Site icon ETHIO12.COM

ሕንድ ውስጥ ከኮቪድ ያገገሙ ሰዎች ዓይነ ስውር በሚያደርግ ‘ብላክ ፈንገስ’ እየተጠቁ ነው

አሁን ደግሞ የሕክምና ባለሙያዎች ከኮቪድ-19 እያገገሙ ባሉና ባገገሙ ሕመምተኞች ላይ ‘ብላክ ፈንገስ’ የተባለ በሽታ እያዩ ነው። በሕክምና ቋንቋ ሙክሮሚኮሲስ የሚሰኘው ይህ በሽታ ሰው ለይቶ የሚያጠቃ ነው።

ብዙ ጊዜ ይህ በሽታ የሚመጣው ከአፈር፣ ዕፅዋት፣ የከብቶች ኩበት አሊያም ከበሰበሰ ፍራፍሬና አትክልት ነው። በሽታው ወደ ሰውነታችን አየር የሚገባባቸው ቀዳዳዎችን እንዲሁም ሳንባን በማጥቃት በተለይ ደግሞ ተደራቢ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ሊገድል ይችላል።

በተለምዶ የስኳር [ዳያቢቲስ] በሽታ ያለባቸው ሰዎች፣ የሰውነት የመከላከል አቅማቸው የደከመና የኤችአይቪና ካንሰር ተጠቂዎች በዚህ በሽታ የመሞት ዕድላቸው የሰፋ ነው።

ዶክቶሮች ይህ የመግደል አቅሙ 50 በመቶ የሆነ በሽታ የተስፋፋው በኮቪድ-19 እጅግ የታመሙ ሰዎች የሚወስዱትን ኃይል ሰጪ መድኃኒት ተከትሎ ነው ይላሉ።

ስቴሮይድስ አሊያም ደግሞ ሰው ሰራሽ ሆርሞን የሚባሉት ሳንባ እንዳይቆጣ በማድረግና የሰውነት መከላከል አቅምን በመጨመር ይታወቃሉ። ነገር ግን ዳያቢቲስ ያለባቸው እንዲሁም የለሌባቸው ሰዎችን የመከላከል አቅምን ሊያዳክሙም ይችላሉ። በዚህ ጊዜ ነው ይህ ሙኮርሚኮሲስ የተሰኘው በሽታ የሚቀሰቀሰው ሲሉ ዶክተሮች ያብራራሉ።

በሁለተኛው ማዕበል እጅግ በተመታችው ሙምባይ ውስጥ ባሉ ሶስት ሆስፒታሎች የሚሠራው ዶክተር ናይር ከባለፈው ወር ጀምሮ ቢያንስ 40 ሰዎች በዚህ በሽታ ሲጠቁ ማየቱን ይናገራል።

ከባፈለው ታህሣሥ እስከ የካቲት ባለው ጊዜ በአምስት ዋና ዋና ከተሞች 58 ሰዎች በዚህ በሽታ የተጠቁ ሰዎች ተገኝተዋል። አብዛኛዎቹ ሰዎች በዚህ የሚጠቁት ከኮቪድ-19 ካገገሙ በኋላ ከ12-15 ባሉት ቀናት ነው።



የሙምባይ ሳዮን ሆስፒታል ባለፉት ሁለት ወራት 24 ሰዎች በዚህ ሰው ለይቶ በሚያጠቃ በሽታ መያዛቸውን ሪፖርት አድርጓል። ከእነዚህ ሰዎች መካከል አስራአንዱ አንድ ዓይናቸውን እንዲያጡ ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በቤንጋሉሩ ከተማ የዓይን ቀዶ ጥገና ባለሙያ የሆኑት ዶክተር ራንጉራጅ ባለፉት ሁለት ሳምንታት 19 በሙኮርሚኮሲስ የተጠቁ ሰዎች ማየታቸውንና አብዛናዎቹ ደግሞ ወጣቶች መሆናቸውን ይናገራሉ።

ዶክተሮች ይህ በፈንገስ የሚመጣው በሽታ በሁለተኛው ማዕበል እንዲህ በፍጥነት መስፋፋቱ እንዳስደገነጣቸው ይናገራሉ። ዶ/ር ናይር ባፈለው አንድ ዓመት ሙምባይ ውስጥ 10 በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች ማግኘቱን ያስታውሳል። ነገር ግን በዚህ ዓመት እጅግ በፍጥነት መስፋፋቱን ይናገራል።

በዚህ በሽታ የተያዙ ሰዎች አፍንጫቸው ይታፈናል፣ ይደማል እንዲሁም ዓይናቸው አካባቢ እብጠት ሕመም ይሰማቸዋል። ትንሽ ቆይቶ የማየት አቅማቸው እየተዳከመ ይመጣና በስተመጨረሻ ዓይነ ስውር ይሆናሉ። ይህን በሽታ ለመከላከል የሚረዳው መድኃኒት አንዱ 48 ዶላር የሚሸጥ ሲሆን ይህን መድኃኒት ለተከታታይ ስምንታት መውሰድ ግድ ይላል።

via – bbc amharic

Exit mobile version