Site icon ETHIO12.COM

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን አፀደቀ፡፡

ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም.፣ አዲስ አበባ፤ የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ጉባኤው የፌዴራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር ረቂቅ አዋጅን መርምሮ አፅድቋል፡፡

ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳቡን ለም/ቤቱ ያቀረቡት የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ አቡ ብርኪ ም/ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ለዝርዝር እይታ ወደ ቋሚ ኮሚቴው ከመራ ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት ከአስረጂዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገበትና በቂ ግብዓትም የተገኘበት መሆኑን ለም/ቤት አስረድተዋል፡፡

በውይይቱም የጥብቅና ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳደር አገልግሎት ላይ ሰፊ የህግ፣ የአሰራር፣ በአንዳንድ ጠበቆች ላይ የብቃትና የስነ-ምግባር ችግሮች እየተስተዋሉ መምጣቱን በጭብጥነት መለየታቸውን አብራርተዋል፡፡

አያዘውም የጥብቅና ፍቃዱ ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑ አገልግሎቱ በሚጠበቅበት ደረጃ እንዳያድግና የሙያ ነጻነቱን በተበቀ መልኩ አገልግሎቱ እንዳይሰጥ ማድረጉ እንዲሁም የጥብቅና ህጎች ሀገሪቱ ካለችበት አጠቃላይ ኢኮኖሚዊ፣ ማህበራዊና ፓለቲካዊ እንቅስቃሴዎች አንጻር ሊኖሯት የሚያስፈልጉ የጥብቅና ድርጅቶችን በተደራጀ ሁኔታ የሚመሩ ተበቆች አለመሆናቸውን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

በረቂቅ አዋጁም አንዳንድ አንቀጾችን ሙሉ በሙሉ በሌሎች አንቀጾች ከመተካት ጀምሮ በርካታ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ነው ባቀረቡት ሪፖርት የተቆሙት፡፡

በመጨረሻም የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳዳር ረቂቅ አዋጅ የሀገሪቱን ዜጎች ፍትህ የማግኘት እና የህግ የበላይነት በማረጋገጡ ሂደት ጠበቆችና የጥብቅና ድርጅቶች የሚኖራቸው ድርሻ የጎላ እንዲሆን እንዲሁም የጠበቆችን ብቃትና የስነ ምግባር ችግር የሚፈታ፣ መብትና ነጻነት የሚስጠብቅ፣ የተገልጋችን መብት የሚስከብር በመሆኑ ም/ቤቱ ረቂቅ አዋጁን እንዲያፀድቀው የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የፌደራል የጥብቅና አገልግሎት ፍቃድ አሰጣጥና አስተዳዳር ረቂቅ አዋጁ አዋጅ ቁጥር 1249/2013 ዓ.ም አድርጎ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል፡፡

በኃ/ሚካኤል አረጋኽኝ via – attorney general

Exit mobile version