ETHIO12.COM

ሕዝብ አሸነፈ!! “የትህነግ ሽርሽራፊ ሃይል ሙትና ምርኮኛ ሆኗል”

አሜሪካ ተገዳ አቋሟን በሚያስደንቅ ቅጽበት ሞርዳ ብቅ ማለቷን ተከትሎ ኢትዮጵያውያን ወሳኝ የተባሉ ድሎችን አስመዝገበዋል። እያስመዘገቡም ነው። ለዚህ ሁሉ ድል ዋናው ሃይል ሕዝብ መሆኑ ደግሞ ደስታውን እጥፍ እንደሚያደረገው አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ። ” ሕዝብ አሸነፈ” ሲሉ የተናገሩ እንዳሉት ድሉ ደረት የሚያስነፋ ግን አይደለም። የህዝብ ልጆችም በበረሃ ድል ተቀዳጅተዋል።

ባሳለፍነው ሁለት ሳምንታት ውጥረቱ ተባብሶ ነበር። የትህነግ ደጋፊዎችና የሴራ አምራች ናቸው የሚባሉት ሚዲያዎች የኔቶ ሃይል እንደሚገባ በስፋት ያስታውቁ ነበር። ቀደም ሲል ሰላም አስከባሪ ሃይል እንደሚገባ፣ ሰላም አስከባሪ ሃይል ሲገባ ከኤርትራ ጋር ውጊያ ለመግጠም መታቀዱ በስፋት ተወራ። የሴኩሪቲ ካውንስል ” ኢትዮጵያን፣ ክብሯንና ሉዓላዊነቷን አጥብቄ አከብራለሁ” በማለት “የሰላም አስከባሪ ይግባ” ጥያቄ ላይመለስ ቀረቀረው። ከዛ ኔቶ መግባት እንዳለበት ለማሳመን ወትዋቾቹ የመርዝና የኬሚካል ወሬ ማራገብ ጀመሩ። ረሃብና ችጋር ከሚፈለገው በላይ ተለጥጦ በችግር ላይ ባሉ ወገኖች የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት ጥድፊያ ተገባ።

ሕዝብ ይህ ሁሉ ሲሆን ዝም አላለል። ” አትግቡብን፣ በድህነትም ቢሆን እኖራለን እንጂ በክብራችን አንደራደርም” ሲል ከዳር እሰከዳር ተነሳ። ልዩነት ወደ ጎን ተወረወረና የአገር ህልውና ቀደመ። በውጭ አገርና በአገር ውስጥ ህዝብ እንደ አንድ ተጋምዶ ድምጹን አሰማ። መሪዎች ” ከቶ አይደረግም” ብለው ህዝብን ተከተሉ። ክህዝብ አሳብ ላይ ቆመው መሩ። መሪና ተመሪ ተጋመዱ። መንግስት በታሪኩ ” ቀንድ” ሆኖ ሰነበተ። አማረበት።



ይህ የገባቸው አቋማቸውን ሞርደው ” ከምርጫ በሁዋላ የሰላም ስምምነት” በሚል ህዝብና መንግስት አብረው የሚሰሩትን ቁልፍ ጉዳይ አጎሉ። ሕዝብ አሸነፈና ይህን ሰማን። ይህ በተሰማ ቀናት ውስጥ አልሸነፍም ባዮች ” የኬሚካል ቦንብ በመጠቀም ተምቤንን መንግስት አወደም” ሲሉ የተጭበረበረ ሰነድና ምስል አሰራጩ። ማርቲን ፓውሌት በስሙ ባዘጋጀው የዌብ ሳይት ላይ ይህንኑ አተመ። ሌሎችም ተቀባበሉት። ኢትዮጵያ አካሏ ትግራይን ለማጥፋት መርዝ የጫነችበት የፈጠራ የበረራ ቁጥር ሳይቀር ታተመ።

ይህ ሁሉ የሆነው የጂ ሰባት አገሮች ስብሰባ ሊካሄድ ቀናት ሲቀሩት ነበር። በተመሳሳይ ሱዳናዊቷ የሲኤን ኤን ሪፖርተር ኒማ አልባጊር የምትመራው “የአሜሪካ አውሮፓ የትግራይ አስቸኳይ እርዳታ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ” ተደረገ። በውይይቱ የአውሮፓ ኮሚሽን ከፍተኛ ሰዎችን፣ ከአፍሪካ ሕብረትና ዋናዎቹ ኢትዮጵያን በተላትነት የነከሱት የቁማሩ ተጋሪዎች  የዩኤስአይዲ ሳማንታ ፓወር፣ የተመድ የሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ፣ እንግሊዛዊው የተባበሩት መንግስታታ የሰብአዊ እርዳታ ዘርፍ ሃላፊ ሰር ማርክ ሎውኮክ እየተረዳዱ ኢትዮጵያ ላይ የአድማ መርዝ ረጩ።



ይህ ሲሆን የትህነግ ሰዎች ለደጋፊዎቻቸውና ሃሰት እየጋቱ በመከራ ለሚያሰቃዩዋቸው ምስኪኖች ” ምርጫው አይካሄድም፣ የኔቶ ሃይል የገባል፣ የማሸነፊያው ደወል ተቃርቧል” የሚል ዜና አሰርጭተው ነበርና የጂ ሰባት አባል አገሮች ስብሰባ ለኢትዮጵያዊያን ምጥ፣ ለትህነግ ወዳጆች፣ መሃል አገር ላሉና በውጭ ሆነው አገራቸውን ለሚያላምጡ ባንዶች የደስታ ማማ ሆነላቸው።

ደስታው የሸተታቸው የጁንታው ቅልብተኞች ደስታቸውን መድበቅ በማይቻላቸው ደረጃ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው በምርጫው ላይ ቀለዱበት። በርቱካን ሚደቅሳን ” ባንዳ” ብለው እስከመስደብ ደረሱ። ምርጫው ተኮላሽቶ፣ ኔቶ ትግራይ ገብቶ፣ የኢትዮጵያ ሰራዊት በኔቶ ዱላ ሲረፈረፍና እግሬ አውጪኝ ሲል በምናብ እያዩ “ቺርስ” አሉ። በምናብ ሲያብዱ ትግራይ ችግር ላይ ያሉ ህጻናት ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ፣ ህዝብ ክትባት እንዳይወስድ፣ ዘወትር የረሃብ ወሬ እንዲወራ፣ ችግሩ እንዲባባስ ከመግፋት በዘለለ ያበረከቱት አንዳችም በጎ ነገር ግን አልነበረም። እህል እየሰረቁ ከሚሸጡት ግፈኞች ጭምር!!

አንድ እግራቸውን ምርጫ ውስጥ ነክረው በአንደኛው የሴራው ሰፈር የሚውሉት ” ቅምጦች” ምርጫውን ባለቀ ሰዓት በመሰናበት አገርና ህዝብ ሊክዱ ያድሙ ነበር። የቅድመ ምርጫ ታዛቢዎች እንዳሉት ” ህዝብ እንዲህ ያለውን ጉዳይ የሚሰማበት ጆሮ የለውም” እናም አሜሪካ በዚሁ መረጃ ተገዳ ” ቅድሚያ ምርጫ” ስትል እነዚህ ባንዳ ፖለቲከኞች ሴራቸው ከሸፈና አደባባይ ወጥተው ሊሸጡት ሲያሴሩበት የነበረውን ሕዝብ ” ግብር ከፋዩ ሕዝባቸን” በሚል ጠርተውት ” ምርጫውን ጥለን አንወጣም” ሲሉ ሃፍረታቸውን ተነፈሱ። ሕዝብ አሸነፈ ማለት ይህ ነው። ሕዝብ ለዓመጽና ለሴራ ” ጥሪ አይቀበልም” የሚል ምልሻ ሲሰጥ፣ በአገሩ ጉዳይ ” ቀልድ የለም” ሲል ታየ!!

ሕዝብ በአሸናፊነት ስሜት ውስጥ ሳለ የጂ ሰባት አገሮችም እንደተባለውና ሲወሰን ለመጨፈር ከበሮ ጸሃይ ላይ ሲቀቅሉ የነበሩ ባልጠበቁት ሁኔታ ” ተመካከሩ” ብለው አረፉት። አሁንም ሕዝብ አሸነፈ። በውላዳብ አማቅ ለበሰው አባቶች ያነቡላት አገር፣ እናቶችና ህጻናት በንብርክክ እየሄዱ የሚጸልዩላት አገር፣ ከሁሉም በላይ ያለ ምክንያት፣ ባጎረሰ እጁን ተነከሰ እንዲሉ የታረደው፣ የተሰቃየውም እንደ ባዕድ የታየው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ድም ይጮህ ኖሯልና አምላክ ሰማ።

በዚህ ሁሉ ስሜት ውስጥ ሌላ ዜና ተሰማ። የኢትዮጵያ አለኝታ የሆነው የኢትዮጵያ መከላከያ ዘንዶ ሆኖ መሬት ለመሬት በመሳብ የተረፈውን የትህነግ ሃይል ደምስሷል። በርካቶቹን ይዟቸዋል። የትግራይ ሕዝብ ነጻ የሚወጣበትና ወንጀለኞች ተይዘው ለፍርድ የሚቀርቡበት ቀን የተቃረበ ይመስላል።


Exit mobile version