አንፃር የአዲስ አበባዉ ነዉ ቀልቤን የሳበኝ። በዚህ በኩል በዕጩነት የቀረቡትን ለመመልከት እንደሞከርኩት ብልፅግና(አማራወቹን ብቻ ነዉ ያወቅኳቸዉ) ከመቸዉም ጊዜ በቸሻለ የተሻሉ ዕጩወች እንደቀረቡ ተመልክቻለሁ። በተለይም በሴራ ፖለቲካ ስትታመስ ለምትዉለዉ አዲስ አበባ እንደነ ዶ/ር ሲሳይ አይነቶቹ እና ሌሎችም የሴራ ፖለቲካን የተረዱ ሰወች ለምርጫ መቅረባቸዉ የአዲስን ፖለቲካ ፈር ያስይዘዋል ብየ አስባለሁ። በርግጥ ይህ የሚሆነዉ ብልፅግና አዲስ ላይ አሸናፊ ከሆነ ነዉ።

ሌላዉና ትኩረቴን ለመሳብ እየሞከረ ያለዉ የአማራ ክልል ምርጫና ተወዳዳዳሪወችን የተመለከተዉ ጉዳይ ነዉ ። በተለይም የአብንና የአማራ ብልፅግና የዕጩ አቀራረብ ቀልቤን ለመሳብ እየሞከረ ነዉ።

አብን እንደ አዲስ ተወዳዳሪ አካል በበርካታ የምርጫ ክልሎች ለዉድድር የቀረበ መሰለኝ። ያልቀረበበት የምርጫ ክልል ካለ አላወቅኩም። ይሄም ሁኖ በዚህ አጭር ጊዜ ዉስጥ በዚህ ልክ ተዘጋጅቶ መገኘቱ በራሱ አበረታች ነገር ነዉ። ከክልሉ ዉጭም ሰፋቱን ባላዉቅም ጅምር ስራ አይቻለሁ።

ከዕጩወች አኳያ እስካሁን ባለዉ ሁኔታ ብዙወቹ የተማሩ(ዶ/ር የበዛበት) መሆኑን ታዝቢያለሁ። በርግጥ ይሄ የሙህር ሽፋን ምን ያክል እንደሆነ በግልፅ አልታወቀም። ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምናየዉን ብቻ አይተን ነዉ እየተናገርን ያለነዉ። ያም ሆነ ይህ ግን አብን ዉስጥ ሙህራን በስፋት እንደተሳተፉበት ታዝቢያለሁ። በአንድ ጎኑ አበረታች ነገር ነዉ።

የአማራ ብልፅግና የዕጩ አሰላለፍንም እንዲሁ በተባራሪ ለማወቅ ሙከራ አድርጊያለሁ። ብልፅግናም ቢሆን ከሙህራን አንፃር ብዙም የሚታማ ሁኖ አላገኘሁትም። የተወሰኑ አ/አደሮችም አሉ፣ይሄንን ጉዳይ በበጎ ጎኑ እንመልከተዉ። ያም ሁኖ በግርድፉ እንደተረዳሁት ብልፅግና ለፖለቲካ ልምድም ትልቅ ግምት የሰጠ ይመስለኛል።ይሄም በአንድ ጎኑ ጥሩ ነዉ።

የኔ ትዝብት ማጠቃለያ!

አብንና ብልፅግና ከየራሳቸዉ እሳቤና የማሸነፍ ግምት ተነስተዉ ዕጩወቻቸዉን አቅርበዋል። በዚህ በኩል ሁለቱም ፓርቲወች ጥሩ እርቀት እንደሄዱ ይሰማኛል።

ነገር ግን የኛ አገር ህዝብ ምርጫን የሚመርጠዉ ድርጅትን ወይስ የቀረበዉን ግለሰብ ስዕብና እና ማንነት በማየት ነዉ? ይሄን ጉዳይ ሁለቱም ድርጅቶች በደንብ አስበዉበታል?

Chuchu Alebachew FB

Exit mobile version